እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ክፍል 3 - አውጎስጢኖስ የማኒ ትምህርትን ስለመቀበሉ

አውጎስጢኖስ የማኒ ትምህርትን ስለመቀበሉ

ማኒኬይዝም በሚል ስም የሚጠራ እምነትን የጀመረው ማኒ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ልጅ ሲሆን ትምህርቱም ከክርስትና፣ ግኖስቲሲዝም፣ ዞሮስትሪያኒዝም፣ እና ከግሪክ አረመኔያዊ እምነቶች የተለያየ ሃሳብን በመቃረም የተደራጀ ነው። ማይኒዝም ዓለም ሁለት ጽንፍ ባሕርይ አላት በሚል መሠረተ ሃሳብ ላይ የቆመ እምነት ነው፤ ይህም ማለት ብርሃንና ጨለማ፣  በጎና ክፉ፣ ሥጋና መንፈስ...ወዘተ የመሳሰሉ ባህርይ አሏት ማለት ነው። በዚህ መሠረት አምልኮም በሁለት አማልክት ማለትም አንዱ የበጎ ምንጭ ሌላው ደግሞ የክፋት ምንጭ ተብሎ ይመደባል። እንደ ማኒ አስተሳሰብ ማንኛውም ሥጋ ለባሽ ክፉ ነው የሚመነጨውም ከሰይጣን ነው፤ ስለዚህ ሰው ከማናቸውም ክፉ ነገር እንዲጠበቅ ከግብረ ሥጋ (ወሲብ) መራቅ፣ ከሥጋ ተድላና ለግዙፍ አካል ከሚጠቅም የምግብ ዓይነት መከልከል አለበት። ይህም ግዙፍ ፍጥረትንና ሥጋን ከተቢ ግምቱ ዝቅ አድርጎ ማየት የጥንት ምሥራቃውያን ሃይማኖቶች የጋራ ዝንባሌ ነው።

የማኒ ደጋፊዎች አንድ የጸና አቋምና ራሱን የቻለ ሃይማኖታዊ ሥርዓት አልነበራቸውም፤ እምነታቸውና ትምህርታቸው በሌላ ሃይማኖት ውስጥ በተለይም በክርስትና ውስጥ ሠርጎ በመግባት የሚበክልና የሚስፋፋ ነበር። በፋርስ (ኢራን) አካባቢ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በሰሜን አፍሪካ፣ በኤውሮጳም ሳይቀር ሲዛመት በካርታጅ (የሰሜን አፍሪካ ክፍል) የገባውም አውጎስጢኖስ እዚያ ሳለ በመሆኑ እርሱም ይህን እምነት በመከተልና በመደገፍ ዘጠኝ ዓመታት ኖረ። ብዙዎች እንደሚሉት አውጎስጢኖስ ይህን እምነት የተቀበለው ሥጋዊ ደካማነቱን ለማሸነፍ የነበረውን ምኞትና ፍላጎት መሠረት በማድረግ ነው። ምክንያቱም ማኒይዝም ግዙፍና ሥጋዊ ነገርን ለማዳከም ይበጃል ተብሎ የተነሣሳ ንቅናቄ ነበርና ነው።

አውጎስጢኖስ ራሱን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጓደኞቹንና ወዳጆቹን ከሌሎች የማኒ ተከታዮች ጋር ሆኖ ወደ ማኒኬይዝም ለመሳብ ብዙ ጥረት አደረገ፤ ምንም እንኳ ማኒኬይዝምን ለማስፋፋት በብርቱ ቢተጋም ይህ እምነት እንደ እርም በመቁጠር የሚያስተምረው ነገር ሁሉ መሠረት የሌለውና እውነተኝነትን ያልተከተለ በመሆኑ አውጎስጢኖስም ሥጋዊ ዝንባሌ ያጠቃው ስለነበረ በማኒኬይዝም ወደሚፈልገው ከፍተኛ ደረጃ ብቃት መድረስ ፈጽሞ አልሆነለትም። ከብዙ ጊዜ በኋላም የማኒ ትምህርት ያበረከተለት የፍልስፍና ሕይወት ዋጋ የሌለው ሆኖ አገኘው። በዚህም ምክንያት ጥርጣሬ ስለገባው ወደ ከፍተኛ የብቃት ደረጃ ደርሰዋል የሚባሉ የማኒ ተከታዮች ነገርን እንዲያብራሩለት ቢጠይቃቸው "ጳጳሳችን ፋውስቶስ መጥቶ ሁሉንም ነገር እስኪያብራራልህ{jcomments on}ና እስኪያስረዳህ ድረስ ታገሥ" በማለት መከሩት።

ጊዜያት ካለፉ በኋላ ፋውስቶስ አውጎስጢኖስ ወደ ነበረበት መጥቶ ስለማኒ ትምህርት ሰበከ። አውጎስጢኖስም የፋውስጦስን ንግግር ከሰማ በኋላ በአንጋገሩ፣ በቃል አመጣጠን ችሎታውም አደነቀው፤ አመሰገነውም። ነገር ግን እንዳሰበውና እንደጠበቀው የነበረውን የእውነትና የአእምሮ ጥም የሚያረካለት ሆኖ አላገኘውም። በዚህ ምክንያትም አውጎስጢኖስ "በውጭው ያጌጠና ያሸበርቀ ጽዋን አቀረበልኝ፤ በውስጡ ግን የነበረኝን ጥም የሚያረካ ምንም አላገኘሁም" በማለት ስለ ፋውስቶስ ትምህርት የነበርውን አስተያየት ገልጿል።

Monica's Dream
የቅድስት ሞኒካ ሕልም ስለልጇ።

አውጎስጢኖስ የማኒን እምነት በተቀበለበት ጊዜ እናቱ ሞኒካ አንድ ሕልም አየች፤ ባንድ ከፍተኛ ሥፍራ ላይ ሆና በልጅዋ ምክንያት ስታዝንና ስተንክዝ ሳልች የከበረ ልብስን የለብሰ ወጣት ታያትና ስለምን እንደምታዝን ይጠይቃታል፤ እርሷም የልጅዋ ሁኔታ እንደሚያሳዝናት ትገጽለታለች። ወጣቱም "አይዞሽ! እስቲ መለስ ብለሽ ተመልከች፤ አንቺ ባለሽበት እሱም መቆሙን ታያለሽ" አላት። መለስ ብላ ባየችም ጊዜ በርግጥ አውጎስጢኖስ ከጎኗ ቆሞ አየችው። ሞኒካ ይህን ሕልም ለልጇ አውጎስጢኖስ ነገረችው፤ እሱ ግን "አንቺ ወደ እኔ፤ እኔም ወዳለሁበት ትመጭ እንደሆነ እንጂ እኔ ወዳንቺ አልመጠጣም" የሚል ድርቅ ያለ መልስ ሰጣት። እርስዋም "ልጄ ሆይ! ለእኔ የተነገረኝ እርሱ ባለበት ልትቆሚ ነው የሚል ሳይሆን አንቺ ባለሽበት ቆሟል የሚል ነው" አለችው። አውጎስጢኖስ ከእናቱ ፈቃድና ፍላጎት ወጥቶ በመባዘን ይቅበዘበዝ በነበረበት ጊዜ ሁሉ እናቱ ሞኒካ ይህን ሕልም ዘወትር በልቧ ታስታውሰውና ተስፋ ታደርገውም ነበር።

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት