የዘመናችን ተምሳሌያዊት ቅድስት

ለክርስቲያናዊ ቤተሰቦች ታላቅ ምሳሌ የምትሆን የዘመናችን ቅድስት

 

<a href="/images/stories/show/photo11.jpg" rel="lytebox" title="Sample photo 1">Click here for example</a>
<br/><br/>

ጃና በሬታ ትባላለች ቅድስት ባለትዳርና የሕክምና ዶክተር ናት፡፡ ጥቅምት 4 ቀን 1922 ዓ.ም. እ.ኤ.አ ሚላን ተብላ በምትጠራ የጣልያን ከተማ ተወለደች፡፡ addis catholic churchከአሥራ ሦስት ልጆችም አሥረኛዋ ነበረች፡፡ ከሕፃንነቷ ጀምሮም እስከ ወጣትነቷ እጅግ በጣም ጥሩ ከነበሩት ወላጆችዋ በሙሉ ፍላጎት ንፁሕ የሆነውን ክርስትያናዊ እምነት ተቀበለች፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ፤ በጸሎት አስፈላጊነት እና ውጤታማነት ላይ ጠንካራ እምነት ስለነበራት ውጤቱም ሕይወት የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታ መሆኑን እንድትገነዘብ አድርጓታል ፡፡

 

የሁለተኛ ደረጃ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችበት ጊዜ ራስዋን በትጋት ለጥናት ያዘጋጀች ነበረች፣ እንዲሁም በዚሁ ሁኔታ እያለች በርኅራኄ ሐዋርያዊ አገልግሎት በዕድሜ ከገፉ አረጋውያን እና በችግረኞች መሐል በመገኘት በቅዱስ ቪንስንት ዴ ፖል ማኅበር ታቅፋ እምነቷን ገልጻለች፡፡

በ1944 ዓ.ም በሕክምና እና በቀዶ ጥገና ከፓቪያ ዩንቨርሲቲ ዲግሪዋን ካገኘች በኋላ ሜሌሮ በሚባል ቦታ የራስዋን ክሊኒክ በ1950 ዓ.ም. ከፈተች፡፡ በሚላን ዩንቨርስቲም በ1952 የሕፃናት ሐኪም በመሆን ትምህርቷን በማጠናቀቅ ትኩረቷን ሁሉ ለሕፃናት፣ ለእናቶች፣ ለአረጋውያን እና ለድሆች በማድረግ አሳልፋለች፡፡ በአጠቃላይ በሕክምናው ዓለም ስትሠራ ሥራዋን እንደ ተልእኮ ትቆጥር ነበር፡፡ እንዲሁም ካቶሊካዊ ተግባር የሆነነውን የርኅራኄ አገልግሎቷን ጭምር ታከናውን ነበር ፡፡ በዚህም ሁኔታ እያለች ለተፈጥሮ ያላትን ፍቅር ትገልጽ ነበር። በተለይ በወጣቶች መከከል የተራራ ወጪነት ብቃቷን /ችሎታዋን/ አሳይታለች፡፡

በጸሎቷ እና በሌሎችም ነገሮች ጥሪዋን አንጸባርቃለች፡፡ ወጣቶች የእግዚአብሔር ስጦታ መሆናቸውንም ገልጻለች፡፡ የቃልኪዳን ጥሪ በመምረጥ ኃላፊነትን ተቀብላ በሙሉ ትጋት እና በፍጹም ሁለንተና ራሷን በመስጠት እውነተኛ ክርስቲያናዊ ቤተሰብ መሥርታለች››፡፡ ለጴጥሮስ ሞላ ከታጨች በኋላ በአንጸባራቂ ደስታ እና ደስተኛነት የእጮኛነት ጊዜያቸውን አሳልፈው ነበር፡፡ ለዚህም እግዚአብሔርን ታከብር እና ታመሰግን ነበር፡፡ መስከረም 24 ቀን 1995 ዓ.ም ማጀንታ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በሚገቃ ቅዱስ ማርቲን ቤተክርስቲያን ተጋቡ ፤ እናም ደስተኛ ሚስት ሆነች፡፡

በኅዳር 1956 ዓ.ም. የፔሪቡጂ ፣ በታህሳስ 1957 ዓ.ም. የማሪዮሊና፣ በሐምሌ 1959 ዓ.ም. የላውራ እናት መሆንዋ ትልቁ ደስታዋ ነበር፡፡ ቀለል ባለ መልኩ የዶክተርነት እና የሕይወት አፍቃሪነት ግዴታዎቿን አስማምታለች፡፡ የእናቶች እና የቤተሰቦች ጠባቂ/ባልደረባ ቅድስት ጃና በ1962 ዓ.ም በእናታዊ ፍቅር ሰማእትነት ሞታለች፡፡

በመስከረም 1961 ዓ.ም በሠላሳ ዘጠኝ ዓመቷ ቅድስት ጃና አራተኛ ልጅዋን አርግዛ ነበር፡፡ ሕክምና ምርመራ ከተደረገላት በኋላ የእንቁላል ተሸካሚው ከረጢት ፈሳሽ ነገር መያዙን እና ቀዶ ጥገባ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡ የቀዶጥገና ጠቢብ ጽንሱን በማስወረድ ሕይወቷን እንድታድን ነገራት፡፡ የሷ ውሳኔ ግን ፈጣን እና የማያወላውል ነበር ፡፡ ‹‹እኔ የምቀበለው በማንኛውም ሁኔታ እነሱ ልጁን ለማዳን የሚያስፈልገውን ሁሉ እንዲያደርጉ ነው›› የሚለውን ምርጫ ነው በማለት አቋሟን አሳወቀች፡፡ የሷ መጪው ሁኔታ የታወቀ ወይም የተወሰነ ነበር፡፡ በቀጣዩ ዓመት በዓርብ ስቅላት ጃን ሞንዛ ማተርኒ ሆስፒታል ገብታ ነበር፡፡ ልጅዋ ጃን አማኑኤል እናቷ ሆስፒታል በገባች በማግስቱ ተወለደች፤ የቅድስት ጃና ምድራዊ ጉዞ ግን ከሰባት ቀን በኋላ በሚያዚያ 28 ቀን 1962 ዓ.ም. አበቃ፡፡

የቅድስት ጃና ጸሎት

ኢየሱስ ሆይ አንተ በእኔ ላይ እንዲሆን የፈቀድከውን ሁሉ ለመቀበል ላንተ ቃል እገባለሁ፡፡ ፈቃድህን እንዳውቅ ብቻ አድርገኝ፡፡ ፍጹም ውድ ኢየሱስ፤ ምሕረትህ ወሰን የሌለው እግዚአብሔር ሆይ! በልዩ ሁኔታ ደግሞ በጣም ደካማ ለሆኑት ፤ በጣም ተስፋ ለቆረጡት፤ በጣም ላረጁት በተለየ መልኩ ርኀሩኅ የነፍሳት አባት አድርገህ ራስህን በመስጠት በመለኮታዊ እጆህ የምትጠብቅ፤ በቅዱስ ልብህ ፍቅር እና ደግነት ሁልጊዜ ቅዱስ ፈቃድህን የምፈጽምበትና የምገነዘብበትን፤ ባንተ በዘላለማዊነት ያለስጋት በአፍቃሪው እቅፍህ የማርፍበትን ጸጋ እለምንሀለሁ፡፡

 

የበሬታ ቤተሰብ የቅዱሳኖች ቤተሰብ

እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ-ጳጳሳት ዩሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የስድስት አዲዳስ ቅዱሳኖችን ቅድስና በይፋ አወጁ፡፡ ከነዚህ ውስጥም አባ ኦሪኔ እና ጃና በሬታ ሞላ ይገኙበታል፡፡ የመገናኛ ብዙኀኑን ቀልብ በተለየ መልኩ የሳበው ግን ከሎምባርዲያ ጣልያን የሆነችው የወጣቷ እናት እና ዶክተር የጃና በሬታ ቅድስና ነው፡፡ ጃና በ1962 ዓ.ም እ.ኤ.አ. በ39 ዓመት እድሜዋ ስትሞት ታሪክዋም እንዲህ ነው፡፡ በማሕፀንዋ ውስጥ የነበረችውን ሕፃን ለማትረፍ ነው ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ጉጉትም ይህ ነበር፦ 1500 ዓመት በላይ በሚቆጠረው በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ያላገባች ሴት ቅድስና ታወጆ ስለማያውቅ ጃና የመጀመሪያዋ ቅድስና ሴት መሆንዋን ለመግለጽ ነበር፡፡ በካቶሊክ ቅዱሳኖች ስም ዝርዝር ውስጥ አግብተው የነበሩ እና ለብዙ ጊዜ በመበለትነት ባሎቻቸው የሞቱ ወይም በምንኩስና በድንግልና ሕይወት የኖሩ ናቸው፡፡ ጃና ግን በኪዳናዊ ትዳር ሕይወት ላይ እንዳለች የሞተች እና ቅድስት ተባለች የሰለጠነው ዘመን ሰው ናት፡፡ በ1955 እ.ኤ.አ. ጃናን ያገባው ባለቤቷ ኢንጂነር ጴጥሮስ ሞላ ቅድስናዋ በታወጀበት ወቅት ተገኝቶ ነበር፡፡

ቅድስት ጃና በሬታየዚህች አዲስ ቅድስት ብዙም ያልተነገረና ያልተፃፈ ሁኔታ ቢኖር የቤተሰቧ ሁኔታ ነው፡፡ ጃና በሬታ መንፈሳዊ ትምህርቷን ገዳም ውስጥ፣ መንፈሳዊ ተቋም ውስጥ ወይም ካቶሊካዊ ማኅበራት ውስጥ አላገኘችውም ይህን የእምነት አብነት ያገኘችው ከቤተሰብ ነው፡፡ የእርሷ ቅድስና ስምምነት ያለበት፣ እምነታቸውን በሕይወት የሚተረጉሙ የመልካም ቤተሰብ ውጤት ነው፡፡ ይህ ከማንኛውም በላይ አስፈላጊው እና ጠቃሞው ነጥብ ነው፡፡

በዛሬው ዘመን ቤተሰቦች በተቃወሰ ሁኔታ በመጓዝ ላይ ናቸው፡፡ የዚህም መዘዝ ሕብረተሰብ፣ ግለሰብ እና ሰብአዊነት በአስጊ ወይም በደፈረሰ ሁኔታ ላይ ይገኛል ፡፡ ቤተሰብም ያካተተው ይህ አስጊ ሁኔታ ከምንገምተው በላይ ከፍተኛ ጥፋት እያስከተለ ነው ፡፡ ከሃምሳ እና ከመቶ ዓመታት በኋላም የሚያስከትለውን ጥፋት ወይም መዘዝ ልንናገር ወይም ልንገልጽ አንችልም፡፡ የጃና በሬታ ቤተሰቦች፤ ተራ ቤተሰብ በወላጆቻቸው ጽኑ እና መሠረታዊ የእምነት ኑሮ የሚመሩ ነበሩ፡፡

ሁለቱም ወላጆቻቸው እንደ ሕበረተሰብ እና እንደ እግዚአብሔር ልጆች ክብራቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ነበሩ፡፡ እነዚህ እንዱ የአንዱ ጥገና የመሆ ሁኔታዎች የአንዱ እውነት እንደመሆናቸው መጠን አንድ ከአንዱ ጋር ይዛመዳል፡፡ ይህ ሁኔታ ሃይማኖትን እንደ አንድ የሕይወት ፍልስፍና ምርጫ አድርጎ ለሚገነዘበው ለዘመናችን ባህል አስቸጋሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በእነዚህ እሴቶች ለማመን የቻሉና መልካም ሁኔታዎችም ከተመቻቸላቸው ቤተሰቦች ውስጥ ጃና ያደረገችበት እና የተማረችበት ቤተሰብ አንዱ ነው፡፡ ሁለቱ የጃና ወንድሞች እና እህቶች በሕይወት አሉ ፤ሁለቱንም አረጋግተናቸዋል፡፡

የቅድስት ጃና ወላጆች ማሪያ እና አልቤርቶ ተብለው ይጠራሉ፡፡ ወ/ሮ ማሪያ የቤት እመቤት ሲሆኑ አቶ አልቤርቶም የቢሮ ሠራተኛ ነበሩ፡፡ አስቀድሞ እንዳልነው ሁለቱም በጣም ጥሩ ክርስቲያኖች እና እምነታቸውንም በከፍተኛ ጽሞና እና ቅንነት ይኖሩበት ነበር፡፡ አሥራ ሦስት ልጆች ነበሯቸው፡፡ አምስቱ ልጆች በወጣትነት እድሜያቸው ብዙዎች በተጎዱበት ‹‹የስፔን ትኩሳት›› ተብሎ በሚታወቀው በሽታ ሞቱባቸው፡፡ የተቀሩት ስምንት ልጆች ግን ልዩ በሆነ ሸጋ ፀባይ ሕይወትን መቀጠል ችለው ነበር፡፡ በእርግጥ ሁሉም ለመማር እና ዲግሪ ለማግኘት በቅተዋል፡፡

አልቤርቶ እና ማሪያ እለታዊ ኑሮአቸውን የሚጀምሩት ቅዳሴ በመስማት እግዚአብሔር ስለሰጣቸው የሕይወት ስጦታ ምስጋና በማቅረብ እና እንዲሁም ስለገጠሙአቸው ችግሮች እና የእለት ከእለት ሁኔታዎች እርዳታን በመጠየቅ ነበር፡፡ የቅድስት ጃና ወንድም አባ ጁሴፔ እነደሚመሰክሩት ‹‹የእኛ ቤተሰቦች ከለሊቱ በአሥራ አንድ ስዓት ከእንቅልፋቸው ይነቁ ነበር፡፡ አባታችንከጥዋቱ በአሥራ አንድ ተኩል ወደ ቤተክርስቲያን ይሄዱ ነበር፡፡ እንዲሁም እናታችን ቁርሱን እና ወደ ሥራ ይዞት የሚሄደውን ምሳ ታዘጋጅለት ነበር ፡፡ እሱ ወደ ሙላን የሚሄደውን ባቡር ለመያዝ ሲወጣ ለኛ ቁርስ ታዘጋጃለች፤ እኛም ከጥዋቱ አንድ ስዓት ወደ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ለመስማት እንሄዳለን፡፡ ታላላቆቻችንም በርሷ ምሳሌነት የታነፁ ስለሆኑ በስምምነት በመንቃት ለቅዳሴ እሷን ይከተሏታል ፡፡ እነሱ ከተመለሱ በኋላ ቁርሳችንን በአንድ ላይ እንበላለን ከዛም እያንዳንዳችን የየራሳችንን ልዩ ልዩ ዕለታዊ ተግባር እናከናውናለን፡፡

ይህን ትልቅ ቤተሰብ ማስተዳደር ቀላይ ሥራ አልነበረም፡፡ በእነ በሬታ ቤተሰብ ውስጥ ብቸኛው ደሞዝተኛ በሚላን ጽሕፈት ቤት ይሠሩ የነበሩት የቤቱ አባወራ ብቻ ናቸው፡፡ ነገር ግን አቶ አልቤርቶ አንድ ቀንም ፈርተው ወይም ተስፋ ቆርጠው አያውቁም ነበር፡፡ አባ ጁሴፔ እንዳሉት ‹‹ለትምህርት ክፍያችን እናት እና አባታችን ከማንኛውም ነገር ላይ ገንዘብ ይቆጥቡ ነበር፡፡ እያደግን በሄድን ቁጥር ብዙ ገንዘብ ያስፈልገን ነበር፡፡ አባት እና እናታችን ከሚገባ በላይ ወጪ ማድረግ ተው፡፡ አባታችን ማታ ከእራት በኋላ ሲጃራ ማጨስ ይወድ ነበር እናም በድንገት ማጨሱን ተወው ፤ ምክንያቱም የማያስፈልግ ወጪ መሆኑን ስለተገነዘበ ነው፡፡ እናታችንም ገንዘብ ለመቆጠብ ልብሳችንን ማታ ማታ እራሷ ትሰራልን ነበር፡፡ እሷ በልብስ ሥራ በጣም ጎበዝ ስለነበረች አንዳንዴ ሀብታም እመቤቶች እና የትምህርት ቤት ጓደኞቻችን እናቶች ለነሱም እንድትሰራላቸው በመፈለግ ልብሳችንን የሚሰራልን ማን የገንዘብ ችግር የበሬታን ቤተሰብ ልጆቻቸውን ከማስተማር፣ ለሌሎች ከማሰብ፣ ከማፍቀር እና ድሆችን ከመርዳት አላገዳቸውም፡፡

አባ ጁስፔ ሲያስታውሱ እንዲህ ይላሉ ‹‹እሁድ እሁድ እኛ ሁላችንም ቅዳሴ ለመስማት በሁለት ስዓት ወደ ቁምስናችን ቤተክርስቲያን እንሄዳለን፡፡ ሁለት መደዳ እግዳሚ ወንበሮችንም እንይዛለን፡፡ ወንዶች ከአባታችን ሴቶችም ከእናታችን ጋር እንቀመጣለን ፡፡ ከቤተክርስቲያን እንደወጣን መንገድ ስንጀምር የኔቢጤዎችን ማግኘት የተለመደ ነበርና አባታችን የኪስ ቦርሳውን ከከሱ በማውጣት ለእያንዳንዳችን ሳንቲም ይሰጠናል፤ እኛም እየሪጥብ በመሄድ ለኔቢጤዎቹ ሳንቲም እንሰጣቸዋለን፡፡ ትላልቆች ሆነን በነበረ ጊዜም እሁድ እሁድ አባታችን በቁምስናችን የሚገኙ ድሃ ቤተሰቦችን ለመጎብኘት ይወስደናል እኛም እናታችን ያዘጋጀችውን ልብስ በቦርሳ ተሸክመን እንሄዳለን፡፡ እነዚህን ከኛ የከፋ ኑሮ ያላቸውን ሰዎች በማወቅ ድሆችን ማፍቀር እና ያለን ይበቃናል ማለትን ተምረናል፡፡ በቤተሰባችን ውስጥ ገንዘብ አባካኚነት የሚባል ነገር የሚባል ነገር አልነበረም፡፡ ነገር ግን አንድ ድሃ ሰው በራሳችንን አንኳኩቶ ባዶ እጁን ተመልሶ አያውቅም፡፡››

አንድ ትልቅ ቤተሰብ በአንድ ላይ ሲኖር ከኑሮው ጋር የተያያዙ ብዙ ችግሮች፣ አለመረዳዳት፣ ጥላቻ ፣ ክርክሮች ሊመጡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የበሬታ ቤተሰቦች ገደብ በሌለው ፍቅር እና መረዳዳት ያስተካክሉታል፡፡ አባ ጁሴፔ እንደሚያስታውሱት ‹‹ቁጣ ወይም ተገላጽ ፈጽሞ አልነበረም እናት እና አባታችን በራሳቸው በጣም ጠንካሮች ነበሩ ነገር ግን ለኛ በጣም በጣም ደጎች ነበሩ፡፡ አንዳችንን አንኳን ጥፊ የመቱበት ቀን አይታወሰኝም፡፡ በደግነት እና በጽኑ እምነት አሳድገውናል፡፡

ከወላጆቻችን ጋር መሆን ስለምንፈልግ ማታ ማታ ወደ ቤት የመሄድ ልማድ ነበረን አባታችንም ከሥራ ተመልሶ እናገኘዋለን፡፡ የንግግር ርእሳችንም የነበረው ስለ ትምህርት ቤት እና ስለ አጋጠሙን ችግሮ ነበር፡፡ እራት ሁሉ አንድ ላይ እንበላ ነበር፡፡ ከእራት በኋላ እናወራለን፣ እናታችን ኤሚልያ የምትጫወተውንም ሙዚቃ እናዳምጣለን እናም ወደ መኝታ ከመሄዳችን በፊት መቁጠሪያ እንደግማለን መቁጠሪያውን ይመራን የነበረው አባታችን ነው፡፡ እሱም ከእመቤታችን ምስል ፊት ለፊት ይቆም ነበር፡፡ ታላላቆቻችን ከሱ ቀጥለው ይቆሙ ነበር፤ ታናናሾች ደግሞ እናታችን አጠገብ እንንበረከክ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ እኛ ትንንሾቹ እናታችን በተንበረከከችበት እናንቀላፋ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቀላል እና ጥልቅ ፍቅር ያለበት ቀጣይ ባህሪያዊ ኑሮ ነበር፡፡››ኑሯችን እና አስተዳደጋችን ለየት ያለበት ምክንያት በዚህ ነበር፡፡

ጃናም ዶክተር ሆነች አሁን ደግሞ ቅድስናዋ ታወጀ፡፡ ሌሎች ወንድሞችዋ እና እህቶችዋን የታወቁ ባለሙያዎች እና ለሌሎች ጥቅም በመንቀሳቀስ የሚደነቁ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ኤንሪክ በሕክምና ዲግሪውን ካገኘ በኋላ አባ አልቤርቶ የሚለውን ስያሜ በመቀበል የካፑቺን ወንድሞች አባል ሆኗል ፡፡ ወደ ብራዚልም ልኡክ ሆኖ በመሄድ ለማንኛውም በሽታ የሚን በልዩ ሁኔታም የሥጋ ደዌ ህሙማን ሆስፒታል መሥርቷል፡፡ ኢንጅነር ፍራንቼስኮም ሙያውን በጣሊያን አገር ተግባራዊ ካደረገ በኋላ ወደ ብራዚል ሄዶ ከወንድሙ ጎን በመሆን ለብዙ ዓመታት የሆስፒታል ሕንጻ ሥራ በመምራት አገልግሏል፡፡

የማሕፀን ሐኪም ፈርዲንድም ሙያውን በሎምባርዲያ ተግባራዊ በማድረግ በታካሞዎቹ ዘንድ ተወዳጅነት ነበረው የመወደዱ ምክንያት ያዳምጣቸው እና ያክማቸው ስለነበረ ብቻ አይደለም በችግር ላይ ያሉትን በገንዘብም ጭምር ያግዛቸው ስለነበረ ነው፡፡ ከዚያም ኢንጅነር ጁሴፔ ካህን ሆነ፡፡ ከአርባ ዓመት በላይ በቤርጋሞ ሀገር ስብከት ለሚሰሩት የሃይማኖታዊ ተቋም ህንፃዎች ኃላፊ ነበር፡፡ ዶክተር ቪርጃኒያም የካኑሳውያን ማኅበር ሲስተር በመሆን ተልእኮዋን እና ሙያዊ ግዴታዋን ለመወጣት ወደ ሕንድ ሄደች፡፡ ፋርማሲስቷ ዚታም ሙያዊ ሥራዋን በመተው በደግነት ያረጁ እና የደከሙ ወላጆችዋን ተንከባከበች፡፡ እሷ አባ አልቤርቶ ከሠላሳ ሦስት ዓመት የተልእኮ ሥራ በኋላ ባጋጠመው ድንገተኛ የአካል ጉዳተኛነት የሚያግዘው ሰው ያስፈልገው ስለነበር ለሃያ ሁለት ዓመት አገልግላዋለች፡፡

የፒያኖ ጠቢቧ ኤሚልያ በሃያ ስምንት ዓመት ዕድሚዋ ሞታለች፡፡ አስቀድሜ እንደገለጽኩት ከነዚህ ከስምንቱ ድንቅዮ ልጆች መካከል ሁለቱ ብቻ አሁንም በሕይወት አሉ፤ እነሱም ኢንጅነሩ ካህን አባ ጁሴፔ ዶክተሯ የካኑሳውያን ሲስተር ቪርጂኒያ ናቸው፡፡

ስለቅድስቷ እህታቸው ሊነግሩኝ የቻሉት ቤርጋሞ በሚገኘው ቤታቸው ሄጄ ስለአገኘሁዋቸው ነው፡፡ ይህ ሙሉ በሙሉ ልብን የሚነካ ወይም የሚመስጥ አጋጣሚ ነበር ፡፡ ፈጽሞ የማልረሳው ነገር ቢኖር አስተዋይነታቸው፣ ጥበባቸው እና ደግነታቸው ነው፡፡


ምንጭ ፡- ሜጅጉሬ ቁ.48 ጸሐፊው፡- ሬንዞ አሌግሪ እና በስሟ የሚገኝ ድረ ገጽ

ተርጓሚ፡- ሩፋኤል በቀለ {jathumbnail off}