Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የዘጠኝ ቀን ዝግጅት (ቅዱስ ዮሴፍ) ቀን 9

St Joseph Novena 2013 9

9ኛ ቀን - ቅዱስ ዮሴፍ ፡ የመልካም ሞት ባልደረባ

ጸሎተ ተሰዓት (ኖቬና) ዘቅዱስ ዮሴፍ

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ከዚህ ዓለም በተለየህ ጊዜ የምትወዳቸው እና የሚወዱህ ኢየሱስና ማርያም ከጎንህ መገኘታቸው ተገቢና ትክክል ነው፡፡ ሙሉ ሕይወትህን ለኢየሱስና ማርያም መሥዋዕት አድርገህ አቀረብክ፡፡ በመጨረሻም አፍቃሪ ክንዳቸውን ተንተርሰህ የቅዱሳንን ሞት አገኘህ፡፡ ሞትን ፍቅር በተሞላበት መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ብለህ በደስታ ተቀበልክ፡፡ የተቀበልከውም ፍርድ ቅንና ርኅራኄ የተሞላው ነበር፤ ፈራጅ ልጅህ ሲሆን እጮኛህ ማርያም ጠበቃህ ነበረች፡፡ አንተ የዘለዓለማዊ ሕይወትን ለመወረስ በትእግስትና በመተማመን ዘመንህን ሙሉ ጠበቅክ፡፡

አዳኛችን ኢየሱስ ለጥቂት ጊዜ ያገኛቸውን እረኞችን፣ ሰብዓ ሰገልን፣ መጥምቁ ዮሐንስንና ሌሎችን የተባረከ ሕይወት የሰጠ አንተ ከመጸነሱ አንስቶ ለረጅም ጊዜ ብዙ መሥዋዕትነት ለከፈልከው የተትረፈረፈ ጸጋውን አፈሰሰብህ፡፡ አንድ ብርጭቆ ወኃ በስሙ የሚለግሱትን የሚባርክ ከሆነ ሕይወት ዘመንህን ለእርሱ የሰጠህ ብዙ በረከትን ማግኘትህ አያጠያይቅም፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እግዚአብሔር እራሱን የአንተ ባለዕዳ አደረገ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በምድራዊ ኑሮህ ይህንን ዕዳ ብዙ ፀጋን በመስጠት በተለይም ከስጦታዎች ሁሉ በላይ ፍጹም በሆነው በፍቅር ሕይወትህን እንድትመራ በማድረግ ከፈለክ፡፡ ሕይወትህ ለሰዎች ፍቅር በመስጠት የተሞላ ነበር፡፡ ነፍስህም በዚህ ፍቅር ክንፍ ወደ ፈጣሪዋ በደስታ ተመለሰች፡፡

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ በኢየሱስ እና ቅድስት ድንግል ማርያም እጆች ለመሞት እድል ስላጋጠመህ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ እኛም መልካም ሞት ፀጋ አሰጠን፡፡ በሕይወት ዘመናችን በእያንዳንዱ እለት ሞትን ለመቀበል ዝግጁ እንድንሆን አማልደን፡፡ እኛም እንደ አንተ በኢየሱስ እና ማርያም እጆች የመሞትን ፀጋ አሰጠን፡፡ አሜን፡፡

በመሞት ላይ ላሉ ጠበቃ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ - ለምንልን፡፡

(በየዕለቱ የሚደገም)

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ እኔ ደካማው ልጅህ ሰላም እልሃለሁ፡፡ አንተ የሚወዱህንና የሚያክብሩህን ትከላከላለህ፤ ታማልዳቸዋልህ፡፡ በአንተ ላይ ልዩ የሆነ መታመን እንዳለኝና ከአዳኜ ኢየሱስና ከቅድስት እናቱ በመቀጠል የደኅንነት ተስፋዬ አንተ ነህ፡፡ ምክንያቱም አንተ የእግዚአብሔር ወዳጆችን ለመርዳት ከቶ አታመነታም፡፡ ስለዚህም በትህትና ስምህን እጥራለሁ፡፡

ከምወዳቸው እና የቅድስት ቤተስብ አፍቃሪ ከሆኑት ጋር አማላጅነትህን በመተማመን ወደ አንተ እንቀርባለን፡፡ ለአዳኛችን ኢየሱስና ለወላዲተ አምላክ ባለህ ፍቅር በዚህች ዓለም እስካለንና በሞታችን ጊዜ እንዳትለየን እንለምንሃለን፡፡

የእመቤታችን ቅድስት ደንግል ማርያም እጮኛ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ንጹሕ፣ ትሑት፣ በቸርነት የተሞላ አዕምሮና ፍጹም ለእግዚአብሔር ፈቃድ የመገዛት ጸጋ አሰጠኝ፡፡ አንተ በኢየሱስና በድንግል ማርያም እጅ እንደሞትክ እኔም ተመሳሳይ ዕድል ያጋጥመኝ ዘንድ መሪ፣ አርአያ እና አባት ሁንኝ፡፡

አፍቃሪና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ለመንፈሳዊና ለየእለቱ በጎነት በተለይ ደግሞ መልካም ሞት አገኝ ዘንድ በዚህች ሰዓት በልቤ ውስጥ ያለውን አሳብ አስፈላጊ የሆኑትን ጸጋዎች ከኢየሱስ መለኮታዊ ልብ ታሰጠኝ ዘንድ አማላጅነትህን እማጸንህለሁ፡፡

/እዚህ ላይ በልብ ያለውን አሳብ መጥቀስ/

ሥጋ የለብሰው ቃል ጠባቂ ስለእኔ የምታቀርበው ጸሎት በእግዚአበሔር ፊት እንደሚሰማ እተማመናለሁ፡ አሜን፡፡

የቅድስት ድንግል ማርያም እጮኛ፣ አፍቃሪና ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጥበቃህናን እርዳታህን የፈለገ፣ መጽናናትን ሳያገኘ የቀረ ማንም የለም፡፡ በቅዱስነትህ በመተማመን እነሆ ወደ ፊትህ እቀርባለሁ፡፡ የመድኃኒታችን ምድራዊ አባት ሆይ ልመናዬን በቸርነት ተቀበለኝ እንጂ ችላ አትበለኝ፡፡ አሜን፡፡

የቅዱስ ዮሴፍ መዝሙር

ቅዱስ ዮሴፍ ሆይ ጠብቀን

ወደ ገነትም አድርሰን፡፡

ስለደረሰ ዕድሜህ

የአዳም ሞት መጣብህ

ቡራኬን ከልጅህ

ተቀብለህ ሞትህ፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት