Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 7 እና 8

Untitled 1 Recovered

7ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ የሠራተኞች ባልደረባ

ጸሎተ ተሰዓት (ኖቬና) ዘቅዱስ ዮሴፍ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በናዝሬት ከተማ ኑሮህን  ስትገፋ በአናጢነት ሙያ ነበር፡፡ አንተና ልጅህ በጉልበት ሥራ በቅንነት እንድትሠማሩ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የጉልበት ሥራ ለሚሠሩ ሁሉ  አርአያ ነህ፡፡ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም የመጣው በአብላጫው በድህነት ለሚኖሩት ነው፡፡ በነቢዩ ኢሳይያስ አስቀድሞ የተነገርው “ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና” ነውና፡፡

ምድራዊ ተልዕኮህ እንደ ማንኛውም ለፍቶ አዳሪ በመደበኛ ሥራ እንድትሠማራ ነበር፡፡ ልጅህም ከአንተ ተምሮ በጉልበት በማገልገል ይህንን ሙያ አከበረው፡፡ ይህን በማደረጉ ጌታቸን የሚያስተምረን በትሁንታን ቅን ሥራ የተሠማሩ ጥረው ግረው ራሳቸወንና ቤተሰቦቻቸወን የሚደግፉ ሠራተኞች በእርሱ ዘንድ ዋጋ እንዳላቸው ነው፡፡ በናዝሬት ከተማ ስትኖር የእለቱ ሥራህ ትሕትናን እንድትለማመድ አደረገህ፡፡ ክልጅህም በየቀኑ አካሄዱ ትሕትናውን ለመማር፣ ለመለማመድና የራስህ ለማድረግ አስቻልህ፡፡ ለምድራዊ ኑሮህ የመረጠልህ የነገሥታትን ቤተመንግሥት ወይንም የሊቃውንትን አዳራሽ ሳይሆን ያችን የናዝሬቷን ደሳሳ ጎጆን ነበር፡፡ በዚያች ውስን ቦታ በትሕትና በህቡዕ ወልደ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር አበሮ ለፋ፡፡ ይህም ሥራ ለእኛ አሁን በተለያያ ሙያ ለተሠማራነው ሠራተኞች ትልቅ አብነት ሆነ፡፡

እጅህ በሥራ ቢጠመድም አዕምሮህ በጸሎትና በአስተንትኖ ክእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡ “እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ" /ዮሐ 14፡6/ ካለው የእግዚአብሔር ልጅ ጋር በመሥራትህ ሁሉን ነገር በጸሎት መንፈስና ፈጣሪህን ደስ በሚያሰኝ መልክ ማድረኝ ተለማመድክ፡፡ ምክንያቱም እርሱ ሁሉን ነገር በአባቱ ፈቃድ፣ ለአባቱ ክብር ያደርግ ስለነበር ነው፡፡

ኢየሱስ ዝቅ ብሎ እንደአናጢ ሲሠራ ባየኸው ጊዜ ስለእርሱ በልብህ ያለው የእምነት ብርሃን አልቀነስም፡፡ ከጎንህ ሆኖ እየታዘዝህ የሚያገለግልህ በእውነትም የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን አልተጠራጠርህም፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በእንጨት ሥራ ቦታሀ ከኢየሱስ ጋር ጎን ለጎን ለመሥራት በመቻልህ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ በገዛ እጃችን ሠርተን ራሳችንንና ሌሎችን መርዳት እንድንችል ፀጋ አሰጠን፡፡

እንደ አንተ በትሕትና፣ በትጋትና በጸሎት መንፈሰ ከአምላካችን ጋር ተሳስረን መሥራትን አስተምረን፡፡

እጅግ ታዛዥ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ - ለምንልን፡፡

(በየዕለቱ የሚደገም)

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እኔ ደካማው ልጅህ ሰላም እልሃለሁ፡፡ አንተ የሚወዱህንና የሚያክብሩህን ትከላከላለህ፤ ታማልዳቸዋልህ፡፡ በአንተ ላይ ልዩ የሆነ መታመን እንዳለኝና ከአዳኜ ኢየሱስና ከቅድስት እናቱ በመቀጠል የደኅንነት ተስፋዬ አንተ ነህ፡፡ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር ወዳጆችን ለመርዳት ከቶ አታመነታም፡፡ ስለዚህም በትህትና ስምህን እጥራለሁ፡፡ ከምወዳቸው እና የቅድስት ቤተስብ አፍቃሪ ከሆኑት ጋር አማላጅነትህን በመተማመን ወደ አንተ እንቀርባለን፡፡ ለአዳኛችን ኢየሱስና ለወላዲተ አምላክ ባለህ ፍቅር በዚህች አለም እስካለንና በሞታችን ጊዜ እንዳትለየን እንለምንሃለን፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም እጮኛ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ንጹሕ፣ ትሑት፣ በቸርነት የተሞላ አዕምሮና ፍጹም ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛት ጸጋ አሰጠኝ፡፡ አንተ በኢየሱስና በድንግል ማርያም እጅ እንደትክ እኔም ተመሳሳይ ዕድል ያጋጥመኝ ዘንድ መሪ፣ አርአያ እና አባት ሁንኝ፡፡

አፍቃሪና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለመንፈሳዊና ለየእለቱ በጎነት በተለይ ደግሞ መልካም ሞት አገኝ ዘንድ በዚህች ሰዓት በልቤ ውስጥ ያለውን አሳብ አስፈላጊ የሆኑትን ጸጋዎች ከኢየሱስ መለኮታዊ ልብ ታሰጠኝ ዘንድ አማላጅነትህን እማጸንህለሁ፡፡

/እዚህ ላይ በልብ ያለውን አሳብ መጥቀስ/

ሥጋ የለብሰው ቃል ጠባቂ ስለእኔ የምታቀርበው ጸሎት በእግዚአበሔር ፊት እንደሚሰማ እተማመናለሁ፡ አሜን፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም እጮኛ፣ አፍቃሪና ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጥበቃህናን እርዳታህን የፈለገ፣ መጽናናትን ሳያገኘ የቀረ ማንም የለም፡፡ በቅዱስነትህ በመተማመን እነሆ ወደ ፊትህ እቀርባለሁ፡፡ የመድኃኒታችን ምድራዊ አባት ሆይ ልመናዬን በቸርነት ተቀበለኝ እንጂ ችላ አትበለኝ፡፡ አሜን፡፡

የቅዱስ ዮሴፍ መዝሙር

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጠብቀን

ወደ ገነትም አድርሰን፡፡

እጅግ ክቡር ዮሴፍ

ሲፈረድ በምድር ላይ

ለነፍሳችን እዘን

ተስፋ አድርገናል አንተን፡፡

8ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ በስቃይ ጊዜ ወዳጅ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለአዳኛችን እጅግ ቅርብ ስለነበርክ የስቃይ ድርሻ የበዛ ነበር፤  የኢየሱስ ሕይወት በስቃይ የተሞላ ነበርና ፡፡ በድህነትም በሄድክበት ሁሉ ልፋት ይከተልህ ነበር፡፡ ቅድስት ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በጸነሰች ጊዜ ሰው እንደመሆንህ የተሳሳተ አሳብ አእምሮ ገብቶ ንጽሕናዋን በመጠራጥጠር ተሰቃየህ፡፡ መልአኩ ሰለወደፊቱ የኢየሱስ ስቃይ የተሞላ ሕይወት ሲነግርህ በዚያም ተሰቃየህ፤ ስለ ሕጻን ኢየሱስ የወደፊት እጣ የስምዖንን ትንቢት ስትሰማ፣ ወደ ግብጽ እንድትሰደድ ሲነገርህ፣ ኢየሱስ ከአንተና ከቅድስት ማርያም ተለየቶ በኢየሩሳሌም ሲቀር፣... ለአንተ አሳዛኝና አስጨናቂ ጊዜያት ነበሩ፡፡ በተጨማሪም የዚያን ጊዜ የሕዝቡን ኃጢአት ማየት ለአንተ እጅግ ከባድ ሐዘን ነበር፡፡

እነዚህን ሁሉ ስቃዮች ልክ እንደ ክርስቶስ ስለታገስካቸው ለኛ ትልቅ አርአያ ነህ፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ምንም ዓይነት ስሞታ፣ ብስጭት፣ ትእግስት የማጣት ስሜቶችን አላንጸባረቅህም፡፡ በእርግጥ አንተ ታጋሹ፣ ዝምተኛው ቅዱስ ነህ! ሁሉንም በእምነት፣ በትእግስት፣ በትሕትና፣ በመታመንና በፍቅር መንፈስ ከኢየሱስና ከእናቱ ጋር በመሆን ተቀብልክ፡፡ ምክንያቱም የአንተ ተልዕኮ እውነትኛ የፍቅር መሥዋዕትነትን እንዲሚጠይቅ ተገልጾልህ ነበር፡፡ የምትተማመንበትም እግዚአብሔር አምላክህ በመከራህ ጊዜ አልተወኽም፡፡

በመጨረሻም ሐዘንህን በደስታ መከራህን በእፎይታ ለወጠው፡፡ እግዚአብሔር  ሕይወትህን ለተቀደሰ ዓላማ መከራና መጽናናት፣ ሐዘንና ደስታ የተፈራረቀበት አደረገው፡፡  ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ሕይወት ውጣ ውረድ ያካተተች መሆኗን ተረድተን ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር  እንድናመሰግን፣ የሰጠንን ሁሉ በደስታ እንድንቀበልና መስቀላችንን በፀጋ እንድንሸከም ለኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው፡፡  

