እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

በሙዚቃ ውስጥ ሰይጣን?

በሙዚቃ ውስጥ ሰይጣን?

rock n rollበፈረንሳይ የሳይንስ ተቋም በሕክምናው ዘርፍ ለኖቤል ሽልማት የታጩት ሲሞን ሞራቢቶ የጣልያን ቁጥር አንድ የስነ አዕምሮ ምሁር ናቸው፡፡ ከሌሎች ነገሮች በተጓዳኝ "በሲኦል የአዕምሮ ሕክምና" የሚለው መጽሐፋቸው ሰይጣናዊው የሮክ ሙዚቃ በሰው ልጅ አዕምሮ ላይ ያለው ተጽዕኖ ይዳስሳሉ፡፡

ዶክተር ሞራቢቶ ከ3ዐ ዓመታት በላይ በእዕምሮ ሕክምና እና በውስጣዊ በሽታዎች ላይ የተለያዩ ምርምሮችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በርካታ ወጣቶች የእርሳቸውን ምክር እና የሕክምና ክትትል ይፈልጋሉ፡፡ አብዛኞቹ ወጣቶች ከጥቂት ጊዜ በፊት እጅግ በጣም ጐበዝ ተማሪዎች፣ ሠራተኞች ወዘተ... የነበሩ ቢሆኑም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን መንፈሳዊ እና አእምሯዊ ቀውስ የገጠማቸው ናቸው፡፡ በሥራቸው፣ በትምህርታቸው ባጠቃላይ በሕይወታቸው ደስተኞች አይደሉም፡፡ ቆራጥነታቸው ስለተሽመደመደ እውቀታቸው እንኳን እዚህ ግባ የማይባል ይሆናል፡፡ ከዚህ በመነሣት በነርቭ ችግር፣ ጭንቀት /ዱካክ/ በጨለምተኛ አስተሳሰቦች እና በዝቅተኛ የራስ መተማመን ስሜት መሰቃየት ይጀምራሉ፡፡ ድፍረት አጥተው ውሳኔ ለመወሰን ይቸገራሉ፣ ቶሎ ይደክማቸዋል፣ ይሰለቻሉ ስለዚህም በትምህርት ቤትም ይሁን በሥራ ገበታቸው ላይ የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን በአግባቡ ለመወጣት ይቸገራሉ፡፡ የዶክተር ሞራቢቶ ጥናታዊ ግኝት እንዳስቀመጠው የእነዚህ ሰዎች የሕይወት ቀውስ መነሾ በተደጋጋሚ ያለማቋረጥ በጭፈራ ቤቶች ጐራ ማለፋቸውና እና ያለማቋረጥ በከፍተኛ ድምፅ የሚዘፈኑትን ሰይጣናዊ ይዘት ያላቸውን የሮክ ሙዚቃዎች ማድመጣቸው ነው፡፡ዶክተር ሞራቢቶም ሙዚቃ የአድማጭን አስተሳሰብ አመለካከት እና ባህርይ ለመቅረፅ የሚችል መግባቢያ ነው ብለው ይሟገታሉ፡፡ ሙዚቃ በባህሪው የጉዳቱን መጠን እና የሚወክለውን ነገር በመሸፋፈን ለአእምሮአችን ውስጠኛ ክፍል አዳዲስ ሃሳቦችን ያቀርባል፡፡ ሰይጣናዊ ይዘት ያለው ፀረ ክርስትና ሙዚቃ ለጤናማ የሕይወት ዑደት በጣም አስፈላጊ የሆነውን ራስን ከክፉ ነገር የመጠበቅ ተፈጥሯዊ ስጦታን ያጠፋል፡፡ "የገሃነም ጐዳና"፣ "ከነውበት በውጣትነት መሞት"፣ "ራስህን አጥፋ" የመሳሰሉትን ዓይነት የዘፈን ግጥሞት ቀጥተኛ መልእክት አንድ ሰው ራሱን እንዲያጠፋ፣ እርሱነቱን አሳልፎ ለሰይጣን እና ለእርሱ አገልግሎት እንዲያውል በገሃድ ግብዣ ያቀርባል፡፡ ይህንን መሰል ሙዚቃ በሚያደምጡ ሰዎች ስነ ልቦና ውስጥ ሠፊውን ድርሻ ይዞ የሚገኘው ራስን የማጥፋት ሃሳብ ቢሆን የሚገርም አይደለም፡፡ "ለእኛ ለስነ አእምሮ ምሁራን፤ ሰይጣናዊ መልእክትን የሚሰብክ የሮክ ሙዚቃ፣ በቀስታ ቢሆንም ተግባሩን በስኬታማነት የሚደመድም አደገኛ መርዝ ነው፡፡ የሕክምና መጽሔታችን ዘገባ እንደሚጠቁመን፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአሜሪካ ብቻ 5ዐዐዐ ወጣቶች ውድ ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ ለእነዚሁ ወጣቶች ሕይወት መጥፋት ምክንያቶች አንዱ እና ዋነኛው ራስን ማጥፋትን የሚያስተጋባው ሰይጣናዊ የሮክ ሙዚቃ መሆኑን አረጋግጫለሁ"

ዶክተር ሞራቢቶ ቀጥለው እንዲህ ዓይነቱን ሙዚቃ ገዳይ ተፅዕኖ የሚተነትነው ሳይንሳዊ መግለጫ በሰው ልጅ ውስጠኛው የሕሊና ክፍል ውስጥ በግልጽ ሊቀመጥ ይገባል ይላሉ፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮው አንድን ሐሳብ ያለማስተዋል በጆሮው ሰምቶ ብቻ ከተቀበለው፣ ከጊዜ ብዛት አእምሮው ያንኑ ሃሳብ ከራሱ ማንነት፣ "ከእኔነት" እንደመነጨ ሃሳበ አድርጐ ይቀበለዋል፡፡ {jathumbnail off}

ሰይጣንም ይህንን የሥነ ልቦና አካሄድ ጠንቅቆ በማወቁ የተነሣ ከሰው ልጆች ቀድሞ ሐሳቡን በማቅረብ ከትክክለኛው መንገድ መጥተው ስሕተት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡ በመሠረቱ እያንዳንዱ ሰይጣናዊ ፈተና ወደ ውስጠኛው የአእምሮ ክፍል የሚቀርበው በከፍተኛ የማጭበርበር ሐሰተኛ ጥበብ ታጅቦ ነው፡፡ የሰው ልጅም ይህንን ማጭበርበር አምኖ ከተቀበለ ቀጣዩ ተግባር ኃጢአትን መለማመድ ይሆናል፤ በምላሹም የሰው ልጅ ሰብዓዊ መንፈስ ሰለሚፈራርስ ከእግዚአበሐር እና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን ጤናማ ግንኙነት ሁሉ ገደል ይገባል፡፡

አብዛኞቹ የሮክ ሙዚቃ ስልቶች የሰውን ልጅ ውስጣዊ የሕሊና ክፍል በማጥቃት ተፈጥሮውን ይመርዛሉ፤ እነዚህ ዘፈኖች አእምሮአችን የማይታወቁ ሃሳቦችን እና ስልተምቶችን በማጋጨት እና በማምታታት እንዲቀጥል ካደረጉት በኋላ "እኔ" ብሎ የሚጠራውን ማንነቱን እና ሕልውናውን ያጠፋሉ፡፡ የሰው ልጅ ነፃ ፍጡር ነው የሚባለውን አስተሳሰብ፣ የድርጊት፣ የፍላጐቶቹን እና የፍቅር ሰሜቶችን መግዛት የቻለ እንደሆነ ነው ሲሉ ዶክተር ሞራቢቶ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተቃራኒው በሰይጣናዊው የሮክ ውዚቃ ውስጥ የሚንቆረቆረው መልእክት የሰውን ልጅ ራስን የመግዛት ብቃት ቀስ በቀስ ሸርሽሮ በማጥፋት በዲያብሎስ ኃይል ስር ወድቆ በባርነት እንዲገዛ ያደርገዋል፡፡ ለምሳሌ ፡- Stairway to Heaven የሚለው ዘፈን ሰይጣን አምላክ ስለመሆኑ እና አዳኝም እንደሆነ ይናገራል፡፡ Hot summer night የሚለው ሌላኛው ዘፈን ደግሞ አንድ ሰው ሰይጣንን ለመከተል ያለውን ጉጉት ይገልፃሉ፡፡ ሰይጣን የሚባል ነገር የለም ብሎ የሚያምን ሰው ቢኖር እንኳን በእነዚህ ዘፈኖች ውስጥ የታጨቀው አፍራሽ መልእክት በሕሊናው የውስጠኛው ክፍል ተመዝግቦ ስለሚቀመጥ እግዚአብሔርን እና ሌሎችን ይጠላል፣ የነፍስ ግድያ ለመፈጸም ይነሣሣል፣ ልክ እንደ እንስሳት ከብር በሌለው መልኩ ወሲብ ይፈጽም ዘንድ ይገፋፋል፣ ሴተኛ አዳሪ ለመሆን ሌባ እና ወንበዴ ለመሆን አልያም ደግሞ ራሱን ስለማጥፋት ያስባል፡፡ ይህ ነገር የሚፈጸመው "ውኃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው" እንደሚባለው ነው፡፡

ዶክተር ሞራቢቶ የሕክምና ክትትል ከሚያደርጉላቸው ሕሙማን መካከል አንዲት ሴት ታካሚ በሕይወቷ በሰይጣት ተገዝታ እንድትኖር ካደረጓት አበይት ምክንያቶች አንዱ የዲስኮ ዳንስ ቤቶች /ቡና ቤቶች/ ደንበኛ መሆኗ እንደነበረ ምስክርነቷን ሰጥታለች፡፡ ይህቺ ሴት ከዚህ አስፈሪ የባርነት ቀንበር ነፃ ልትወጣ የቻለችው በቃላት ሊነገር ከማይችል ከባድ ሥቃይ በኋላ ነበር፡፡ እስከ መቶ የሚጠጉ የሰይጣን ማስለቀቂያ ጸሎቶች ተደርገውላታል፡፡ በዚሁ ጊዜ የማያቋርጥ የንስሐ ሕይወት፣ በየዕለቱ የጸሎት ሕይወት፣ በየዕለቱ ቅዳሴ በደስቀደስ እና ቅዱስ ቁርባን በመቀበል ከዚህ ቀንበር ልትገላገል ችላለች፡፡

rnrrየዚህ ሙዚቃ ደራሲያን የሰይጣን ባሪያዎች እና ተከታዮች መሆን ለአብዛኞቹ ወጣቶች ምሥጢር ከመሆኑም በላይ የሮክ ሙዚቃ ቡድኖች የሚጫወቷቸው የዘፈን ግጥሞች ሰይጣናዊ መሆናቸው እንቆቅልሽ ነው፡፡ ለነፍሳችን ተፈጥሯዊ እና መንፈሳዊ ሕይወት እጅግ አደገኛ ከሆነው የዚህ ሰይጣናዊ ግጥም አፍራሽ መልእክት ተጽዕኖ ባሻገር በየጭፈራ ቤቱ ቤተኛ የሚሆኑ ሰዎች ሰውነታቸውን እና አአምሯቸውን ለእንግልት ይዳረጋሉ፡፡ የጆሮ ታምቡር በሚያደነቁረው ከፍተኛ የሙዚቃ ድምፅ፣ በጨለማ ውስጥ የሚንቦገቦገው ከፍተኛ ደማቅና ዝብርቅርቅ መብራት፣ የተለያዩ አልኮል መጠጦች እና ጭሶች ሁሉ ተደማምረው የሰው ልጅ አካል እና አእምሮ እንዲዝል የደርጋሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ከአደንዛዥ ዕፅ ውስጥ የሚወጡ ጭሶች የአዕምሮን ሕዋሳት በማውደም ሊቀለበስ የማይችል አእምሯዊ ለውጥ ያስከትላሉ፡፡ ከዚህም ሁሉ በላይ እነዚህ ነገሮች በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የአድሬናሊን ሆርሞን በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር በማድረጋቸው ሳቢያ የሰው ልጆች የወሲብ ፍላጐት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀሰቀስ እና አስገድዶ መድፈርን የመሳሰሉ በኃይል የተሞሉ ጥፋቶች እንዲፈጽሙ በር ይከፍታል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ "ማንኛውንም ኃጢአት" እንድናስወግድ ያሳስበናል 1ኛ ተሰ. 5፡22፡፡ሰይጣናዊ ዘፈኖች እና እነዚህን ዘፈኖች የሚጋብዙን ጭፈራ ቤቶች በሙሉ በአንድ ክርስቲያን የሚታዩ ግልጽ ኃጢአቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም እነዚህን ሥራዎች ልብ ብለን ማድመጥ እና የሚደመጡባቸውን ስፍራዎች መጐብኘት ራስን ለኃጢአት እና ለዲያብሎስ ኃይላት በማጋለጥ አደጋ ውስጥ መግባት ነው፡፡

በጣም መንፈሳዊያን በሆኑ እና ልምድ ባላቸው ካህናት የሰይጣን ማስወጣት ጥረቶች ላይ ለበርካታ ጊዜ የታደሙት ዶክተር ሞራቢቶ ሁኔታውን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡- "በእርግጥም ሰይጣን በእውነተኛ መልኩ በምድር ላይ አለ፤ እርሱ የራሱ የሆኑ ምሥጢራት አሉት፤ ደግሞም እርሱ የሁሉም ጠላት ነው፡፡

በመሆኑም የትኛውንም ዓይነት የስነ አእምሮ ምርምር ወይም ሌላ ማንኛውነን ዓይነት ሳይንሳዊ ፅንሰ ሐሳብ ይህንን ሊክድ አይችልም፡፡ የሳይንስ ተመራማሪው ሆን ብሎ ለመካድ በመጥፎ ሃሳብ ካልተነሣሣ በቀር ሊክደው አይችልም፡፡ እስመ አልቦ ዘይመስላ ለእውነት /እውነትን የሚስላት የለም/ ምንም ቢሆን ሳይንስ በዓይን ለሚታየው እውነት ተገዢ መሆን አለበት፡፡ ሰይጣን መኖሩ እውነት ነው፤ እርሱ በዙሪያችን ይገኛል፤ ዘወትር ሰዎችን ወደ ስሕተት ይመራቸዋል፤ በኃጢአት ጊዜያዊ ደስታ ተታልለው ራሳቸውን አሳልፈው ለሚሰጡት በነፃነታቸው ፈንታ በኃይልና በባርነት ጠምዶ ይገዛቸዋል፡፡ መቼም ጊዜ ቢሆን በተቀደሰ ጸሎት ሰይጣን በማስወጣት ሂደት ውስጥ ሰይጣን የእርሱን ሕልውና በግልጽ እንዲያጋልጥ በክርስቶስ ኃይል ይገደዳል፡፡

ምንጭ፡- እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ካቶሊካዊ መጽሔት  ቁ. 4

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት