ብፅዕት ኤሚሊ ታቨርጊየር (ኤሚሊ ጋሜልን 1800-1891)

Written by Super User on . Posted in አጫጭር ገድለ ቅዱሳን

ብፅዕት ኤሚሊ ታቨርጊየር (ኤሚሊ ጋሜልን 1800-1891)

ኤሚሌ በየካቲት 9 ቀን 1800 ዓ. ም. ከአባቷ አንቶን ታቨኒየር እና ከእናቷ ማርያ ጆሴፍ ማውራ ካፈሯቸው አስራ አምስት ልጆች የመጨረሻዋ ሆና ተወለደች፡፡ ኤሚሊ ገና በአራት ዓመቷ ሁለቱም ወላጆቿ ስላረፉ ቤተሰቧ በከባድ የሃዘን ድባባ ተዋጠ፡፡ በዚህ ሳቢያ ኤሚሊ ከአክስቷ ጋር መኖር ጀመረች የኤሜሊ አክስት በቅዱስ ዮሐንስ አውራ ጐዳና ላይ ወደ ሚገኘው የኖተርዳም የሴት መነኮሳን ገዳም በወቅቱ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት ለመከታተል ትችል ዘንድ ኤሚሊን ላከቻት፡፡ ይህ ገዳም ኪውቤክ በተባለ ቦት በቅድስት ማርጋሪት ቡድጅስ (1620-1700) የተመሠረተ ሲሆን በሞንትሪያል በሚገኘው ትምህርት ቤት ደግሞ የመጀመሪያው ለዓለማውያን ግልጋሎት የሚሰጥ ተቋም መሆኑ ነው፡፡

ወጣቷ ኤሚሊ ከመጀመሪያው ጀምሮ ድሆችን እና አቅመ ደካሞችን ለመርዳት ጥልቅ ፍላጐት ነበራት፣ ሆኖም ግን ዕድሜዋ 18 ዓመት ሲሞላት የወንድሟ ባለቤት ስላረፈች ብቻውን የቀረውን ወንድሟን ለመርዳት ወደእርሱ ሄደች፡፡ በወንድሟ ቤት እያለች በድሆችና በአቅመ ደካሞች ከገበታዋ የምትችለውን ሁሉ ለመካፈል ወደበር ለተጠጉት ሁሉ እርዳታዋን ማበርከትዋን ቀጠለች፡፡ በእንዲህ አይነት ሁኔታ እያለች ለድሆችና ለአቅመ ደካሞች የእርሷን አይነት ፍላጐት ካለው ዮሐንስ ፓጋሜሊን ከተባለ ወጣት ጋር ጋብቻዋን ፈጸመች፡፡ ይህ ወጣት ባለጸጋ እና የእርሻ ባለቤት ነበር ኤሚሊ አሁንም በየሄደችበት ከሚከተላት ሃዘን አልዳነችም፡ ከዮሐንስ ጋር ካፈረቻቸው ልጆች ያለጊዜያቸው በመወለዳቸው አንድ እንኳን የተረፈላት አልነበርም፤ ከሦስት ልጆቿ ሃዘን በወጉ ሳታገግም ከልጆቿ ሞት አራት ዓመት በኋላ ባለቤቷ ዮሐንስ አረፈ፡፡

ኤሚሊ እንደርሱ ልጇን በስቃይ ጊዜ እናት ሆና ሃዘኑዋን ወደተጋራችው የሃዘንተኞች ሁሉ እናት ወደ ሆነችው ድንግል ማርያም የልብ ጸሎት በማድረግ እና እርሷን በማፍቀር የልብ ሠላምን መጽናናት አገኘች የግል መኖርያ ቤቷንም የድሆችና የአቅመ ደኮሞች ማረፊያ አደረገችው፣ በቤቷ ውስጥ መጠለያ አልባ ስደተኞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ አረጋውያን እናቶችን፣ የአዕምሮ ሕመምተኛ ሕፃናትን፣ ወላጅ  አልባ ልጆችን የጐዳና ተዳዳሪዎችን ለማስጠጋት  አዲስ ቤተሰብ ለመመሥረት ቻለች፡፡ ቤቷም "የመለኮታዊ ጥበቃ ቤት" ተብሎ ሲሠራ ኤሚሊ በሕይቷ የገጠሟትን ስቃዮች ሁሉ በአንድነት "የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰብአዊ ገጽታዎች" ስትል ሰየመቻቸው፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቤቱ በማይጠረጠር መልኩ ጠባብ ሆኖ በመገኘቱ ከባለቤቷ በወረሰችው ሀብት ተጠቅማ ተጨማሪ መቆያ ቦታዎችን አዘጋጀች፡፡ ኤሚሊ የቤተሰብ አባላቶቿን ወንድሞች እህቶቿን፣ አቻ ጓደኞቿን ጭምር  ወደዚህ የፍቅር ሥራ በመጋበዝ እንዲህ ባለ መልኩ ለተከታይ 15 ዓመታት የዓለማውያን በጐ ፈቃድ ማኀበርን መምራት ቻለች፡፡ ሥራዋን የተገነዘቡት የጊዜው የሞንትሪያል ጳጳስ ሞንሲኞር ኢግናንስ ቡርጌት ለዚህ በጐ ሥራ ተጨማሪ ዕርዳታ አስፈላጊ ነው በማለት በ1841 ዓ. ም. ፓሪስን ቢጐበኙ የቅዱስ ቪንሰንት ዴፖል እህት መነኮሳን እህቶችን ወደ ሞንትሪያል እንዲልኩ ጋበዟቸው፡፡ ጳጳሱ ወደ መንበራቸው በተመለሱ ጊዜ ለእህት መነኮሳት ማረፊና ቦታ በማዘጋጀት ሥራ ተጠመዱ ሆኖም ግን እህት መነኮሳት ወደ ሞንትሪያል ሳይመጡ ቀሩ ሞንሲኞር ኢግናንስ ቡርጌት በዚህ ክስተት ተስፋ ባለመቁረጥ የሰበካውን ቤተ ምዕመናን ወደ ሥራው ጋበዟቸው፤  የርሳቸውን ጥሪ ተከትሎ በርካታ በጐ ፈቃደኞች ኤሚሊን ለመርዳት መጡ፡፡ በ1843 ዓ. ም. የሴቶቹን ጥልቅ ፍላጐት በመረዳት የሰበካው ጳጳስ በአንድ ማኀበር ተዋቅረው እንዲኖሩ ወሰኑ፡፡ በዚህ መልኩ የመለኮታዊ ጥበቃ  ደናግል ማኀበር ሊመሠረት ቻለ፡፡

ኤሚሊ የመጀመርያዋ የመነኮሳያይት አለቃ ስትሆን በመጋቢት 29 ቀን 1844 ዓ. ም. የመጀመሪያዎቹ ሰአሊያን (postulant) ማሃላቸውን አደረጉ፡፡

እንደማንኛውም በፈጣን ዕድገት ውስጥ ያለች ከተማ ሞንትሪያልም በንጹህ የመጠጥ ውሃ እና የመጸዳጃ ቤት እጥረት በእጅጉ ተጠቃች፡፡ አብዛኞቹ ነዋሪዎቿ በኮሌራ እና ታይፈስ በሽታ ተጋለጡ፣ በዚህ ጊዜ እንደ ዕድል ሆኖ የእህት መነኮሳን ቁጥር ተበራክቶ ስለነበር ያሉትን በርካታ ሕመምተኞች በተገቢው ሁኔታ ለማስተናገድ ተቻለ፡፡ እንደ በርካታ ጀግኖች የሕይወት ውጣ ውረዶች ሁሉ ኤሚሊም በአሳዛኝ ሁናቴ አንዲት እህት መነኩሲት ፈተነቻት፡፡ መነኩሲቷ ሰዎች በኤሚሊ ላይ ከባድ ጥርጣሬ እንዲያሳድሩባት  ለማግባባት ሙከራ አደረገች፡፡ ኤሚሊ ይሕንን እውነታ ባወቀች ጊዜ የትዳር ጓደኛዋንና ሦስት ልጆችዋን ስታጣ የተሰማትን ዓይነት ሃዘን ልቧን አቆሰለው፡፡ ጳጳሱ በመነኩሲቷ ኤሚሊን በሚመለከት የቀረበላቸውን ውንጀላ መሠረተ ቢስነት በማረጋገጣቸው ሰዎች ስለ ኤሚሊ ያላቸውን አስተሳሰብ እንዲቀይሩ አስተዋፅዖ አድርገዋል፡፡ በ1851 ዓ. ም. ከተማዋ በከፍተኛ የኮሌራ ወረርሽኝ በተጠቃች ጊዜ በገዳሙ ውስጥ የነበሩት መነኮሳት በቁጥር 50 ያህል ይሆኑ ነበር፤ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት  ኤሚሊ በሽተኞችን ሁሉ በመርዳት ላይ ሳለች በበሽታው ክፉኛ  በመጐዳቷ ሳቢያ በመስከረም 23 ቀን  1891 ዓ. ም. አረፈች፡፡ የኤሚሊ ብፁዕና መታወጅ ከዘገየባቸው ምክንያቶች  አንዱ እርሷ የመለኮታዊ ጥበቃ ደናግል ማኀበር የመጀመሪያ አባል እንጂ መሥራች አለመኖኗ ነበር፤ እስከ 1993 ሂደቱ ተዳክሞ የቆየ ቢመስልም ብፁዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አጥቢያ ቤተክርስቲያናትን ለማጠናከር ባደረጉት ቅስቀሳ ወቅት የግለሠቦችን መልካም ክርስቲያናዊ የሕይወት ተሞክሮ ሲያስተዋውቁ የኤሚሊ መልካም ክርስቲያናዊ ትሩፋቶች ጐልተው ወጡ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንድ በከባድ የሕመም ስቃይ ይሰቃይ የነበረ የ13 ዓመት ታዳጊ ወጣት በእርሷ አማላጅነት ከስቃዩ እና ከበሽታው ሙሉ በሙሉ በመፈወሱ፣ ይህንንም ሃቅ ቤተክርስቲያን በማረጋገጧ በጥቅምት 7 ቀን 2001 ዓ. ም. በርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ዮሐን ጳውሎስ ዳግማዊ (ብፁዕ) ታወጀ፡፡

የማሰላሰያ ጥያቄዎች

1.  የሕይወትዎን መጥፎ ገጠመኞች ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ እንዴት ይጠቀሙባቸዋል?

2.  በውስጥዎ፣ በክርስቶስ አሳብና በራስዎ ፈቃድ መካከል ትግል አጋጥሞዎት ያውቃል? በዚህ ጊዜ ምን ያደርጋሉ?