ቃሉን በትሕትናና በፍቅር መቀበል

ለዘለዓለም ፍጹም የምትወደጂ ማርያም ሆይ

እጅግ የተቀደሰች ቅድስት ማርያም ያለ አዳም በመፀነስዋ ከመጀመሪያው ጀምሮ በተሰጣት ጸጋ የተቀበለችው የሕይወት ክብር ምሳሌነትዋን ፍጹም በሆነ ምክንያት ለእኛ ታቀርባለች፤ እርሱም በታዛዥነት ኑሮ ለዘለዓለም ተገለጠ፤ ይህም የጸጋና የእግዚአብሔር ፍቅር ፍሬ ነው፡፡

ወንጌል እንደሚለው ማርያም ምልዕት ነች፡፡ በግሪክ ቋንቋ አባባሉ በቦዝ አንቀጽ የተገለጠ ነው፡፡ እርስዋ ቀድማ የተቀበለችው አድርጐ ያቀርበዋል፡፡ እንዲያውም ከዘመናት በፊት አድረጐ ነው፡፡ ስለዚህ እንደሚከተለው አድርገንም መተርጐም እንችላለን፡፡ “ማርያም ሆይ ከጥንት ጀምሮ የተወደድሽ ነሽ” ይህ ለዘለዓለም ፍጹም የተወደደች ነች የሚለው ነገር የማርያምን ክብር ይገልጣል፡፡

ዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልእክቱ የእግዚአብሔርን ዕቅድ ፍጹምነት ይነግረናል፤ እኛ ማርያምን አሰላስለን በምንገነዘብበት ጊዜ የእያንዳንዱን ሰው ክብር እናስባለን፡፡ እያንዳንዳችን የተፀነስንበትን፣ የተወለድንበትንም ክብር እናስባለን፡፡ ልክ በማርያም ላይ እንደተገለጡት ቃላት በእኛም ላይ ቃላቱ ተፈጻሚነት አላቸው፡፡ ፍጥረታት ሁሉ ለዘለዓለም የተወደድን ነን፤ ሁል ጊዜና ለዘወትርም በእግዚአብሔር ውስጥ ተወድደን የምንገኝ ነን፡፡ “በሰማይ መንፈሳዊ በረከትን በመስጠት በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ቅዱሳንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን በፊቱ እንድንገኝ ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ መረጠን ኤፌ. 1፡3-4

በዚህ ምስጢር የታየው የሰውን ልጅ ክብር፣ ጸጋ ስጦታንና መወደድን ነው፡፡ ለመወደድ ግን እንዲወደዱ ራስን መፍቀድ ማለት ነው፡፡ ስለዚህም ትሑት መሆንና የእግዚአብሔርን ቃል መስማትን ይመለከታል፡፡ ቃሉን በትሕትናና በፍቅር መቀበል፣ ልክ ቅድስት ድንግል ማርያም ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ፍጹምነትዋን በገለጸችለት መሠረት እያንዳንዳችን ሁል ጊዜ ስማችንን እየጠራ ዘወትር ይወድደናል፡፡ ልክ ቅድስት ድንግል ማርያም “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” ሉቃ.1፡38 አለችው፡፡ ስለዚህ የእኛ ክብር የሚመሠረተው እኛ በምናደርገው ትሕትና አማካይነት ይገለጣል፡፡

ማርያም የመጀመሪያዋ አማኝ መሆንዋ

እግዚአብሔር ከዚያ ጨለማና አሉታዊ በሆነው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ብርሃን ማምጣቱን የመጻሕፍት ጥቅሶች ይገልጣሉ፡፡

የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ አዳምን ፈርቶ ነበር የለዋል ዘፍ. 3፡1ዐ፡፡ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ፍርሃቶዎችን ቅዱሳን መጻሕፍት ይነግሩናል፡፡ ይህ ፍርሃት ከዚያ ቀጥሎ በተከታታይ ለመጡት ፍርሃቶች ሁሉ መሠረት ነው፡፡ ከውጪ በኩል ባጋጠመ ማስፈራራት ወይም ጠላት ወይም ከፍጥረት ድብቅነት የመጣ ፍርሃት አይደለም፡፡ ይልቁንም ከራስ ውስጥ የመጣ ነው፡፡ እኛ የራሳችን መስተዋል ነን፤ ጭንቀታችንን በመገንዘብ እገዚአብሔር ከእኛ ጋር እንዲሆን እንሻለን፡፡ እኛ እግዚአብሔርን እንፈራለን፡፡ ስለዚህ ስግስበው እኛ ራሳችን ከእበግዚአብሔር ርቀን እንገኛለን፡፡ ራሸችንን ከእግዚአብሔር መደበቅን እርሱን መክዳት ከእርሱም ጋር ሊኖረን የሚገባንን ሕይወት ደስተኛ እንዳይሆን እንፈልጋለን፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በላከው መልዕክቱ ለዚህ ፍርሃት መልስ ይሰጣል፤ የሰውን ሕይወት አዎንታዊና አንጸባራቂ ሁኔታውን እንድናስብ ይመክረናል፡፡ “ቅዱሳንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን እንድንገኝ ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ መረጠን፡፡” ኤፌ. 1፡4 እበግዚአብሔር መረጦናል፡፡ ቅድስ ጳውሎስ “እኛ” እያለ በመጀመሪያ ራሱን፣ ቀጥሎም ወንድሞቹን አይሁድን ከዘመናት በፊት በእግዚአብሔር የተመረጡትን የቃል ኪዳኑ መራሾችን መሆናቸውን ይጠቅሳል፡፡ ይልቁንም ቤተክርስቲያን ተወዳዳሪ የሌላት የቃል ኪዳኑኑ ልጃገረድ አድርጋ ትጠቅሳለች፤ ይህች የጽዮን ልጃገረድ ማርያም ናት፡፡ እርስዋ ከአማኞች መካከል የመጀመሪያይቱ ናት፤ እነዚህ ስለ ቅድስት ድንግል ማረያምና ስለ መለኮት የሚገልጡት ቅዱሳን መጻሕፍት ከሌሎች መጻሕፍት የበለጡ ጠቃሚ መጻሕፍት ናቸው፡፡ ማርያም “በእርሱ ፍቅር እንድትገኝ የተደረገች፣ ነቀፋ የሌለባት ለቅድስና መርጦ ያሳደጋት ልጃገረድ ናት፡፡” በመለኮታዊ መገለጥ የተገለጠው ይህንኑ ነው፡፡

እመቤታችን የእግዚአብሔር እናት፣ ቅድስትና ያለ አዳም ኃጢአት የተፀነሰች ብርሃናችንና እናታችን ናት፡፡ እርስዋ በዓለም እያንፀባረቀች በእርስዋ ኩራት የሚሰማው ሰው እንድንሆን ታደርጋለች፡፡ እኛ የእርስዋን ሕይወትና ተልዕኮ እንካፈላለን፡፡

ማርያም እንደዚህ ለመሰለው ለውስጣዊ ንጽሕና የተፈጠረች በመሆንዋ ከእንግዲህ ለሚያጋጥሙን የግብረ ገብ ውድቀቶችን ለመቋቋም በእግዚአብሔር ፊት በቅንነትና በትሕትና እግሰላስል ዘንድ ትረደናለች፡፡ አልፎ አልፎ በዚህ ዓለም ውስጥ ማንም ታማኝ፤ ማንም ቅን፣ ማንም ንጹሕ አይደለም በማለት ብንገደድና መራራነትና ብቸኝነት ቢሰማንም ነገር ግን ማርያም እያልን በመዘመር እርስዋ በፊታችን ስለምትገኝ ዘወትር መደሰት እንችላለን፡፡

የጌታ አገልጋይ

አጠቃላይ የብሥራቱን ታሪክ ማቅረብ አስቸጋሪ ስለሆነብኝ የታሪኩን መጨረሻ በግልጽ ቃላት ለማቅረብ ወስኛለሁ፡፡ ማረየም “እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ፣ አንተ እንዳልህ ይሁንልኝ” ሉቃ 1፡38 አለች፡፡

እነዚህ ቃላቶች ያለጥርጣሬ ግልጽ የሆነ ግንኙነት መኖሩን የረጋግጣሉ፡፡ ማርያም ከሌላ ጋር ግንኙነት ያላት መሆኑን በማመልከት ራስዋን አገልጋይ ብላ ትጠራለች፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ የአገልግሎት ግንኙነት ችግርን ያቀርባል፡፡ በግሪክ ድሌ የሚለው ቃል ግዳጅን ወይም አገልጋይነትን ያመለክታል፡፡ የሆነ ሆኖ በመንፈሳዊና በወንጌላዊ ይዘቱ “አገልጋይ” የሚለው ቃል ጥልቅና በጣም ልስልስ ያለ ፍች ያለው መሆኑን እናውቃለን፡፡

የማርያም ቃላት ከኢሳይያስ ቃላት ጋር ተመሣሣዮች ናቸው፡፡ እኔ የምደግመው የመረጥሁትና በእርሱም ደሰ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው ኢሳ. 42፡1

በእርግጥ እመቤታችን በነቢዩ ኢሳየያስ ንባብ ረክታ ነበር፤ የተነገሩ ትንቢቶችም በእያንዳንዱ የሰውነት ቃላቶችዋ ተሰራጭተው ነበር፡፡ የመጀመሪያው ክፍል ከድንግል ማርያም ንግግር ጋር ተመሣሣይነት እንዳለው እግያለን፡፡ “እኔ የጌታ ባሪያ ነኝ፡፡” የኢሳይያስ ሁለተኛው ምንባብ አጋማሽ ከመላኩ ቃል ተመሣሣይ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ “ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻል” ሉቀ. 1፡31

ማርያም ራስዋ እግዚአብሔርን ለይታ አውቃለች፣ ምክንያቱም እርሱ በእርስዋ ውስጥ ከእርስዋ ጋር የቀረበ የወዳጅነት ፍቅር ማድረግን ወሰነ፡፡

እንደዚሁም ሌላ ቆንጆ የሆነ ተመሣሣይነት ያለው ቃል እናገኛለን፣ “መንፈሴ በእርሱ እንዲበያድርበት አደርገዋለሁ” ኢሳ. 42፡1፡፡ መላኩ ለማርያም ካደረገላት ንግግርም ጋር ይመሳሰላል፤ ይኸውም “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል” ሉቃ. 1፡35

ማርያም መላከ የነገራትን ተቀብላ እንዲህ ብላ መለሰች፣ “እኔ የጌታዬ አገልጋይ ነኝ” በጸጋና በተልዕኮ ተመሣሣይ አባባል ውስጥ ነቢዩ ኢሳይያስ እንደተናገረው የያህዌን አገልጋይ ቅርጽ እናስቀምጣለን፡፡ በመንፈስ ቅዱስ እንድመላ እንደ ምስጢር አገልጋይ አድርጐ አስቀድሞ እግኪአበሔር የመረጣት እርስዋ አንድ ዓይነት ጥንቃቄ አላት፡፡ ይህ ጥንቃቄዋ የብቸኝነት ጥንቃቄ ግን አይደለም፤ ስለዚህ ስለሰዎች የሚደረግ ጥንቃቄ ነው እንጂ፡፡ ማርያም በምትወክላቸው ሰዎች ስም ትናገርበታለች፡፡ ይህም በነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እናገኛለን፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ (እዚህ ላይ አገልጋይ የተባለው ቃል የእሰራኤልን ሕዝብ ነው) የወዳጄ የአብርሃም ዘር የሆነው ያዕቆብን የመረጥሁ እኔ ነኝ፡፡ ነገር ግን አንተ አገልጋዬ እስራኤል ሆይ ሕዝቤ እንድትሆን የመረጥሁህ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ነህ፡፡ ከምድር ዳርቻ አመጣሁህ፣ በአራቱም ማዕዘናት ጠራሁህ፣ አገልጋዬ ትሆናለህ ብዬ መረጥሁህ እንጂ አልጠፋህም እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝ፤ ተስፋም አትቁረጥ፤ እኔ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነው ሥልጣኔም እደግፍሃለሁ” ኢሳ. 41፡ 8-1ዐ፡፡ እንደሁ መላኩ ማርያምን “እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው አትፍሪ” ሉቃ. 1፡29-31

በማርያም የሚወደዱ መሆናቸውን ከሚያውቁና የእግዚአብሔር ኃይል የማያቋርጥ መሆኑን እንዲያውቁ ከተመረጡና ከሚገነዘቡ ሰዎች ጋር በአንድነት ትኖራለች፡፡

በነቢዩ ኢሳይያሰ መጽሐፍ ውስጥ አንድ መንትያ ጥቅስ አለ፣ “የምታደግህ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሁ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፡፡ አንተ ነጻ ለማውጣት ግብፅን፣ ኢትዮጱያንና ሰባእን ቤዛ አድርጌ እሰጣለሁ”፡፡

የማርያም ነፍስ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የሰተጠች ናት፡፡ ማርያም የሕዝብዋን ነፍስ ድምፅ፣ የጥሪያቸውም መግለጫ ናት፡፡ በዚሁ ምክንያት ነው ለጌታ እንደ ብቸኛ የእስራኤል ድንግል፣ የጽዮን ልጃገረድ አድርጋ የምትመልሰው፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሰሜት ሳሻገር፣ ማርያም የሰው ልጅ በሙሉ ለደኅንነቱ ትጠነቀቃለች፡፡ “እኔ እግዚአብሔር አንተን ጠርቼሃለሁ፤ በምድር ላይ ፍትሕን ስታገኝ ዘንድ ኃይልን ሰጠሁህ፤ የዕውሮችን ዐይን ታበራለህ፣ በጨለማ ሥፍራ በግዞት የተቀመጡትን ነጻ ታወጣለህ፡፡ እጅህንም እይዝሃለሁ፤ እጠብቅህምአለሁ፡፡ በአንተ አማካይነት ከሕዘቦች ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ለሕዝብህም ሁሉ ብርሃን እንድታበራላቸው አደርግሃለሁ” ኢሳ. 53፡ 11-12

ማርያም በመጽሐፍ ቅዱስ ራእይ ማዕበል ላይ ትኖራለች፤ ይኸውም በመላኩ ቃላት አማካይነት በእርስዋ እንዳይፈጸም ተደረገ፡፡ ማርያም በሶስጽ ጥያቄዎች አማካይነት ማለትም የግል ሕይወትዋን ለእግዚአብሔር ሰጥታ የፍላጐት ነፀብራቅዋን በሙሉ ለሕዝቧ፣ ኃላፊነትዋን ወደ ደኅንነት አቅጣጫ በማተኮር ትኖርለች፡፡

ምንጭ፡ ጉዞ ከጌታ ጋር