ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስና ኦርቶዶክሳዊው ፓትሪያርክ በርቶሎሜዎስ ስለ ክርስቲያኖች ኅብረት በኢየሩሳሌም ጸሎት አደረሱ

Category: የክርስቲያኖች ኅብረት Written by Super User Hits: 4598

Pope Patriarch Bartholomew Jerusalem web..ጳ. ፍራንቼስኮስና የቁስጥንጥኒያ መንበር ፓትሪያርክ የሆኑት በርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ ባለፈው እሑድ በኢየሩሳሌም ተገናኝተው ስለ ክርስቲያኖች ኅብረት በአንድ ላይ ሆነው ጸሎት ያደረሱ መሆኑና ስለርእሰ ሊ.ጳ. የሦስት ቀናት ቆይታም ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስና የፓትሪያርክ በርቶሎሜዎስ ቀዳማዊ የክርስቲያኖች ኅብረት ጸሎታቸውን ያደረሱት በክርስቲያኖች ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት፣ የተቀበረበትና ከሞትም የተነሣበት ነው ተብሎ በሚታመንበት ቦታ ላይ ሲሆን ሁለቱ አባቶች በአብያተ ክርስቲያኑ መካከል ይበልጥ ኅብረት ይኖር ዘንድ የጸለዩበት ቦታ “የመቀቢያ ድንጋይ” ተብሎ በሚጠራው ማለትም ጌታችን ከመቀበሩ በፊት አስክሬኑ እንዳረፈበት በሚነገረው ድንጋይ ላይ ተንበርክከው መሆኑ ይህን ጸሎት ይበልጥ ትርጉማዊ ያደርገዋል።

ከጸሎቱም ቀደም ሲል የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የበላይ የሆኑት ር.ሊ.ጳ. እና የምስራቃዊቷ የዓለም ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የበላይ የሆኑት ፓትሪያርክ ለካቶሊክና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጋራ የሆኑትን እሴቶች የሚያጎላ ተከታታይ ንግግሮች ለማድረግ ተፈራርመዋል፤ “የዛሬው ወንድማማቻዊ ግንኙነታችን ወደ ኅብረት በምናደርገው ጉዞና በተገቢ ልዩነታችን ውስጥ በምናደርገው ኅብረት አዲስና አስፈላጊ እርምጃ ነው” ይላል የመግለጫው አንደ ሐረግ። ይህ ሰነድ በኢየሩሳሌም የሚገኙ 13 የካቶሊክና የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች በተገኙበት መፈረሙም ታውቋል። {jathumbnail off}

ይህ ክንውን የር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጉብኝት ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ሲታወቅ፤ የሁለቱ አባቶች ግንኙነት ከ50 ዓመታት በፊት በጊዜው ር.ሊ.ጳ. በነበሩት ጳውሎስ ፮ኛውና ፓትሪያርክ አቴናጎራስ የተደረገውንም ግንኙነት ያስታወሰ ነው።  

እሑድ ማለዳ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ እስራኤልን ከፍልስጤም ለመለየት በጋዛ ሰርጥ በተገነባው አጥር ሲያልፉ በተያዘው እቅድ ወስጥ ባይኖርም አስቁመው በግንቡ አጠገብ በጸጥታ ጸሎት ያደረሱ ሲሆን ይህ ግንብ በእስራኤልና በፍልስጤማውያን መካከል ትልቅ የውጥረት ምክንያት መሆኑ ይታወቃል።

Pope Patriarch Bartholomew Jerusalem

ከጀረመን ድምጽ ድረ ገጽ የተተረጎመ ጭብጥ http://www.dw.de/pope-joins-orthodox-patriarch-in-historic-prayer-for-unity/a-17661933