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በእርግጥ አንተ በሕይወት ዘመንህ ብዙ መሥዋዕትነት የከፍልክ ሰማዕት ነህ፡፡ የሚጠበቅብህን ግዳጅ በሚገባ ስለተወጣህ የሚገባህን ክብር ተጎናጸፍክ፡፡ እንደ ቅድስት ማርያም ልቧን የሐዘን ሠይፍ እየወጋው ስቃይዋን ችላ ኖራ በሰማይ ቤት የመላእክትና የቅዱሳን ንግስት እንደሆንች ሁሉ አንተም የደረስብህን ስቃይ በትእግስት ተቋቁምህ በማለፍህ በመንግሥቱ እጅግ የከበረ ቦታ አገኘህ፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ስለ ኢየሱስ እና ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ያጋጥመህን ስቃይ በመቋቋምሀ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ ስለ ህጻን ኢየሱስ እና የሐዘን እናት ስለሆንችው ቅድስት ማርያም ስንል መከራዎችንና ስቃዮችን እንድንችል ፀጋ አሰጠን፡፡ በሕይወት ዘመናችን የሚያጋጥሙንን ሁሉ በፀጋ ተቀብለን፣ ተቋቁምንና የሚያስፈልገወን መሥዋዕት ከፈለን ለቤቱ የተገባን እንደንሆን አግዘን፡፡

የአጋንንት አስደንጋጭ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ - ለምንልን፡፡

(በየዕለቱ የሚደገም)

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እኔ ደካማው ልጅህ ሰላም እልሃለሁ፡፡ አንተ የሚወዱህንና የሚያክብሩህን ትከላከላለህ፤ ታማልዳቸዋልህ፡፡ በአንተ ላይ ልዩ የሆነ መታመን እንዳለኝና ከአዳኜ ኢየሱስና ከቅድስት እናቱ በመቀጠል የደኅንነት ተስፋዬ አንተ ነህ፡፡ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር ወዳጆችን ለመርዳት ከቶ አታመነታም፡፡ ስለዚህም በትህትና ስምህን እጥራለሁ፡፡ ከምወዳቸው እና የቅድስት ቤተስብ አፍቃሪ ከሆኑት ጋር አማላጅነትህን በመተማመን ወደ አንተ እንቀርባለን፡፡ ለአዳኛችን ኢየሱስና ለወላዲተ አምላክ ባለህ ፍቅር በዚህች አለም እስካለንና በሞታችን ጊዜ እንዳትለየን እንለምንሃለን፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም እጮኛ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ንጹሕ፣ ትሑት፣ በቸርነት የተሞላ አዕምሮና ፍጹም ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛት ጸጋ አሰጠኝ፡፡ አንተ በኢየሱስና በድንግል ማርያም እጅ እንደትክ እኔም ተመሳሳይ ዕድል ያጋጥመኝ ዘንድ መሪ፣ አርአያ እና አባት ሁንኝ፡፡

አፍቃሪና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለመንፈሳዊና ለየእለቱ በጎነት በተለይ ደግሞ መልካም ሞት አገኝ ዘንድ በዚህች ሰዓት በልቤ ውስጥ ያለውን አሳብ አስፈላጊ የሆኑትን ጸጋዎች ከኢየሱስ መለኮታዊ ልብ ታሰጠኝ ዘንድ አማላጅነትህን እማጸንህለሁ፡፡

/እዚህ ላይ በልብ ያለውን አሳብ መጥቀስ/

ሥጋ የለብሰው ቃል ጠባቂ ስለእኔ የምታቀርበው ጸሎት በእግዚአበሔር ፊት እንደሚሰማ እተማመናለሁ፡ አሜን፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም እጮኛ፣ አፍቃሪና ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጥበቃህናን እርዳታህን የፈለገ፣ መጽናናትን ሳያገኘ የቀረ ማንም የለም፡፡ በቅዱስነትህ በመተማመን እነሆ ወደ ፊትህ እቀርባለሁ፡፡ የመድኃኒታችን ምድራዊ አባት ሆይ ልመናዬን በቸርነት ተቀበለኝ እንጂ ችላ አትበለኝ፡፡ አሜን፡፡

የቅዱስ ዮሴፍ መዝሙር

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጠብቀን

ወደ ገነትም አድርሰን፡፡

እጅግ ክቡር ዮሴፍ

ሲፈረድ በምድር ላይ

ለነፍሳችን እዘን

ተስፋ አድርገናል አንተን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት