እግዚአብሔር ፍቅር ነው

እግዚአብሔር ፍቅር ነው

ቅዱስ ዮሐንስ በመጀመሪያ መልእክቱ እውነተኛ ክርስቲያን ማን ነው? ለሚለው ጥያቄ መልስ ይፈልጋል፡፡ ለክርስቲያኖች ብዙ ልዩ ልዩ ምልክቶች ቀርበዋል፤ በፍቅርም ተሳስረዋል፡፡ ነገር ግን ፍቅር ምንድን ነው? በአንድ በኩል ከእኛ በጣም የላቀ በመሆኑ፣ ልናስብ ከምንችለው ባሻገር ነው፡፡ ዘወትርም ከእኛ በፊት ነው፡፡ የሚወድደንና ወደፊትም መውደዱን የሚቀጥል በመሆኑ መንፈስ ቅዱስን በማስከተል አንድያ ልጁን ኢየሱስን ላከልን፡፡ እራሱ እግዚአብሔርም ፍቅር ነው፡፡

አንድ “ኬርክጋርድ” የተባለ የሆላንድ ተወላጅ የሆነ ፈላስፋ እንዲህ በማለት የሰጠውን ቆንጆ አስተያየት አስታውሳለሁ፤ “እግዚአብሔር ሆይ ከመጀመሪያ ጀምሮ ወደኸናል፡፡ እኛን መጀመሪያ አንድ ጊዜ ብቻ የወደድኸን ይመስል እኛ ስለ አንተ እንናገራለን፡፡ ይሁን እንጂ፣ ዕለት በዕለት እስከ ሕይወታችን መጨረሻ ድረስ አንተ በቅድሚያ መውደዱን ትቀጥላለህ፡፡ በጠዋት ተነስቼ መንፈሴን ወደ አንተ ሳቀና የመጀመሪያው አፍቃሪዬ አንተ ነህ፣ በንጋት ተነስቼ ከሆነም ፈጥኜ መንፈሴን ወደ አንተ ሳቀናና ስጸልይ አንተ ትቀድመኛለህ፣ ሁል ጊዜ ቀድመህ የምትወደኝ አንተ ነህ፡፡ አሁንም ይኸው ነው፡፡ እኛም እናከብርሃለን፡፡ በመጀመሪያ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የወደድኸን ይመስል እንናገር ይሆናል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሕይወታችን ውስጥ ፍቅር ተጠናክሮ ይኖር ዘንድ እርስ በርሳችንም በፍቅር ተሳስረን እንገኝ ዘንድ ይጠይቀናል፤ ይህን ያስተማረን ፍቅር፤ ለእኛ ሲል እርሱ ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠን ስለሆነ፣ እኛ ደግሞ ለመንድሞቻችን ስንል ሕይወታችንን አሳልፈን መስጠት አለብን፡፡

በሥራና በእውነት እንጂ፣ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ፣ በፍቅርም እንደዚያው ነውና፡፡ ለእግዚአብሔር ስላለን ፍቅር ሳይሆን፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ለእኛ ስላለው ፍቅር ሲል ነው አንድያ ልጁን ልኮ ኃጢአታችንን ለማስወገድ መስዋዕት እንዲሆን ያደረገው፡፡ ፍቅር የምለውም ይህን ነው፡፡

ወዳጆች ሆይ እግዚብሔር እንደዚህ አድርጐ በጣም ስለወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን መዋደድ አለብን፡፡ እግዚአብሔርን ያየ  ማንም የለም፤ ነገር ግን እርስ በርሳችን ስንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ውሰጥ  ይኖራል፤ በእኛም ውስጥ ፍቅሩ ፍጹም ይሆናል፡፡ ቀድሞ የወደደን እርሱ ስለሆነ፣ እኛም እርሱን መውደድ አለብን፤ እርስ በርሳችንም እንደዚሁ መዋደድ ይረባናል፡፡ ማንም እግዚብሔርን እወዳለሁ የሚል ወንድሙን ግን የሚጠላ  ውሸታም ነው፤ የሚያየውን ወንድሙን የማይወድድ እግዚብሔርን አይወድድም፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ መሆኑን የሚያምንና አባቱንም የሚወድድ ልጁንም ይወድዳል፡፡ (1ኛ ዮሐ. 3፣16-18፤ 4፣ 1ዐ-12፣ 19-2ዐ፤ 5፣1-2)

 

ፍቅርና ሥርዓተ አምልኮ

ፍቅር በእግዚአብሔር ምስጢርና በሰዎች መካከል ይዘረጋል፡፡ ጥልቀቱና ዘለዓለማዊ የሆነው የሥራ ፍሬውም ትክክል ነው፡፡ በሰዎች ድርጊት እንዴት አድርጐ ወደዚህ እንደመጣ፣ ለሰው ደኅንነትና ፍላጐት እንዴት አድርጐ መልስ የሰጠውን፣ ታሪክ የመሰከረለትን፣ የምስጢራዊውና የፍሬያማውን ፍቅር መንገድ ማወቅ እንችል ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳን እንለምነዋለን፡፡

እኔ በእውነቱ የሃያኛውን ክፍለ ዘን ክርስቲያንነት መመርመር አልችልም፡፡ በጊዜያችን የፍቅርን አቀራረብ እንዴት መሆን የሚገባበትን መንገዶች ለመረዳት ጠቃሚዎች ናቸው ብዬ የማምንባቸውን በርካታ ሐሳቦችን ብቻ ማቅረብ እችላለሁ፡፡

