Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 4

St Joseph Novena 2013 4

 4ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ ታማኝ አገልጋይ (ጸሎተ ተሰዓቱ - ኖቬና)

4ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ ታማኝ አገልጋይ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በሕይወት ዘመንህ አንተ አንድ ዓላማ ብቻ ነበርህ ፤ ሥጋ የለበሰው ቃል - ኢየሱስን ማገልገል፡፡ እግዚአብሔር በደግነቱ በአንተ ላይ ያፈሰሳቸወ ፀጋዎችና ስጦታዎች ጌታችንን እንድታገለግል የተሰጡህ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ቃልህ፣ ሐሳብህና ድርጊትህ ለወልደ እግዚአብሔር ፍቅርና ክብር አክብሮት ነበረው፡፡  ለእግዚአብሔር ቤት በመንጠንቀቅህ የታማኝና የጥሩ አገልጋይ ሚናህን በሚገባ ተውጥተሃል፡፡ መታዘዝህ እንዴት ፍጹም ነበር! የቤተሰብ አባት በመሆንሀ ማዘዝ ሲሆን የሚጠበቅብህ ነገርግን በተጨማሪ ደቀ መዝሙሩ ነበርክ፡፡

ለሠላሳ ዓመታት ሥጋ የለበሰው አምላክ ፍጹም በሆነ መልኩ ሲታዘዝህ ነበር፤ አንተም ወደደከው፤ ራስህም ከእርሱ እየተማርክ በሥራ ላይ አዋልከው፡፡ ያለምንም እንከን ለእግዚአብሔርና ለኅሊናህ ተገዛህ፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያምን እንድትንከባከባት እግዚአብሔር በመልአኩ ሲነግርህ ምንም እንኳን የወልደ እግዚአብሔርን መጽነሷ በሚስጥር የተከበበ ቢሆንም ሳታመነታ ታዘዝክ፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ከሕጻን ኢየሱስና እናቱ ጋር ወደ ግብጽ እንድትሰደድ ስትታዘዝ ምንም ሳታጉረመርም እሺ አልክ፡፡ ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሕልም ወደ ናዝሬት እንድትመለስ ሲመክርህ ሳታቅማማ ታዘዝክ፡፡ በማናቸውም ሁኔታ መታዘዝህ እምነትህ ፍጹም፣ ልብህ ትሑት፣ ፍቅር ለመስጠት ዝግጁ እንደሆንክ ያሳያል፡፡ የታዘዝከውን ሁሉ አንዳች ችላ ሳትል ፈጸምክ፡፡ የጥሩ አገልጋይ መገለጫ የሆነ ፍጹም ቅድስና ነበረህ፡፡ እያንዳንዱ የሕይወትህ ጊዜ - ሥራ፣ እርፍት፣ መከራ፣ እንቅልፍ ... ለጌታችን የተቀደስ አገልግሎት የተሰጠ ነበር፡፡

ለግዴታዎችህ ታማኝ በመሆንህ ማንኛውንም መሥዋዕትነት በደግነትና በደስታ ከፈልክ፡፡ ፍጹም ደግነት በተሞላው ታማኝነት ምስጋናን ሳትሻ ያለደመወዝ በትጋት ሠራህ፡፡ ሕይወትህን በሙሉ ለኢየሱስና ለማርያም እስከሞት ድረስ ታዛዥ ሆነህ አሳለፍክ፡፡ እግዚአብሔር ባቀደወ መልክ በሰው ልጅ የማዳን ሥራ ወስጥ ተሳተፍክ፡፡ መለኮታዊ ልጁን እንድትንከባከበውና እንድትከላከልለት በአደራ ሰጠህ፡፡ የድህነትና የመከራ ሕይወት አሳልፈክ፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር በሥቃዩና በሞቱ ዓለምን ያዳነው አንድያ ልጁ መከራ ተካፋይ እንድትሆን ስላቀደ ነው፡፡ በእነዚህ ኃላፊነቶች ሁሉ ልዑል እግዚአብሔር ታማኝ አገልጋይ ሆንህ አገኘህ፡፡ በመጨረሻም በሚወደው ልጁና ቅድስት እናቱ እጅ ወደ ዘለዓለም ሕይወት ተሻገርክ፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ታማኝ አገልጋይ ሆንህ ስለተገኝህ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ እንደ አንተ ታማኝ አገልጋይ እንድንሆን ፀጋ አሰጠን፡፡ የራሱን ሳይሆን የአባቱን ፍቃድ ለመፈጸም ወደ ዓለም የመጣውን ኢየሱስን ፍጹም እንዳገለገልከው እኛንም ለአገልግሎት አነሳሳን፡፡ ፍቃዱን መፈጸም እንድንችል ኃይልና ብርታትን አሰጠን፡፡ ለሥጋችንም ሆነ ለነፍሳችን የሚያስፈልገንን እግዚአብሔር እንደሚስጠን እንድናምን እርዳን፡፡ ፈተና ሲገጥመን ሳንረበሽ በእርሱ በመተማመን ሁሉን ችለን እንደምንወጣ እናውቀው ዘንድ  አሳየን፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን የሚያሰገኘውን ደስታና ክብር የሚስተካከል ሽልማት የለምና እንደአንተ ደግና ታማኝ አገልጋይ እንድሆን እርዳን ፡፡ አሜን፡፡

እጅግ ታማኝ አገልጋይ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ - ለምንልን፡፡

(በየዕለቱ የሚደገም)

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እኔ ደካማው ልጅህ ሰላም እልሃለሁ፡፡ አንተ የሚወዱህንና የሚያክብሩህን ትከላከላለህ፤ ታማልዳቸዋልህ፡፡ በአንተ ላይ ልዩ የሆነ መታመን እንዳለኝና ከአዳኜ ኢየሱስና ከቅድስት እናቱ በመቀጠል የደኅንነት ተስፋዬ አንተ ነህ፡፡ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር ወዳጆችን ለመርዳት ከቶ አታመነታም፡፡ ስለዚህም በትህትና ስምህን እጥራለሁ፡፡ ከምወዳቸው እና የቅድስት ቤተስብ አፍቃሪ ከሆኑት ጋር አማላጅነትህን በመተማመን ወደ አንተ እንቀርባለን፡፡ ለአዳኛችን ኢየሱስና ለወላዲተ አምላክ ባለህ ፍቅር በዚህች አለም እስካለንና በሞታችን ጊዜ እንዳትለየን እንለምንሃለን፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም እጮኛ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ንጹሕ፣ ትሑት፣ በቸርነት የተሞላ አዕምሮና ፍጹም ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛት ጸጋ አሰጠኝ፡፡ አንተ በኢየሱስና በድንግል ማርያም እጅ እንደትክ እኔም ተመሳሳይ ዕድል ያጋጥመኝ ዘንድ መሪ፣ አርአያ እና አባት ሁንኝ፡፡

አፍቃሪና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለመንፈሳዊና ለየእለቱ በጎነት በተለይ ደግሞ መልካም ሞት አገኝ ዘንድ በዚህች ሰዓት በልቤ ውስጥ ያለውን አሳብ አስፈላጊ የሆኑትን ጸጋዎች ከኢየሱስ መለኮታዊ ልብ ታሰጠኝ ዘንድ አማላጅነትህን እማጸንህለሁ፡፡

/እዚህ ላይ በልብ ያለውን አሳብ መጥቀስ/

ሥጋ የለብሰው ቃል ጠባቂ ስለእኔ የምታቀርበው ጸሎት በእግዚአበሔር ፊት እንደሚሰማ እተማመናለሁ፡ አሜን፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም እጮኛ፣ አፍቃሪና ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጥበቃህናን እርዳታህን የፈለገ፣ መጽናናትን ሳያገኘ የቀረ ማንም የለም፡፡ በቅዱስነትህ በመተማመን እነሆ ወደ ፊትህ እቀርባለሁ፡፡ የመድኃኒታችን ምድራዊ አባት ሆይ ልመናዬን በቸርነት ተቀበለኝ እንጂ ችላ አትበለኝ፡፡ አሜን፡፡

የቅዱስ ዮሴፍ መዝሙር

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጠብቀን

ወደ ገነትም አድርሰን፡፡

የፈጠረ ሁሉን

ቢወለድ በበረት

አንተ አባት ብትሆን

አገባኸው ከቤት ፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት