የሃንጋሪዋ ቅድስት ኤልሣቤጥ

የሃንጋሪዋ ቅድስት ኤልሣቤጥ

የሃንጋሪዋ ቅድስት ኤልሣቤጥኤልሣቤጥ እ.ኤአ. 1207 ዓ.ም. የተወለደች የሃንጋሪው ንጉሥ አንድርያስ ልጅ ናት፡፡ ገና በወጣትነቷ የቱሪንግያውን ባላባት ሎድዊግን አግብታ ሦስት ልጆች ወለደች፡፡ በጸሎት ትተጋ ነበረ፣ ባሏ ከሞተባት በኋላም ሃብቷን ሁሉ ትታ ለበሽተኞች ባሠራቸው ሆስፒታል ውስጥ እነሱን መንከባከብ ጀመረች፡፡ ... 1231 ዓ.ም. ማልበርግ ውስጥ አረፈች፡፡

የቅድስት ኤልሳቤጥ ነፍስ አባት ከነበረው ከማርበርጉ ኮንራድ ደብዳቤ የተወሰደ ንባብ

ኤልሣቤጥ ክርስቶስን በድሆች ውስጥ አየች፣ ወደደቻቸውም”

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኤልሣቤጥ ቅድስና ሙሉ እየሆነ ሄደ፡፡ ሕይወቷን በሙሉ የድሆች መጽናኛ ነበረች፤ አሁን የረሃብተኞች ረዳት ሆነች፡፡ ከታላላቅ የግንብ ቤቶቿ ከአንድ ደጃፍ የእንግዳ ማረፊያ አሠርታ በልዩ ልዩ በሽታዎች ይሰቃዩ የነበሩትን ወንዶችና ሴቶች በዚያ አሳረፈች፡፡ ወደዚህም ቦታ ሌላ ምጽዋት ለመቀበል የመጣ ማንም ሰው ከርስዋ ያልተቆጠበ እርዳታ ያገኝ ነበር፡፡ የባልዋ ግዛት በሆነው ሁሉ ያላትን ንብረት ሁሉ በመጠቀም፣ በመጨረሻም ጌጦቿንና ልብሶቿንም ሁሉ እየሸጠች በርሱ ግዛት ውስጥ ላሉት ሁሉ ትረዳ ነበር፡፡

በሽተኞቹን በቀን ሁለት ጊዜ፣ ጠዋት በማለዳና  ፀሐይ ሳትጠልቅ ሄዳ ትጐበኛቸው ነበር፣ ከነዚህም በሽተኞች ውስጥ ስቃይ የሚበዛባቸውን ራሷ ትንከባከባቸው ነበር፡፡ እርሷ ታበላቸው፣ አልጋቸውን ትጠርግ፣ ትሸከማቸውና በፈለጉት መንገድ ትንከባከባቸው ነበር፡፡ ባልዋም መልካም ሰው ስለ ነበር በምታደርገው ሁሉ ይስማማ ነበር፡፡ እርሱ ሲሞት ፍጽምናን ለማግኘት መጣጣር አለብኝ ብላ አሰበች፡፡ ወደኔም መጥታ ከቤት ወደ ቤት እየዞረች ለመለመን እንድፈቅድላት እያለቀሰች ለመነችኝ፡፡ በዚያ ዓመት ዓርብ ስቅለት፣ የቤተ-ክርስቲያን አልባሳትና ጌጦች ከተነሡ በኋላ በቤተ-ክርስቲያኑ መሰዊያ ፊት ለፊት ተንበርክካ እጆቿን አሳረፈች፡፡ ከዚያም የቤተ-ክርስቲያኑ ካህናት በተሰበሰቡበት ምድራዊ ሃብቷንና መድኃኒታችን በወንጌል ውስጥ እንድንሰጥ የሚመክረንን ሁሉ በፈቃዷ ተወች፡፡

 

ይህን መሃላ ከፈጸመች በኋላ እንኳን ባሏ በሕይወት ዘመኑ ከነበረበት ጊዜ ትኖርበት በነበረው ሁኔታና በአስተዳደር ሥራዎች ውስጥ እንዳለች ተረዳች፡፡ ከዚያም ያለኔ ፈቃድ ወደ ማርበርግ ተከትላኝ በመምጣት በከተማው ውስጥ የድኩማን ማረፊያ በመሥራት በሽተኞችንና አካል ጉዳተኞችን በዚያ ሰበሰበች፣ ከዝቅተኞቹና ከምስኪኖቹም ጋር በአንድ ማዕድ ቀረበች፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ ውጫዊ ተግባሯ ነበር፡፡ ይህን ከእግዚአብሔር ፊት እናገራለሁ፤ ከዚህች የበለጠ ስለ እግዚአብሔር የምታስብ ሴት አይቼ አላውቅም፡፡ የግል ጸሎቷን ለማድረግ ስትመጣ አንዳንድ ቄሶችና ደናግል ብዙ ጊዜ ያይዋት ነበር፣ ፊቷ ወደ ብርሃን ተለውጦ  ፀሐይም ከዓይኖኟ የምታበራ ይመስል ነበር፡፡ ከመሞቷ በፊት ኑዛዜዋን ሰማሁ፡፡ ሃብቷንና ልብሶቿን ምን እንደሚሆኑ ስጠይቅ የቀራት ማንኛውም ነገር የድሆች እንደሆነ ገልጻ ለብሳው ለመቀበር  ሰበችው አሮጌ ቀሚስ በስተቀር ሁሉንም ለድሆች እንዳከፋፍል ነገረችኝ፡፡ ከዚያም ቅዱስ ቁርባንን ተቀበለች፡፡ ከዚህ በኋላ የምሽት ጸሎት ሰዓት እስኪደርስ ድረስ በስብከት ስለሰማቻቸው ቅዱሳን ነገሮች ተናገረች፡፡ ይህን ስትጨርስ በአጠገቧ ለሚገኙት ሁሉ ከጸለየች በኋላ እንቅልፍ ያሸለባት መስላ አረፈች፡፡ በዓሏም ኅዳር 8 ቀን ይከበራል።

የሃንጋሪዋ ቅድስት ኤልሣቤጥ