እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የእግዚአብሔር መንግሥት

የእግዚአብሔር መንግሥት

ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት (አልፎ አልፎ መንግሥተ ሰማይ ብሎ ይጠራዋል) ይናገራል፡፡ ይህ መንግሥተ ሰማይ የሚለውን ሐረግ ምንአልባት ከሞት በኋላ አንድ ቀን እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንደምናየው ተስፋ የምናደርግበት ሕይወት ይመስለን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ወይም ስለ መንግሥተ ሰማይ ሲናገር ከሞት በኋላ (ከዚህ ምድራዊ ሕይወት በኋላ) ስላለው ሕይወት ብቻ አያመለክትም፡፡

የእግዚአብሔር መንግሥት የምድር ላይ ሕይወታችንን መመዘን  የሚችል እውነታ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት እግዚአብሔር እኛንና ሁሉንም ተፈጥሮ የሚያስተዳድርበት የሕይወት ሁናቴ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ለማድረግ የፈለገውን መፈፀም ከቻለ ማለትም ከአንተ ምንም ዓይነት መከላከል ካልገጠመው አንተ በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ አለህ(ትኖራለህ) ማለት ነው፡፡ በጌታ ፀሎት (አቡነ ዘበሰማያት) መንግሥትህ ትምጣቀጥለን ደግሞ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነ እንዲሁም በምድር ይሁን በማለት እንፀልያለን፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ በሰማይ በምልአት እና በነፃነት እንደሆነ ሁሉ በእኛ ውስጥም ልክ እንደዚያው ሲሆን የእግዚአብሔር መንግሥትም ይመጣል፡፡ 

የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲመጣ መጸለይ ማለት አምላክ ሆይ! ንጉሴና ጌታዬ ሁን መጥተህም ግዛኝ፡፡ እንደማለት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር እመቤታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም እንዳለችው እነሆ!እኔ የጌታ አገልጋይ ነኝ አንተ እንዳልክ ይሁንልኝ፡፡ (ሉቃስ 1፡38) ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር ሁለንተናችንን እንዲያስተዳድር ከመናፈቅና በሁኔታዎች ያልተወሰነ እሺታን ለእርሱ ከመስጠት የላቀ ምንም ነገር የለም፡፡


ዲያቆን ተሻለ ንማኒ - ሲታዊ - ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ አ.አ.

(source:- This is the day the Lord has made. by Wilfrid Stinissen Nov. 25)

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት