ቅዱስ አውጎስጢኖስቅ. አውጎስጢኖስ ክክርስትና ደማቅ ከዋክብት አንዱ ነው። አፍሪካ ለዓለም ካበረከተቻቸው ድንቅዬ ልጆቿ ተጠቃሽ ሲሆን የዕድሜውን ማለትም ከኖራቸው 75 ዓመታት ውስጥ አራቱን ዓመታት ብቻ ነበር ከአፍሪካ አህጉር ውጭ ያሳለፈው።

በምዕራቡ ዓለም በፍልስፍናው ዘርፍ በተለይም የፕሌቶን ሃሳብ ከክርስትና እይታ ጋር በማተሳሰሩ በኩልና የራሱም አዳዲስ እይታዎችን በሚመለከት ሰፊ አበርክቶ ያለው ፈላስፋ፣ በነገረ መለኮት ረገድም የተከበረና ለዘመናት የዘለቀ አዎንታዊ ጫናን የፈጠረ ነገረ መለኮታዊ ሲሆን በክርስትና እምነት አናኗሩም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ታላቅ ተብለው ከሚታወቁት ቅዱሳኖች አንዱ ነው።

ቅ. አውጎስጢኖስ ከልጅነቱ ጀምሮ መንፈሳዊ ፍላጎቱን የሚያረካ እውነትን ሐቅንና የሕይወት መመሪያን ለማግኘት በልዩ ልዩ የፍልስፍና ማዕበል ውስጥ ገብቶ ጭንቀትን ያተረፈ፤ በሕይወቱ እጅግ የበዛ ውጣ ውረድ የገጠመውና በመጨረሻም የክርስትና እምነትን በመቀበሉ ታላቅ የሕይወት ለውጥን ያሳየ የነፍስ ሰላም፣ የኅሊና እርጋታና የአእምሮ ብርሃን ያገኘ ሰው ነው። በዚህም ሁኔታ የሕይወት ትግል ሁሉ መፍትሔ ክርስትና መሆኑን አስመሰከረ።

የቅዱሳን ሕይወት የክርስቲያን አናኗር መመሪያ ነውና ዛሬም ቢሆን በማንነቱ እውነተኛ እፎይታን ለሚመኝ ሰው በተለይም የዘመኑ ወጣት እውነተኛ የማይለወጥ ማረፊያ ፍለጋ ላይ ስለሚገኝ የዚህ ቅዱስ ታሪክ መመሪያና መነቃቂያ ሊሆነው ይችላልና ክርስቲያን ከመሆኑ በፊትም ሆነ በኋላ፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለነፍሳት ደኅንነት፣ ለእግዚአብሔርም ክብር ያበረከተውን አገልግሎትና ያሳለፈውን ቅዱስ ሕይወትን በጣም አጠር ባሉ ተከታታይ ክፍሎች ልናቀርብላችሁ እንወዳለን።

(ከቪዴዮው በታች ያሉትን ርእሶች በመጫን ተከፋፍሎ የተቀመጠውን የቅዱሱን ታሪክ በሙሉ ማንበብ ይችላሉ)

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።