ጾም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ

Category: የተለያዩ አስተንትኖዎችና አስተምህሮዎች Written by Super User Hits: 3126

ጾም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ

በመጽሐፍ ቅዱሳዊ አገላለጽ ደግሞ ጾም ማለት ለእግዚአብሔር ክብር ሲባል ከምግብ ወይም ከውሃ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለተወሰነ ጊዜ በፈቃድ መከልከል (መታቀብ) 2ኛ ሳሙ.12፤17። እንዲሁም ነፍስን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ማድረግ እንደሆነ  ያስቀምጣል።

ጾም በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት

በብሉይ ኪዳን ዘመን በተለያዩ ጊዜያትና ምክንያቶች የሰው ልጆች በጾምና በጸሎት እግዚአብሔር አምላክን ይማጸኑ ነበር (1ሳሙ.7፤6 1ነገ.21፤9)። “ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፤ የአንድ ቀን ጾም አውጁ፤ ሕዝቡንም በአንድነት ሰብስቡ ለናቡቴም የክብር ቦታ ስጡት። በኀዘን ጊዜም እንዲሁ የሙሴ ሕግ የአንድ ቀን ብቻ ደንግጓል።  ሌዋ.16፤29-34 ከዚህ የሚከተሉትን መመሪያዎች በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ። ሰባተኛው ወር በገባ በአስረኛው ቀን እስራኤላውያንና በእነርሱ መካከል የሚኖሩ መጻተኞች ራሳቸውን ማዋረድ አለባቸው፤ በዚያ ቀን ምንም ሥራ አይሥሩበት። በዚያን ዕለት ንጹሖች እንድትሆኑ የኃጢአት ማስተሰረያ ይደረግላችኋል። ከዚያ ከኃጢአታችሁ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የነጻችሁ ትሆናላችሁ። ያም ዕለት እንደሰንበት የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ። በዚያም ቀን ራሳችሁን አዋርዱ ይህም የዘላለም ሥርዓት ነው። በአባቱ ምትክ ሊቀ ካህናት እንዲሆን ተለይቶ የሚሾመው ካህን የተቀደሰ የክህነት በፍታ ልብሱ ለብሶ ያስተሰርያል። እርሱም ለቅድስተ ቅዱሳኑ ለመገናኛው ድንኳን ለመሰዊያው ለካህናቱና ለጉባዔው ያስተሰርያል። በዓመት አንድ ጊዜ የእስራኤላውያንን ኃጢአት ሁሉ ማስተሰረያ የዘላለም ሥርዓት ይሆናል። ዘኁ.29፤7 ሰባተኛው ቀን በገባ በአስረኛው ቀን ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ በዚያን ቀን ምግብ አትመገቡም፤ ሥራም አትሠሩም።

ከባርነት ነጻ ከወጡ በኋላ አራት የጾም ቀናት ተጨመሩ (ዘካ.8፤19) የሠራዊት አምላክ እንዲህ አለኝ፦ በአራተኛው፣ በምስተኛው፣ በሰባተኛውና በአስረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።

ጾም በአዲስ ኪዳን ውስጥ

desertoለአዲስ ኪዳን ዘመንም ለክርስቲያን ወገኖች የጾም አስፈላጊነት፣ ጥቅምና ሥርዓትን በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ተገልጸው እናገኛቸዋለን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አገልጎት ከምጀመሩ አስቀድሞ በዮሐንስ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ወደ በረሃ ሄደ፤ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመ (ማቴ.4:)። በሌላ ስፍራ ደግሞ ኢየሱስ ራሱ ለደቀ መዛሙርቱ ስለጾም ሲያስተምር ጾም ለሰኦች ታይታ ተብሎ የሚፈጸም ሥርዓት ሳይሆን በስወር ከእግዚአብሔር አምላክ ጋር ብቻ የሚደረግ መንፈሳዊ ግንኙነት እንዲሆን በማስጠንቀቅ ጭምር ነው (ማቴ.6:16)።