ትእምርተ-መስቀል /ማማተብ/

ትእምርተ-መስቀል /ማማተብ/

የክርስቶስ መስቀል የምናከብርበት ቀላሉና ግልጹ መንገድ እትምርተ-መስቀል በመሥራት /በማማተብ/ ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የመስቀል ምልክት የሚያደርጉት ግንባራቸው ላይ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ በትልቅ ምልክት ተተካ፡፡ ይኸውም ግንባር ላይ ብቻ ተወስኖ የነበረው ከግንባር ወደ ደረት ከዚያም ወደ ግራ ትከሻ ከግራ ትከሻ ወደ ቀኝ ትከሻ ማድረግ ተጀመረ፡፡

የመስቀል ምልክት ማድረግ /ማማተብ/ ለክ ጋሻን ይዞ “ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል?” ሮሜ 8፡35 እንደማለት ነው፡፡ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለበት ወቅት መስቀሉ ኢየሱስን ተሸከመው እንጂ ኢየሱስ መስቀሉን አልተሸከመውም፡፡ ስለዚህ እኛም በመስቀሉ የድጋፍ መሠረት እናገኛለን።

ትእምርተ መስቀል ማድረግ ተጨባጭ የሆነ የእምነታችን ይዘት ነው ከላይ ከግንባራችን እንጀምራለን። ይህ የሚያሳየው ሁሉም ነገር የሚጀምረው ከላይ ከሰማይ የሁሉም ነገር የመጀመሪያ ፈጣሪ የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከእግ/ር ዘንድ እንደሆነ ነው፡፡ ከዚያም እጃችን ወደ ደረታችን እናወርደዋለን፡፡ ይህም የሚያሳየው እግ/ር ከሠማይ ወርዶ በልባችን በሚኖረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው እንደሆነ ነው፡፡ ይህ ከላይ ቀጥታ የሚወርደው መስመር ምስጢረ-ሥጋዌን ያሳያል፡፡ ይህን መስመር በመከተል ከግራ ትከሻችን ወደ ቀኝ ተከሻችን መስመር እናሰምራለን። ይህ ደግሞ የሚያሳየው ሁሉንም ነገር ያገናኘውና አንድ ያደረገው መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ነው፡፡ እግ/ር በዚህ ዓለም ላይና ወደ ጎን (Horizontal) ባለን ትስስርና ግንኙነት ውስጥ የሚሰራው በመንፈሱ አማካይነት ነውና፡፡

ትእምርተ መስቀል ከማድረግ ፈንታ እኛ እራሳችን እጆቻችንን በመዘርጋት መስቀል ልንሆን እንችላለን፡፡ የሰው ልጅ እጆቹ ሲዘረጉ በጣም ውብ ነው፡ ይኸውም ወደ እግ/ር ለመፀለይ አሊያም ጎረቤቱን ለማቀፍ ነውና። የመስቀል ምልክት በቋሚነት የሚያስታውሰን ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀልን እና የራሳችን ሕይወት እንደማንኖር ነው፡፡ /ገላ 2፡19/

አባ ተሻለ ንማኒ - ሲታዊ

Source (This is the day the Lord has made 365 daily meditations: By Wilfrid Stinissen)