የጾም ታሪካዊ አመጣጥ

የጾም ታሪካዊ አመጣጥ

የጾምን ታሪካዊ አመጣጥ ስንመለከት ደግሞ በመጀመሪያዎቹ ክፍለ ዘመናት ተጀምሮ በቋሚነት የረቡዕና የዓር ጾም ክርስቲያኖች ይጾሙ ነበር (ዲድስቅሊያ)።

በክርስትና ታሪክ የቤተክርስቲያንየጾም ሥርዓት (ልማድ) እንደየአካባቢው የተለያየ ባህልና አመለካከት ይዞ የመጣ ቢሆንም የጌታን ስቅለትና ሞት ለማስታወስ ሲባል በምዕራቡም ሆነ በምሥራቁ ዓለም የዓርብ ጾም ይተገበር ነበር።

በምዕራቡ ዓለም ወደ 400 ዓ.ም. አካባቢ አረቡዕ ዕርብ ጾም በቅዳሜ ጾም እንደተተካ ታሪክ ሲያስረዳ  የዐቢይ ጾምን ጨምሮ የታላላቅ በዓላት ዋዜማዎች በጾም ማሳለፍ ደግሞ ከጥንት ጀምሮ የመጣ ልምድ ነው። እናም የእስራኤላውያን ልማድን በመከተል ክርስቲያኖች ጾምን ይጾሙ የነበረው ከሁሉም የምግብ ዓይነት ጸሐይ እስከትጠልቅ ድረስ በመከልከ እና በማታ ጸሎት በማሳረግ ነበር።

በ9ኛው ክ.ዘ. የነበረውን የጾም አተገባበር ስንመለከት ደግሞ በሁሉም ክርስቲያን አገሮች እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ከምግብና ከውሃታቅበው በምዋል ነበር። ሆኖም ግን ከዕለት ሥራው ብዛት የተነሣ ሳይበሉ እስከዚያ ሰዓት ድረስ መቆየት ለብዙዎች አስቸጋሪ እንደነበር ግልጽ ነው።

በገዳማትም ቢሆን የነበሩት የጾምና ይተጋድሎ ጊዜያት በርከት ያሉ ሆነው በገዳማት ሕግና ቤ/ያን ሕግጋት የተቀመጡ አጽዋማት ይተገበሩ ነበር። በገዳሙ ትእዛዝ ብቻ ይየሚጾሙ ጾሞች በሚደረጉበት ዕለት በማታ ትንሽ መክሰስ ዳቦና የወይን ጠጅ እንዲቀምሱ ይፈቀድላቸው ነበር።

በምሥራቃዊቷ ቤ/ያን ያለውን የጾም ታሪካዊ አመጣጥ ስንመለከት ደግሞ ከመጀመሪያው ክ.ዘ. ጀምሮ ረቡዕና ዓርብ በግሪክ ቤ/ያን ምንም ዓይነት ምግብ አይበላበትም ነበር። ከጊዜ በኋላ ሌሎች ቀናቶችና ወቅቶች ተጨመሩ። የሁዳዴ ጾም የተጀምረው ከ2ኛው ክ.ዘ. ጀምሮ ነው። 4ኛው ክ.ዘ. ላይ ስለ የተቀደሱ 40 ቀናት ይነገር ነበር። ከዚሁ ከታላቁ (ዐቢይ) ጾም በተጨማሪ ሌሎች 3 የጾም ጊዜያት በምሥራቁ ዓለም ተለምደው ነበር። እነዚህም፦

  1. የሐዋርያት ጾም የሚባለው (ሰኔ ወር ውስጥ 2 ቀናት)
  2. የማርያም ጾም (ነሐሴ 1-14)
  3. የገና ጾም (ኅዳር 15-ታኅሣሥ 24) እ.ኤ.አ.

እነዚሁ 3ቱ ንኡሳን አጽዋማት እስከ 8ኛው ክ.ዘ. ግዴታዊ አልነበሩም። በምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት የአጾም ቀናት በተለያዩ ምክንያቶች እየተበራከቱ መጡ። እንዲያውም በግሪክ ቤ/ያን እስከ 180 ቀናት ያህል በዓመት ውስጥ ይጾም ነበር። የግብጽ መነኮሳት እንደ አባ እንጦንዮስ ጽምን ያሳልፉ የነበረው ትንሽ ዳቦ በውሃና በጨው በመመገብ ብቻ ነበር በምሥራቁ ዓለም ጾም በኣም በታላቅ ተጋድሎ ይጾም ነበር። በአንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ዛሬም ድረስ ቆሎን በደረቅ ምግብ ብቻ እየተመገቡ የማሳለፍ ልማድ ይታያል።