የፍቅርን ጠቀሜታና መግለጫ፣ ይልቁንም፣ መንፈስ ቅዱስ በግልጽ የሚያሰምርበትን ሁለቱን ቦታዎች በማጣቀስ መጀመር እፈልጋለሁ፡፡

የመጀመሪያው ቦታ ሥርዓተ አምልኮ ነው፤ ይልቁንም፣ የቅዳሴ ሥርዓት የሚቀደስበት ነው፡፡ በእያንዳንዱ ትውልድ አማካይነት ሥርዓተ አምልኮ፣ ከጥልቅ ትርጉሙ ጋር የእግዚአብሔር ፍቅር ከክርስቲያኖች ጋር ነው ብሎ ይገልጥላቸዋል፤ ኢየሱስ እራሱ ሰዎችን ሁሉ በእግዚብሔር የፍቅር ምስጢር ውስጥ በአንድነት ይሰበስባቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ኀብስቱንና ወይኑን በቅዳሴ ጊዜ ወደ ኢየሱስ ሥጋና ደም ይለውጣቸዋል፤ ደግሞም ክርስቲያኖችን ሁሉ እንዲቀደሱ ወደ ክርስቶስ አካል እንዲለወጡ  ያደርጋቸዋል፡፡

ያም የእርሱን እውነተኛ መግለጫና ለሰው ስላለው ፍቅር ነው፡፡ ኢየሱስ ቁርባናዊ በሆነው አካሉና በቤተክርስቲያናዊ አካሉ መካከል ባለው ጠባብ ግንኙነት መንፈስ ይመራናል፡፡ ኢየሱስ በርኀራሄው በሚኖርበት ፍቅርና ፍቅሩም በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በሚኖርበት መካከል ይመራናል፡፡ የሥነ-መለኮታዊ ተግባር የመንፈስ ቅዱሰን አሠራር የምንከተልበትን መሣሪያነት ያቀርብልናል፡፡

በመስዋእተ ቅዳሴ ወቅት የሚታወጀውን ቃል፣ በስብከት ወቅት የተሰጠውን አስተያየት፣ በትምህርተ ክርስቶስ የተብራራውን፣ ለግላዊ አስተያየት የሰጠውን አደራና፣ በቡድን የሚደረገውን የእምነት ግንኙነት አስባለሁ፡፡ የሚነበበውን በትክክል ከተጠቀሙበት፣ ከተረዱትና ከወደዱት፣ ለተለመዱ ምሳሌዎች ከበለጸጉ ምንጮች ውስጥ በመሆን ያረካል፣ ያጠግባልም፣ ምክንያቱም በሚከበረው ሥርዓት ወደ ሕያው ፍቅር መለወጥ ይቻላልና፤ በቅዱስ ቅዳሴ ጊዜ አንዳንድ ጠቃሚ የሆኑ ወቅቶች በባሕርያቸው፣ በሥርዓተ አምልኮና በሕይወት መካከል የሚመሠረተውን ሁኔታ አስባለሁ፡፡

ለምሳሌ በምስጢረ ንስሐ ኃጢአታችንን በጥልቀት መርምረን ስንናዘዝ ፍቅሩን የሚቀንስ ሁኔታ ይወገድልናል፡፡ በክርስቲያኖች ጸሎት የቤተክርስቲያንና የዓለምን ችግሮች እንዴት መቋቋም እንደምንችል እንማራለን፡፡

የሰላም ልውውጥ የሚጋብዘን፣ በቅርብ ጐረቤታችን ጋር በሰላም እንድንኖር የሚያደርገን ሲሆን፣ ይህ በእኛ ምርጫ የተወሰነ ሳይሆን፣ በክርስቲያኖች ጉባኤ ጥሪ የተላለፈ ነው፡፡

በመደበኛ ዕለትም ሆነ በልዩ ጊዜ የሚደረግ መስዋዕትን መሰብሰብ፣ ከችግረኞች ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር አንድነትን እንድንመሠርት ያደርገናል፡፡

ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የምንነጋገርበት ሁለተኛው ቦታ በክርስቲያናዊ ቅድስና ታሪክ ውስጥ ስለ ፍቅር የነግረናለ፡፡ በመንፈስ ለመመራት ራሳቸው ስለፈቀዱትና ስለፈጸሙት ሥራ ወይም አንዳንዴ ሕይወታቸውን አሳልፈው ስለ መጣባቸው ለልዩ ተግባራት እንኳ አያኮራቸውም፤ ይለያያሉ፡፡ ሕይወታቸውንም በትሕትና ለእግዚአብሔር አደራ ይሰጣሉ፡፡ ነገር ግን በእርግጥ በእግዚአብሔር ውስጥ ስለሚኖሩ፣ ወደ እርሱም ልብ በጣም ስለሚቀርቡ፣ ትንቢታዊ ደግነትንና ለዓለም ፍላጐቶች፣ እንደዚሁም፣ ስለነዚሁ ጉዳዮች አንድ ነገር ስለሚያደርጉ ጀግንነት የተመላበት ጥንካሬ እንደሚያስፈልግ ይገነዘባሉ፡፡

ምንጭ፡ ጉዞ ከጌታ ጋር

በካርዲናል ካርሎ ማርያ ማርቲኒ

የቀድሞው የሚላኖ ሊቀ ጳጳስ