እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ክብሩን በብዛት አፈሰሰ - ቅዱሳን

ይህ ጽሑፍ ከእንግሊዘኛ ቋንቋ ወደ አማርኛ የተመለሰ ሲሆን የዋናውን ደራሲ ጽሑፍ በተቻለ መጠን ለማስተላለፍ ተሞኩራል፤ ስለዚህም በዚህ ሂደት ውስጥ አንዳንድ ሃሳቦች ይበልጥ ደራሲው የሚኖሩበትን አገር የሃይማኖቶች ግንኙነት የሚያመለክት ሆኖ ይታያል። ይህን ጽሑፍ በአማርኛ ስናቀርበው ለቅዱሳን የሚሰጥ ክብርን በሚመለከት ብዙ ጠቃሚ ነጥቦች ይኖሩታል ብለን በማመን ነው።

ክብሩን በእያንዳንዱ ሰው ላይና በዙሪያው ባሉት ነገሮች ላይ በብዛት አፈሰሰ - ቅዱሳን

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ቅዱሳንን ማለትም በሰማይ ያሉ የእግዚአብሔር ወዳጆችን ማክበርና መምሰል እንዳለባቸው በቂ ማስረጃ ያቀርባል፡፡ ቀጥሎ ያለው ጽሑፍ የሚያሳየን ክርስቲያኖች የእግዚአብሔርን ፈለግ በመከተል ለቅዱሳኖች ተገቢውን ክብርና ውዳሴ ሲሰጡ ነው፡፡ ስለዚህ ቅዱሳኖች እግዚአብሔር ራሱ ከሰጣቸው ክብር አሳንሶ /ዝቅ/ አድርጎ መመልከት የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡

ከዚህ በፊት ስለ ቅዱሳን ሱታፌ በጻፍኩት መጽሐፍ ይኸውም "ማንኛውም የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ የእኔም ወዳጅ ነው” (Any friend of God`s is a friend of mine) / San Diego: Basilica, 1996/ ውስጥ የተጠቀምኩት ከኘሮቴስታንቶች እንዲሁም ሌሎች ካቶሊክ ካልሆኑት ጋር ለምን ካቶሊኮች ለድንግል ማርያምና ለቅዱሳን ክብርና ልዩ ቦታ እንደ ሚሰጡ ለማሳየት በጣም ውጤታማ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ በዚሁ ውስጥ በካቶሊኮችና በኘሮቴስታንት መካከል ስለዚህ ጉዳይ ያለው ልዩነት በደንብ ተብራርቷል፡፡

ለምሳሌ አንተ አንድን ንጉሥ እየጎበኘኸው ነው እንበል ወደ ንጉሣዊ ዙፋን ስትዘልቅ ወዲያውኑ ደስ የሚል የሙዚቃ ድምጽ በአየር ውስጥ ሽው ሲል ትሰማለህ ወደ አንግዳ መቀበያው አዳራሽ ስትደርስ በምታየው ነገር ትደነቃለህ፡፡ ግድግዳውን ያስዋቡት የሚያማምሩ ስጋጃዎች፣የተለያዩ የእደ ጥበብ ውጤቶች፣ ወለሉን የሸፈኑት ውብ ምንጣፎች፣ በጣም ያስደምሙሃል፡፡ እንደዚሁም ወንዶችና ሴቶች በሚያምር ልብስ ተውበው ፊታቸው በደስታ በርቶና ግርማ ሞገስ ተላብሰው ታየለህ፡፡ እርምጃህን ወደፊት ስትጨምር ወደ ውስጠኛው ክፍል ማለትም ንጉሡ ወደ አለበት ትቃረባለህ። በዚህ ጊዜ የቤቱ ታላቅነትና ውበት እንዴት እንደጨመረ ሂደቱን ትረዳለህ፡፡ በመጨረሻም የንጉሡ ዙፋን ስር ደርሰህ ቀና በማለት ንጉሡን ፊት ለፊት ታየዋለህ። በዚህን ጊዜ ንጉሡ በቤቱ ውስጥ ካያሃቸው ከሚያማምሩና ከተዋቡ ሰዎች በአጠቃላይ በቆይታህ ቀልብህን ከገዙት ነገሮች በላይ የንጉሡ ታላቅነትና ውበት እጅግ በጣም ገዝፎ /ልቆ/ ታገኘዋለህ፡፡

የንጉሡን ልብስ፣ ዘውድ፣ የበትረ-መንግሥቱንና የዙፋኑን ውበት በማየት ትደነቃለህ፡፡ ነገር ግን የነዚህ ነገሮች ዋና ማዕከል ንጉሡ እራሱ ነው፡፡ አንተም በቆይታህ ይህ ንጉሥ ሐብቱና ፍቅሩን በዙሪያው ላሉ ነገሮች ውበት በብዛት እንዳዋለው  ትገነዘባለህ፡፡

