የተተወ አምላክ ይሆን የምናመልከው?

የተተወ አምላክ ይሆን የምናመልከው?

አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ ?(ማር 15:34)

ከፍቅርና ሰላም የተወሰደ መጋቢት 2001 ዓ.ም.

በአዲስ ኪዳን ውስጥ አራቱ ወንጌላቸውን የመጨረሻው ክፍል የጌታችን የመድኃኒታችን ክርስቶስ ሞት ተፈርዶበት መስቀሉን ተሸክሞ ጎሎጎታ ወደ ተባለው ወደሚሰቀልበት ቦታ እንደደሰና እዛም ስቃዩ እጅግ በጣም የመረረ እንደነበር በአንድ ድምፅ ይተርኩልናል።

እያንዳንዱ ወንጌላዊ የሙሴና የነቢያትን መጽሐፍት በተለያየ መልክ በመጥቀስ በወቅቱ በኢየሱስ ስቃይ ሞትና ትንሳኤ ምክንያት መረዳት ቸግሮት ግራ ተጋብቶ ለነበረው ማህበረሰብ ስላስተማሩ በወንጌላቸው በሚያካትቱቸው አባባሎችና ጥቅሶች ምክንያት በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ለየት ያሉ ሚስጢራዊ አገላለጾች እናገኛለን። ለምሳሌ ቅዱስ ማቴዎስና ቅዱስ ማርቆስ ዘጠኝ ሰአት ሲሆን ኢየሱስ “ኤሎሄ ኤሎሄ ለማሰብቅታኔ?” ሲል በታላቅ ድምጽ ጮኽ ትርጉሜውም “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ነው። በማለት (ማር 15:34 ፤ ማቴ 27:46)።

cucifix_2

ቅዱስ ሉቃስ ይህንን ከላይ የተገለጸውን ኢየሱስ ምንም ያህል ስቃዩ ቢባዛ በአባቱ በእግዚአብሔር የሚተማመን አምላክ ነው እንጂ እራሱን የተተወ አምላክ አድርጎ በመቁጠር አይጮህም። እግዚአብሔር አባትም በመረረ ስቃይ ውስጥ በመሆን የሚጮኽው አንድ ልጁን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት የሚረሳ ስላልሆነ ቅዱስ ሉቃስ ይህንን ገለጻ አይጠቀምበትም። በዚህም ምትክ ቅዱስ ሉቃስ ሌላ አገላለጽ በመጠቀም “ኢየሱስም ድምጹን ከፍ አድርጎ “አባት ሆይ! እነሆ ነፍሴን በእጅህ አስረክባለሁ!” በማለት ይገልጻል(ሉቃ 23:46)። ይህም ማለት ለቅዱስ ሉቃስ ኢየሱስ በአባቱ እጅግ በጣም የሚመካና ነፍሱን እንኩን በእጁ በአደራ የሚያኖር ተወዳጅ ልጅ እንደሆነና አባቱም መተማመኛ አለቱ እንደሆነ አድርጎ ያቀርበዋል። ወንጌላዊውን ቅድስ ዩሐንስ ስናይ ደግሞ የሦስቱንም ወንጌላውያን አባባል ሙሉ በሙሉ በመተው ለየት ባለ አገላልጽ ለተለያዩ ነገሮች ትኩረት በመሰጠት አበክሮና ዘርዘር አድርጎ ያቀርበዋል። በዚህም መሰረት እሱ ለሚያስተምረው ማህበረሰብ የኢየሱስን መራራ ስቃይና ሞት በማስረዳት በብሉይ ኪዳን ቀድሞ ተነግረው የነበሩትን ነገሮች በመውሰድና ትርጉም የተሞላበት ትንተና በመስጠት ሌሎች ወንጌላት ውስጥ የማናገኛቸውን ዜናዎች ይገልጽልናል። ለምሳሌ የኢየሱስ እጀ ጠባብ ከላይ እስከታቸ ወጥ ሆኖ የተሰራ እንደነበርና ወታደሮቹም ይህንን እጀ ጠባብ ሳይቀዱ እጣ እንደተጣጣሉበትና በመስቀሉ አጠገብ እነማን እንደነበሩ በመጨረሻ ደቂቃ ጠማኝ እንዳለነና ራሱን ዘንበል አድርጎ ነፍሱን አሳልፎ እንደሰጠ ጥበብ በሞላበት ሁኔታ ይገልጽልናል። እዚህ ላይ በአራቱም ወንጌላት ውስጥ ወታደሮቹ ወደ ኢየሱስ ቀርበው ሆምጣጤ እንደሰጡት ቢገልጽም በተለየ መልኩ ቅድስ ዩሐንስ “ኢየሱስ አሁን ሁሉንም ነገር እንደፈጸመ አውቆ በመጽሐፉ የተጻፈውን ቃል እንዲፈጽም “ጠማኝ” አለ በማለት ጠምቶት ጥሙን መግለጹን አበክሮ ያስረዳናል (ዮሐ. 19:28)”።

 

ይህንን የሕማማት ምስጢር የሚገኝበትን የወንጌል ክፍል በምናነብበት ጊዜ የተለያዩ ጥያቄዎች በብዙዎቻችን አእምሮ ውስጥ እንደሚመላለሱ ግልጽ ነው። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሕይወቱን አሳልፎ ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ የሞቱን ትርጉም ለዛውም በመስቀል ላይ እንደ ወንጀለኛ ተገርፎና ተዋርዶ የእግዚአብሔር ልጅነት ክብሩን አጥቶና በጅራፍ ተገርፎ በደረቅ እንጨት ላይ በሚስማር ተቸንክሮ ደምቶ እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ማለፉ በብዙዎች ህሊና ይህን ያህል ለምን አስፈለገ? እግዚአብሔር ዓለምን በሌላ መልኩ ማዳን አይችልም ነበርን? ይህንን ሁሉ ይሆን ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነስ አንድ ልጁ በስቃይና በመከራ ውስጥ በመስቀል ላይ ተንጠልጥሎ የጣር ጩኽት ሲያሰማ ለምን ትንሽ እንኳን የአለሁ ባይነቱን ምልክት አላሳየውም? ኢየሱስ በሰዎች እጅ ተላልፎ እሰጣለሁ በሶስተኛው ቀን ከሞት እንሳለሁ በማለት ተናግሮ ነበር፤ ስለዚህ መሞት እንዳለበትና ከሙታን መነሳቱን እያወቀ በመጨረሻው ሰዓት ለምን ፍርሃትና መታወክ የተሞላበት ጩኸት ሲያሰማ ለምን ትንሽ እንኳን የአለሁ ባይነቱን ምልክት አላሳየውም? ኢየሱስ በሰዎች እጅ ተላልፎ እሰጣለሁ በሶስተኛው ቀን ከሞት እነሳለሁ በማለት ተናግሮ ነበር፤ ስለዚህ መሞት እንዳለበትና ከሙታን መነሳቱን እያወቀ በመጨረሻው ሰዓት ለምን ፍርሃትና መታወክ የተሞላበት ጩኸት ወደ እግዚአብሔር አብ ማሰማት ፈለገ? በእግዚአብሄር አብ የነበረውን ተስፋ ተሟጦ ተትቼ እቀራለሁ የሚል ስጋት ነበረውን? እኛስ የተተወ አምላክ ይሆን እንዴ የምናመልከው? ዛሬ በየቤቱና በየሆስፒታሉ በስቃይ ላይ ለሚገኙትስ ስቃያቸው ትርጉም ይኖረው ይሆን የሚሉና ሌሎች የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ ይሰምል። በእርግጥ እንደዚህ ዓይነቱ ጥያቄዎችን መጠየቁ  አስፈላጊና ጠቃሚ ቢሆንም መረዳት የሚያስፈልገው ዋናው ነገር ግን በወንጌላውያን በተለያየ መልኩ የተጠቀሱት እያንዳንዳቸው ነገሮች የራሳቸው የሆነ ሚስጢር አዘል ትርጉም እንዳላቸው በማወቅ ወንጌላዊው ምን ለማለት እንደፈለገ ለመረዳት በመጣር እሩቅ መሄድ ነው።
ከዚህም አኳያ በሕማማት ታሪክ ዙሪያ ተጠቅሰው ከሚገኙት ብዙ ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነው ኢየሱስ መራራ ስቃይ ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምጽ ወደ አባቱ የጮኸው “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” የሚለው ዓረፍተ-ነገር ምን አይነት መልዕክት እንዳለውና አባባሉስ ከየት የመነጨ እንደሆነና ለምንስ በወንጌላውያን ማርቆስና ማቴዎስ ብቻ ተጠቅሶ እንደቀረበ ለማየት እንሞክራለን። ከዚህም ጋር በተያያዘ መልኩ እግዚአብሔር ለምን ጸጥታን መረጠ? ወይስ በራሱ በዚህ ጩኸት ውስጥ ቀድሞውኑ የተሰጠ የእግዚአብሔር መልስ ያካተተ ምስጢር አዘል አባባል እናገኛለን? የሚሉትና ሌሎችም ለመቃኘት እንጥራለን።

ከዚህም አኳያ በሕማማት ታሪክ ዙሪያ ተጠቅሰው ከሚገኙት ብዙ ነገሮች ውስጥ አንዱ የሆነው ኢየሱስ መራራ ስቃይ ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምጽ ወደ አባቱ የጮኸው “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” የሚለው ዓረፍተ-ነገር ምን አይነት መልዕክት እንዳለውና አባባሉስ ከየት የመነጨ እንደሆነና ለምንስ በወንጌላውያን ማርቆስና ማቴዎስ ብቻ ተጠቅሶ እንደቀረበ ለማየት እንሞክራለን። ከዚህም ጋር በተያያዘ መልኩ እግዚአብሔር ለምን ጸጥታን መረጠ? ወይስ በራሱ በዚህ ጩኸት ውስጥ ቀድሞውኑ የተሰጠ የእግዚአብሔር መልስ ያካተተ ምስጢር አዘል አባባል እናገኛለን? የሚሉትና ሌሎችም ለመቃኘት እንጥራለን።"ኤሎሄ! ኤሎሄ! ለማ ሰበቅታኒ!”ስ አመጣጡ (መሰረቱ ከየት ነው?)

ይህንን “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” የሚለውን በአረማውያን ቋንቋ ተጠቅሶ የሚገኘውን የሃዘን ጩኸት ለመረዳት ወደ መጽሐፈ መዝሙር 22:1-31 ተመልሶ በአስተውሎት መመልከቱ በአጠቃላይ የጩኸቱና ትርጉምና አምጣጡን ለመረዳት ብቻ ሳይሆን ሰፋ ባለ መልኩ የጌታችንን የሕማማት ምስጢር እንድብንገዘብ ይጠቅመናል። በእርግጥ በቅዱስ  ማርቆስ እና በሉቃስ ተጠቅሶ የሚገኘውን ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር የሚያደርገው ጥያቄ አዘል ተማጽኖም መሰረቱና አመጣጡ ከዚሁ መዝ. 22 ነው። መዝ. 22:1 ገና ሲጀምር “አምላኬ! አምላኬ! ለምን ተውከኝ? ለዕርዳታ በብርቱ በምጮህበት ጊዜ ስለምን ከእኔ እራቅህ?” በማለት በመራራ ስቃይ ውስጥ የሚገኘው ዘማሪ ጩኸቱን ደጋግሞ ያሰማል። በዚህም ጩኸት ውስጥ የሚታዩት ሰዎች ሁሉ እንደሚዘባበቱበት በንቀት ራሳቸውን እየነቀነቁ ከንፈራቸውን እንደሚያጣምሙበት በእግዚ ያብህሄ ተማምነህ አልነበረምን? ታዲያ ለምን አያድንህም? እግዚአብሔር የሚወድህ ከሆነ ለምን አይረዳህም እያሉ እንደሚያላግጡበት ምሬት በተሞላበት መንፈስ ይገልጻል (መዝ.22:1-8)። በተጨማሪም እጆቹንና እግሮቹን እንደቸነከሩት አጥንቶቹም እንደተቆጠሩ ልብሶቹምንም እንደተከፋፈሉ በእጀ ጠባቡም እጣ እንደታጣጣሉ በመግለጽ እግዚአብሔርን ከእርሱ እንዳይርቅና ፈጥኖ በመድረስ እንዲረዳው ሲማጸነው እናያልን(መዝ 22:12-18)። ይህንን መረር ያለ የእርዳታ ጩኸት ድምጽ ካሰማ በኃላ ግን ወዲያውኑ የምስጋና መዝሙር ይጀምራል። “የስምህን ታላቅነት ለወገኖቼ እናገራለሁ፤ እነርሱም በተሰበሰቡበት ስፍራ አመሰግንሃለሁ” በማለት እግዚአብሔር ድሆችን እንደማይንቅ ስቃያቸውንም ቸል እንደማይል፤ ከእነርሱም እንደማይርቅና ወደ እርሱ በሚጮህበት ጊዜ እንደሚሰማቸው አበክሮ ይገልጽልናል(መዝ 22: 22-31)። በአጠቃላይ መዝ 22 በሁለት ሃሳቦች ዙሪያ የተገነባና ሁለት ግልጽ የሆኑ ትልልቅ ክፍሎች ያሉት መዝሙር ነው።

 

  1. መዝ. 22:1-21 ለዕርዳታ በብርቱ የተደረገ የሐዘን ጩኸት
  2. መዝ. 22:22-23 የምስጋና መዝሙር ነው በብርቱ ስቃይ ውስጥ በመሆን ጩኸቱን ወደ እግዚአብሔር አሰምቶ የነበረው ስቃይና ወደ ምስጋና መዝሙር ተላልፎ ወዲያውኑ እግዚአብሔርን በብርቱ ሲያመሰግን ብቻ ሳይሆን መልካም ሥራ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት ስፍራ እንዲያመሰግን መጪው ትውልድ ሁሉ ሊያመሰግነው እንደሚገባ ከመናገሩም አልፎ ገና ላልተወለዱመ እንኳን እግዚአብሔር ሕዝቡን አዳነ ተበሎ እንደሚናገራቸው አበክሮ ይገልጻል። ይህ መዝ. 22 (የሐዘን ጩኸትና የምስጋና መዝሙር ከኢየሱስ መውለድ በፊት የነበርና እስራኤላውያን በጋራ የሚጸልዩት የማህበር መዝሙር ወይም የጋራ ጸሎት ሆኖ በማህበረሰቡ ውስጥ በደንብ የታወቀ መንፈሳዊ ዝማሬ ነበረ። በዚህም መዝሙር ውስጥ መሰቃየቱንና እስከሞት ላዛውም ተቸንክሮ መራራ ሞት እስከመጎንጨት ደራጃ ደርሶ መተውን የሚገልጸው ዘማሪ እንደ አንድ ግለሰብ ሳይሆን የመላው የእስራኤል ሕዝብ የመከራ ስቃይና የምስጋና ቃል ሆኖ የሚታወቅ ነው። ዘማሪው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ስለ ብዙሃኑ ስቃይና መከራን በመወከል ያቀረበው ስለሆነ በየጸሎት ቦታው መላው የእስራኤል ሕዝቦች አምልኮ ስር አታቸውን በመከተል ይዘምሩት ስለነበር አበዛኞች አማኞች በቃላቸው እንኳያውቁት እንደነበር ይገልጻል።በዚህ መዝሙር ውስጥ ግን የሚሰቃየው ግለሰቡም ሆነ ሕዝብ ምንም በደል ያልፈጸመ ንጹህ ወገን ከመሆኑም በላይ ከእግዚአብሔር ጋር እጅግ በጣም የቀረበ ወዳጅነት ያለውና በእግዚአብሔርም ተማምኖ ይኖር የነበረው ክፍል ነው። ለዚህም ነው”ከተወለድሁበት ጊዜ ጀምሮ በአንተ ተማምኛለሁ፤ ከእናቴ ማህጸን ጀምሮ  አምላክ ሆኖኛል። መከራ ሊደርስብኝ ስለተቃረበና የሚራዳኝም ስለሌለ እባክህ ከእኔ አትራቅ” በማለት ከእግዚአብሔር ጋር  ያለውን የጠበቀ ወዳጅነት በመግለጽ የሚማጸነው (መዝ 22:16-21**)። በሌል በኩል ከአንዳንድ የአይሁዳውያን የሃይማኖት ትምህርት መጽሐፍት እንደምንረዳው የአንድ መዝሙር መግቢያ የመጀመሪያውን ስንኝ በቃሉ በመደጋገም የጸለየ ሰው የመዝሙሩ ሙሉ ይዘት (ሙሉ ምዕራፍ) እንደጸለየ ይቆጠርለታል እንደነበርም ያስረዳሉ። ለዚህ ኢየሱስም በጊዜው በነበሩት አይሁዳውያን ጋር በየጸሎት ምኩራቦቻቸው ተገኝቶ ይጸልይና ያስተምርም ስለነበር (ሉቃ 4:16-20) ይህንን የመዝሙር ክፍል በቃሉ ሊያውቀው እንደሚችል ይታመናል።

በአጠቃላይ በአራቱም ወንጌላውያን የህማማት  ዜና በሚገልጸው የወንጌል ክፍላችን ማህበረሰባቸውን ለማስተማር መዝ 22ን ብሰፌው በመጥቀስ እንደተጠቀሙበት ግልጽ ነው። ይህም የጠቀማቸው ዋናው ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ወደ ሰዎች ዘንድ በመምጣት ዓለምን ያድናል የተባለው ኢየሱስ እንደ ተራ ወንጀለኛ በመስቀል የመንቸንከሩና የመዋረዱ ምስጢር ለብዙዎች መረዳትና አምኖ መቀበል አዳጋች ስለነበር ነው። ከእነዚህም ውስጥ አይሁዳውያን ይመጣል ተብሎ የተጠበቀው መሲህ የእግዝያብሄር ልጅ ከነገስታት ወገን የሆነው ከሮማውያን ይጭቆና ቀንበር ነጻ የሚያወጣውና መንግስቱም በዚህ ዓለም ለዘላለም የሚምሰረት ኅያል የሆነ መሲህ ይጠብቁ እንደነበር ይታወቃል።

በአጠቃላይ በአራቱም ወንጌላውያን የህማማት ዜና በሚገልጸው የወንጌል ክፍላችን ማህበረሰባቸውን ለማስተማር መዝ.22ን በሰፊው በመጥቀስ እንደተጠቀሙበት ግልጽ ነው። ይህም የጠቀማቸው ዋናው ምክንያት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ወደ ሰዎች ዘንድ በመምጣት ዓለምን ያድናል የተባለው ኢየሱስ እንደ ተራ ወንጀለኛ በመስቀል የመቸንከሩና የመዋረዱ ምስጢር ለብዙዎች መራዳትና አምኖ መቀበል አዳጋች ስለነበር ነው። ከእነዚህም ውስጥ አይሁዳውያን ይመጣል ተብሎ የተጠበቀው መሲህ የእግዚያበሄር ልጅ ከንገስታት ወገን የሆነው ከሮማውያን የጭቆና ቀንበር ነጻ የሚያወጣውና መንግስቱን በዚህ ዓለም ለዘለዓለም የሚመሰርት ኅያል የሆነ መሲህ ይጠበቁ እንደነበር ይታወቃል። ለእነዚህ አይሁዳውያን የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ በማለት የመሰከረው ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሚያሳዝን ሁኔታ በታላቅ ድምጽ ጮኸና አባቴ ካለው እግዚአብሔር ምንም አይነት የእርዳታ ምላሽ ሳያገኝ የመሞቱን ነገር ለመቀበልና በእውነት የእግዚአብሄር ልጅ ነው ብሎ ለማመን አስቸጋሪ ስለነበር ነው ወንጌላውያኑ ይኸውላችሁ እራሳችሁ መጽሀፉ ውስጥ ቅድሞውኑ መሲህ መሰቃይትና መሞት እንዳለበት ተነግሮ ነበር በማለት የመጽሀፍ ቃል እየጠቀሱ የሚገልጹት። አረማዊያን:- ለጣኦት አምላኪ አረማውያን የእግዚአብሄር ልጅ ነኝ ብሎ ሲያስተምርና ሲመሰክር የነበረው ኢየሱስ በቀላሉ በሰዎች እጅ ተዋርዶና ክብሩን ተገፎ እንደወንጀለኛ በሚስማር በደረቅ እንጨት ላይ ሕይወቱን አሳልፎ ሲያዩት በእውነትም የእግዚአብሄር ወይም በምድር ላይ ያለው የሰማያዊው ፈጣሪ ተወካይ በምንም መልኩ መሰቃየትም ሆነ መሞት የለበትም። በዚህም ምክንያት ወንጌላውያን ለአረማዊያን እንዲረዱት ኢየሱስ መሰቃየት እንደነበረበት ቀድሞ የተነገረ ነገር ያስረዷቸዋል።