ከእኔ ይልቅ ለእኔ የሚቀርበው እግዚአብሔር

ከእኔ ይልቅ ለእኔ የሚቀርበው እግዚአብሔር

Jesus-loveሰሞኑን እመለካከታቸው ከነበሩ መጻሕፍት መካከል በአባ ዤራርድ ሒዩስ የተጻፉ ሁለት መጻሕፍት ነበሩ፡፡ አንደኛው "God, where are you?" የሚል ርእስ ያለው ሲሆን ሁለተኛው "God of Surprises" ይሰኛል፡፡ የመጀመሪያው እንደቅዱስ አውጉስጢኖስ ኑዛዜዎች (Confessions) የተባለው መጽሐፍ አባ ዤራርድ ከሦስተ ዓመታቸው ጀምሮ መጽሐፉን እስከጻፉበት ጊዜ ድረስ እግዚአብሔርን ፍለጋ ያደረጉትን ጉዞ ለዛ ባለው ውብ ፍልስፍናዊ ትረካ ያስቃኙናል፡፡ "God of Surprises" የተሰኘው ሁለተኛው መጽሐፍ የተጻፈበትን ዓላማ ደግሞ የመጽሐፉ ጀርባ ላይ እንዲህ ተብሎ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡-

Jesus said: 'The Kingdom of Heaven is like a treasure hidden in a field.' This book has only one purpose: to suggest ways of finding the treasure in what we may consider a most unlikely field- ourselves. It is a guide book to the inner journey which we are all engaged and has much to say to those who have a love/hate relationship with the Church to which they belong or once belonged. (አጽንዖት የኔ)

ዐቢይ ጉዳዩ እግዚአብሔር በሕይወታችን የሚሠራባቸውን እኛ ግን የማናስተውላቸውን አስደናቂ መንገዶች በማየትና በዚህም እግዚአብሔር ምን ያህል እንደሚወድደን በማሰብ በፍቅሩ መደነቅ፣ በአሠራሩ ግሩምነት መመሰጥ፣ በሕይወትነቱ መኖር ነው፡፡ ከዚህ መጽሐፍ ካገኘኋቸው ቁም ነገሮች ጥቂቶቹን ላካፍላችሁ፡፡

ከእኔ ይልቅ ለእኔ የሚቀርበው እግዚአብሔር

ቅዱስ አውጉስጢኖስ በኑዛዜዎቹ 'God, you are closer to me than I am to myself.' ኢትዮጵያዊው ባለቅኔ ደግሞ

እመኒ ትሁቦ ዕረፍተ ወሀብተ መከራ ትሁቦ

እምርእስየ ለርእስየ አንተ ትቀርቦ፡፡

እንዳለው፣ አባ ዤራርድ እግዚአብሔር በሕይወታችን ለአፍታም እንኳ ከእኛ የማይለይ ወዳጃችን እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ እኛ ወደድነውም ጠላነውም፣ ተቀበልነውም ፊት ነሣነውም እርሱ እኛን ከመውደድ አያቋርጥም፡፡ "በዘለዓለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ፡፡" እንዲል መጽሐፍ፡፡ ስለሚወድደንም ከዕለተ ፅንሰታችን ጀምሮ ይከታተለናል፡፡ በየቀኑም በጥበቃው፣ በመግቦቱ ወደ ራሱ ያቀርበናል ይላሉ፡-

In our journey towards God, our whole being reacts to the direction in which we are moving. God is continuously drawing us to himself in everything we experience.

Yahweh, you examine me and know me,

you know if I am standing or sitting,

you read my thoughts from far away,

whether I walk or lie down, you are watching,

you know every detail of my conduct...

It was you who created my inmost self,

and put me together in my mother's womb. (Psalm 139)

ይህንን መግቦቱን፣ ጥበቃውን አስተውለን ጥሪውን ተከትለን የሕይወት ኮምፓሳችንን ወደ እርሱ ካላስተካከልን በስተቀር ኑሯችን ዕረፍት እንደማይኖራትም ቅዱስ አውጉስጢኖስን ምስክር ይጠራሉ፡-

St. Augustine recognized this action of God in every movement of his heart and so wrote in his Confessions, 'Thou hast created us for thyself, and our heart cannot be quieted till it may find repose in thee' (Confessions c. 1)

በቃ! እግዚአብሔር የሕይወታችን መነሻና መድረሻ፣ አልፋና ኦሜጋ መሆኑን ካላመንን በስተቀር ልባችን ዕረፍት የለውም- ለምን ቢባል የተፈጠርነው በእርሱ ለእርሱ ነውና፡፡ ባዶነትና ዕረፍተ ቢስነት ይህን የእግዚአብሔርን መነሻና መድረሻነት ያለማመን በሽታ የምናስተውልበት ምልክት ነው፡፡ ደግነቱ ምልክቱ መፍትሔው ምን እንደሆነ ያመለክተናል፡፡ ይህንን አስመልክተውም እንዲህ ብለው ጽፈውልናል፡-

God is the answer to our inner restlessness and emptiness. When we move towards him, that is when the fundamental option of our lives is directed to his praise, reverence and service, then our feelings and emotions resonate with this movement and we experience peace, tranquility and joy in some measure. Whatever we do, whatever decision we make, if it is in accord with this fundamental, then the action or decision will deepen, or at least not disturb, our peace, tranquility and joy. If we act or decide in a way contrary to this fundamental direction, the dissonance will register somehow in our feelings, leaving us bored or anxious, agitated or sad. (p92)

በሕይወታችን የሚያጋጥሙን፣ የሚደረጉብንም ሆኑ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ሕይወታችን እግዚአብሔርን ማዕከል ያደረገ እስከሆነ ድረስ በእኛና በእግዚአብሔር መካከል የሚቆሙ ግድግዳዎች ከመሆን ይልቅ ወደ እግዚአብሔር በምናደርገው ጉዞ የምናድግባቸው የመላቂያ ነጥቦች እንደሆኑ ያሠምሩበታል፡፡ አቅጣጫችንን ከእግዚአብሔር ተኮርነት ስንለይ ግን ለጊዜው ምቾትና ዕረፍት ብናገኝም እየቆየ መረበሻችንና የስሜት ስክነት ማጣታችን አይቀርም፡፡ ጊዜያዊ ደስታችንም ያልፍና ውስጣችን ባዶነት ሊሰማው ይጀምራል፤ ፍርሃት ይነግሥብናል፡፡ ለዚህ ትምህርታቸው የሎዮላውን ቅዱስ ኢግናጢየስ "Spiritual Exercises" የተሰኘ የመንፈሳዊ ምሪት መጽሐፉን ይጠቅሳሉ፤ እንዲህም ያብራሩታል፡-

While this is a very general guideline, it can cause anxiety to some people, who begin to wonder whether the core of their being is God- centered or not and this doubt can cause them great inner agony. If you find yourself worrying in this way, it is a sign that the core of your soul is God- centered: if it were not, you would have no such worry.

It is also important to notice that a person who has no explicit religious belief may be, in fact, very God- centered, while another who claims religious belief and practices religious observance may be turned away from God. In St. Mathew's Gospel (Chapter 25), Christ describes the Final Judgment, showing that our relationship to God is expressed in our relationship to other people. (92- 93)

በማብራሪያቸው እንደሚታየው ሰዎች ሕይወታቸው እግዚአብሔርን ማዕከል ማድረጉን ሊያውቁ የሚችሉት ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ነው፡፡ በጎረቤቶቻቸው ውስጥ የሚገለጠውን እግዚአብሔርን ማስተዋል እስካልቻሉ ድረስ በከፋ መንፈሳዊ ዕውርነት ይኖራሉ፡፡ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲመላለሱ ቢታዩም ክርስቶስን የሚመስል ሕይወት ግን የላቸውም፡፡ ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ሕንጻ ውስጥ ቁጭ ብሎ የሚጠብቃቸውን እንጂ ኢትዮጵያዊው የመልክአ ኢየሱስ ደራሲ "ሰላም ለጕርዔከ በጽምዐ ፍቅረ ሰብእ ሐማሚ" (በሰው ልጅ ፍቅር ጥም ለታመመ ጉሮሮህ ሰላም ይሁን፡፡") እንዳለው በኑሯቸው ዙሪያ በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ውስጥ ሆኖ ፍቅራቸውን የሚጠማውን ኢየሱስን ማየት አይችሉምና፡፡