አሁን ደግሞ ወደ አንድ ሌላ ንጉሥ ዙፋናዊ መኖሪያ ቤት እየገባህ ነው እንበል፡፡ በዚህኛው ጉብኝትህ ገና ከመጀመሪያው  ምንም ድምጽ የሚባል ነገር እንደሌለ ታስተውላለህ።እንደዚሁም ምንም የሙዚቃ ድምጽ አትሰማም፡፡ አይንን የሚማርኩ ሥጋጃዎች፣ምንጣፎች፣ የእደ-ጥበብ ዉጤቶች ጭራሹንም የሉም፡፡ ሰዎችንም በፍጹም አታይም /የሉም/።በአጠቃላይ በክብር ዙፋኑ በክፍሉ ጥግ ላይ ከተቀመጠው ንጉሥ ላይ ያለህን ትኩረት የሚረብሽህ ምንም ነገር በክፍሉ ውስጥ የለም፡፡

ለምንድ ነው ክፍሉ ጌጣጌጥና ባለሟል አልባ የሆነው? ምክንያቱም ይህ ንጉሥ ለክብሩ ቀናኢ ነው፡፡ አንተ አሱን ብቻ ከማየት ውጭ በሌሎች ነገሮች በፍጹም ሃሳብህና ትኩረትህ እንዲበታተን አይፈልግም፡፡ ከሁለቱ የትኛው ንጉሥ ነው የበለጠ ባለሞገስ በእርግጥ የመጀመሪያው ንጉሥ ነው፡፡ ሁለቱ ነገሥታት ሁለት የተለያዩ አመለካከቶችን ይወክላሉ፡፡ ይኸውም ካቶሊኮችና ኘሮቴስታንቶች እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ያለውን አመለካከት የሚረዱባቸው መንገዶችን ነው፡፡

የሁለተኛው ንጉሥ ምሳሌ የሚያመለክተው የኘሮቴስታንቶችን ግንዛቤ ነው፡፡ ይህ ንጉሥ ለአንድ አፍታ እንኳን ቢሆን ምንም ነገር ትኩረትህን እንዲሰርቅ አይፈቅድም፡፡ በእርግጥ ታላቅ ንጉሥ ነው፡፡ ግና ዙፋኑ የግብር ይውጣ ሥራና ዖና አይመስልምን? የመጀመሪያው ንጉሥ የሚያመለክተው ካቶሊኮች እግዚአብሔርንና እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ያለውን አመለካከት የሚረዱበት መንገድ ነው፡፡

እርሱ ራሱ ባለ ታላቅ ክብር ስለሆነ ክብሩን በእያንዳንዱ ሰው ላይና በዙሪያው ባሉት ነገሮች ላይ በብዛት አፈሰሰ።ለአፍታ ትኩረትህን በውብ ሥጋጃው ላይ ወይም የሚያምር ልብስ በለበሰው በወዳጁ /በባለሟሉ/ ላይ ታደርጋለህ ብሎ አይጨነቅም፡፡ በነዚህ ቁሶች የምታደርገው ነገር ለንጉሡ የበለጠ ክብርን ያጎናጽፈዋል፡፡ በዙሪያው ያሉትን ነገሮች የሚያፈካ ክብር በራሱ የንጉሡን ክብር ታላቅነት ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህ ክብር እንዚህ ነገሮች በኣጠቃላይ ትኩረታችንን በሞላ ወደ ንገሡእንደሚስቡ ያሳያል፡፡ የካቶሊኮች ዓይነት የቅዱሳን ሱታፌ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔርን ስለምንወደው የርሱን ወዳጆችንም እንወዳቸዋለን። ደግሞም እግዚ/ር እኛን ስለሚወደን የእርሱ ወዳጆችም /ቅዱሳን/ እኛን እንደሚወዱን በደንብ እናውቃለን፡፡ ይህንን በሚከተሉት ጥቅሶች የተደገፈ ምሳሌ ካቶሊክ ካልሆኑት ስተወያዩ እንድትጠቀሙበት እመክራለሁ፡፡ እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚያሳዩት እግዚአብሔር ለወዳጆቹ /ለቅዱሳን/ እኛ ማድረግ ከምንችለው በላይ ክብርንና ግርማን እንደሰጣቸው ነው፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር ይህንን ካደረገ እኛስ ለምንድ ነው የእርሱን ፈለግ የማንከተለው?

ቅድስት ድንግል ማርያምንና ቅዱሳንን ስናከብራቸውና ስናሞግሳቸው በትክክል እግዚአብሔር እራሱን ነው የምናከብረው ምክንያቱም የራሱን ፍጥረት ውበት እያወደስን ነውና፡፡

  • 1ኛ ቆሮ 11፡1 - “እኔ ክርስቶስን እንደመሰልኩ እናንተም እኔን ምሰሉ”
  • 1ኛ ቆሮ 12፡24—27 – “ክብር ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን ብልቶች እርስ በርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን፥ ለጎደለው ብልት የሚበልጥ ክብር እየሰጠ እግዚአብሔር አካልን አገጣጠመው።  አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል። እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ እያንዳንዳችሁም ብልቶች ናችሁ።”
  • ተጨማሪ ጥቅሶች ገላ 1፡24  ፊሊ 3፡17—2ዐ ተሰ 1፡6—7 ተሰሎ 1፡6—7

Source: Where is  that in the Bible? By Patrick Madrid - በአባ ተሻለ ንማኒ (ሲታዊ)

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት