ወርቃማው ሕግ

The-Golden-Ruleስለአንድ ነገር ጥልቅ ጥማት አድሮብህ ያውቃል? በልብህስ ሁሉንም ነገር የመጠቀም ዕርካታ የሌለው ምኞት ተሰምቶህ ያውቃል? ወይም በውስጥህ በማንነትህና በምትሠራው ሥራ እርካታ ማጣት ተሰምቶህ ይሆናል፡፡ እርካታ ሊሰጥ የሚችል እና ባሳለፍከው ሕይወት እንዳትቆጭ ሊያደርግ የሚችል የሕይወት አቅጣጫን ዘዴ መኖሩን ብታውቅ ደስተኛ ልትሆን ትችላለህ፡፡

በተለይ አንድ የወንጌል ሐረግ ቆም እንድንልና እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ትርጉሙንም በተረዳን ጊዜ በደስታ ይሞላናል፡፡ ይህ ቃል ጠቅለል አድርጐ በሕይወታችን ልናከናውነው የሚገባንና እግዚአብሔር በህሊናችን የፃፈውን ሕግ የሚገልጽ ነው፡፡

“ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሙሴ ሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው”

ይህ ሕግ ቀደም ብሎ የሚታወቅ ቢሆንም ኢየሱስ ያመጣልን ወርቃማ ሕግ ነው፡፡ ለምሳሌ የዕብራውያን ቅዱስ መጽሐፍ ይህንኑ ሕግ ይዞአል፡፡ የጥንቱ የሮማው ፈላስፋና ደራሲ ሴነካ ይህንኑ ያውቅ ነበር፡፡ በእስያም የቻይና ሊቅ ኮንፉሽየስ ይህንኑ አስተምሮአል፡፡ ይህም የሚያመለክተው ይህ መመሪያ ምን ያህል የእግዚአብሔር ዕቅድ እንደሆነና ሰዎች መሠረታዊ የሕይወት ሕግ እንዲያደርጉት እንደፈለገ ያሳያል፡፡

ይህ ጥቅስ አቀማመጡ እንደ መፈክር ዓይነት ስሜት ይሰጣል፡፡

“ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሙሴ ሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው”

ስለዚህ በቀኑ ውስጥ የምናገኘው ባልንጀራችንን እንዲህ አድርገን እንውደድ፡፡ እስቲ እራሳችንን በሌሎች ቦታ አድርገን በማሰብ በዚህ ቦታ ሆነን ሊያደርጉልን የምንፈልገውን ነገር እናድርግላቸው፡፡ በውስጣችን ያለው የእግዚአብሔር ድምፅ በየትኛውም ሁኔታ ምን ዓይነት ምላሽ መስጠት እንዳለብን ይነግረናል፡፡

እነርሱ ተርበዋል? “እኔ ተርቤአለሁ” እንበል ለእነርሱም የሚበላ ነገር እንስጣቸው፡፡ የፍትህ መጓደል ደርሶባቸዋል? እኔም ደርሶብኛል፡፡ በጥርጣሬ እና በጨለማ ውስጥ ናቸው? እኔም!

እነርሱ ብርሃን እስኪያገኙ እና እፎይታ እስኪያገኙ ድረስ የሚያፅናና ቃል መናገርና ችግራቸውን  መካፈል አለብን፡፡ እኛም ከሌሎች የምንጠብቀው ይሄ ነውና፡፡

ስለዚህ በሰዎች መሃከል ምንም አይነት ልዩነት ሳናደርግ ተመሳሳይ አቀራረብና ፍቅር ማሳየት እንቀጥል፡፡ ወንጌል ሁሉን ያጠቃልላልና፡፡ የሹክሹክታ ድምፅ ሰምቼ ልረዳ እችላለሁ፡፡ ምናአልባት የእኔ ቃላት ቀለል የሉ  ሊሆኑ ይችላሉ ግን እንዴት ያለ ለውጥ ይጠይቃሉ ከተለመደው አሰተሳሰባችንና አደራረጋችን ምን ያህል የራቁ ይሆኑ?

በርታ እንደገና ሞክር!

በዚህ ሁኔታ ያለፈ ቀን ከመላ ሕይወት ይበልጥ ዋጋ አለው፡፡ ማታ እራሳችንን እኔው? ነኝን ብለን እንጠይቅ ይሆናል፡፡ ከዚህ ቀደም ያልተሰማን ደስታ እና ያላገኘነውን ጥንካሬ እናገኛለን፡፡ እግዚአብሔር በፍቅር ከሚኖሩት ጋር ስለሚኖር እርሱ ከእኛ ጋር ይሆናል፡፡

ስኬታማ የሆኑ ቀናት ይቀጥላሉ …….

ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደገና እየቀዘቀዝን እንሄድ ይሆናል፤ ተስፋ እንድንቆርጥ፣ እንድናቆም እንፈተን ይሆናል፤ ወደቀድሞ አኗኗር መመለስ እንፈልግ ይሆናል፡፡ በተቃራኒው አይሆንም እንበርታ የእግዚአብሔር ጸጋ ከእኛ ጋር ነው፤ ሁልጊዜ አዲስ ሆነን እንጀምር፡፡ ጸንተን በመገኘት ቀሰ በቀስ ዓለም ስትለወጥ ማየት እንችላለን፡፡

ወንጌል ሕይወት ጣዕም ያለው እንዲሆን እንደሚያደርግ መረዳትም እንችላለን፡፡ የወንጌል ቃል ዓለምን ያበራል፣ ለመኖራችን ጣዕም ይሰጠዋል፣ የችግሮቻችን መፍቻ ስልት የያዘ ነው፡፡ የእኛን ልዩ የሕይወት ልምድ ለሌሎች እስካላካፈልን ድረስ ሙሉ እርካታ ሊኖረን አይችልም፡፡ ሊረዱን ለሚገባቸው ወዳጆቻችን፣ ወገኖቻችን፣ ማንም ይህ ሊደርሰው ለሚገባ ሁሉ ልምዳችንን ማካፈል ይኖርብናል፡፡

ተስፋ አሁንም እንደገና ይወለዳል!

“ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የሙሴ ሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው”

ምንጭ፡ ፍቅርና ሰላም መስከረም ፳፻፩ ዓ.ም.

የፎኮላሬ እንቅስቃሴ