ኃጢኣት እና ንስሐ

ኃጢኣት ማለት እግዚአብሔርን እግዚአብሔር እንዳይሆን መከልከል ነው፡፡ ንስሐ ደግሞ እግዚአብሔር እንደ ስሙ "እግዚኣ ለብሔር" የዓለም ጌታ፣ የዩኒቨርሱ ጌታ መሆኑን ማወቅ ብቻ ሳይሆን የእኔ ጌታ፣ የእኔ አምላክ እንዲሆን መፍቀድ ነው፡፡ ከእርሱ በስተቀር አንዳችም የምንታመንበት እንዳይኖረኝ ማድረግ ነው፡፡ ከጽድቁ በስተቀር አንዳች የምመኘው ክብር ወይም ዝና ወይም ሌላ ነገር እንዳይኖረኝ ማድረግ ነው፡፡ በሰማይ የሆነችው ፈቃዱ በእኛ በምድራውያን ዘንድ የምትፈጸም አምላክ እንዲሆን መፍቀድ ነው፡፡ ቀኖቼን ሁሉ በእርሱ፣ ስለእርሱ እና ለእርሱ መስጠት ነው፡፡

ሆኖም ይህ ነገር በሕይወታችን አንድ ጊዜ አድርገን የምናጠናቅቀው ነገር አለመሆኑን ማሰብ ይገባል፡፡ ይልቁንም በእግዚአብሔር ፈቃድ ፈንታ የእኛን ፈቃድ እንድንፈጽም የሚያደርገንን፣ እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ እንዲሠራ ሳይሆን እኛ እርሱን የራሳችንን ክብርና ምልኪ ፍለጋ እንደመሣሪያ እንድንጠቀምበት የሚጋብዘንን፣ በእግዚአብሔር አምላክነት ፈንታ የእኛን ምስል እንድናቆም የሚጠራንን ፍላጎታችንን የምንዋጋበት የዕድሜ ልክ ጦር ሜዳ መሆኑን እንዲህ ሲሉ ይገልጻሉ፡-

We can never reach a stage before death when we no longer need repentance, because layers and layers of consciousness within us, and each moment of existence can reveal these layers, if we let it, and show us the depth of the tendency within us to refuse to let God be God.

God is gentle. He gradually reveals our sinfulness to us. He doesn't seem to worry about our past wrongdoing, even though its effects may still be causing suffering to ourselves and others. 'Though your sins are like scarlet, they shall be as white as snow." (p.73)

በምድር ስንመላለስ የእግዚአብሔር ልጆች እንደሆንን በሚመሰክር ክርስቶስን በሚመስል ኑሮ መኖር እንደ ዓይን ቅጽበት በአንድ ጊዜ የምንደርስበት ግብ አለመሆኑን ማሰብ ተገቢ ነው፡፡ አባ ዤራርድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔርን መንግሥት በሰናፍጭ ቅንጣት መስሎ ለምን እንዳስተማረ እንዲህ ያስረዳሉ፡-

The kingdom of heaven is like a mustard seed which a man took and sowed in his field' (Matt. 13: 331). The growth of the kingdom in our hearts is slow. What is important is not the present size of the mustard seed within us, but that we allow it to germinate. In other words, keep praying for poverty of spirit and do not be deterred by what you consider your poor progress. Preoccupation with our spiritual progress is unhealthy, a sign of our false self. We must accept our failures, whether they be real or imagined, as opportunities for growth in knowledge of the truth that God, and God alone is our rock, our refuge and our strength. St Paul writes of the joy of this truth: 'For I am certain of this: neither death nor life, no angel, no prince, or height or depth, nor any created thing, can ever come between us and the love of God made visible in Christ Jesus our Lord' (Rom. 8: 38- 9)

እንዲህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በፍጹም ደስታ ማመሥገን እንድንችል በመጽሐፋቸው ፍጻሜ ያሰፈሩትን የቅዱስ ኢግናጢየስ ዘሎዮላን ጸሎት ከአባ ዤራርድ ጋር በትዕግሥት እንጸልይ፡-

ጌታ ሆይ! ነጻነቴን፣ የማስታወስ ችሎታዬን፣ የመረዳት ብቃቴንና ፈቃዴን፣ ያለኝን ሁሉ ውሰድ፤ ተቀበለኝም፡፡ ሁሉም አንተ የሰጠኸኝ ነውና እኔ ያለኝ ነገር ሁሉ ያንተ ነው፤ ወዳንተም እመልሰዋለሁ፡፡ ጌታ ሆይ ውሰደኝ፡፡ የምትወድደውንም በእኔ ላይ አድርግ፡፡ ብቻ ጸጋህንና ፍቅርህን ስጠኝ- ለእኔ እርሱ ብቻ ይበቃኛልና፡፡ አሜን፡፡

ከሣህለ ሚካኤል