እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

በፍቅር ማመን

በፍቅር ማመን

“እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፤ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡” /መዝሙር ዳዊት 145፡18/


Near to the heartየእግዚአብሔር ፍቅር ሁሉን አቀፋዊ ፍቅር ነው፤ ዓለምን በሙሉ በማፍቀር ከትንሽ እስከ ትልቅ ያሉት ፍጥረቶቹን ይመለከታል፡፡ ይህንን የሕይወት ቃል የሚይዘው መዝሙረ ዳዊት “ፍቅሩ ብዙ” የሆነው እግዚአብሔርን ለማወደስ የሚረዳን ዝማሬ ነው፡፡ ለፍጥረታት በሙሉ የሚያስፈልጋቸውን የሚያቀርብላቸው ፈጥኖ ደራሽ ነው፡፡

ሰው በጸሎት ሐሳብ ውስጥ በመሆን ምግብም ሆነ ለሕይወቱ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማግኘት ሁልጊዜ ጥያቄ ያቀርባል፡፡ ለዚህም የሰው ጥያቄ እግዚአብሔር የልግስና እጆቹን በመክፈት ለጥያቄአቸው መልስ ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ለሁሉም ይጠነቀቃል፤ ደካሞችን ይንከባከባል፤ “የወደቁትን ያነሣል” /መዝ. 145፡14/ እግዚአብሔር የጠፉትን ወደ እውነተኛ መንገድ ይመልሳቸዋል፡፡

“እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፤ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡” /መዝሙር ዳዊት 145፡18/

የእኛ እግዚአብሔር ቀሪ፤ የሩቅ ወይም ችላ የሚለን አምላክ አይደለም፤ ለሰው ልጆች በሙሉ ዕድል ፈንታው ነው፤ ብዙ ጊዜም አምላክ ለእኛ ቅርብ መሆኑን እናረጋግጣለን፤ አንዳንድ ጊዜ ግን እግዚአብሔር ከእኛ በጣም ሩቅ መሆኑ ይሰማናል፤ ብቸኝነት፤ ግራ መጋባት፣ በችግር ጊዜ ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታም ይሰማናል፡፡ እንዲሁም ከወንድሞቻችን ጋር ስንኖር አንዳንድ ጊዜ የጥላቻ መንፈስ እንዲሁም የዓመፅ ፍላጎት ሊያሸንፈን ይችላል፡፡ በቤታችንም ሆነ በሥራ ቦታ ትንሽም ሆነ ትልቅ ቂም ይዘን እንደሆነ ወይም ታማኝነታችንን በማጉደል ጓደኞቻችንን አሳልፈን በመስጠት፣ የቅናትና የምቀኝነት ስሜት እንዲሁም የመጨቆን ሁኔታ ካለ በዚህ ሁኔታ የተነሣ ልባችን ይደነድናል፡፡ በዓለም ታፍነን በጠብና በንዴት የቆየን፣ እንዲሁም በተለያዩ ምኞቶች የምንመራና ዓላማ፣ ፍትሕና ተስፋ የሌለን አድርገን እራሳችንን እንቆጥራለን፡፡

በዚህ ጊዜ “ጌታ ሆይ! የት ነህ?” በማለት ልባችን ይጮኻል፤ “በእውነቱ ትወደኛለህን?” በእውነቱ ትወደናለህን? ከወደድከንማ ለምን በዚህ ችግሮች ውስጥ ታስገባናለህ”

እንዲህ ተስፋችን መንምኖ ሳለ እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፤ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው የሚለው የሕይወት ቃል በፍጹም በሕይወታችን ጉዞ ውስጥ ብቻችንን እንዳልሆንን ያረጋግጥልናል፡፡

“እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፤ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡” /መዝሙር ዳዊት 145፡18/

እነዚህ ቃላት እምነታችን ሕያው እንዲሆን ይጋብዙናል፤ እግዚአብሔር አለ፤ ይወደኛል፤ ለዚህም ደግሞ በማንኛውም ተግባሩን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ማረጋገጫ አለኝ፡፡ እግዚአብሔር ይወደኛል፤ ለምሳሌ ከሰው ጋር እንገኛለን በዚህ ጊዜ በእርሷ ወይም በእርሱ በኩል እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊግረኝ እንደሚፈልግ አምናለሁ፡፡ በሥራ ተወጥሬያለሁ ቢሆንም በዚያን ወቅት በፍቅሩ እምነት መኖሬን እቀጥልበታለሁ፡፡ ስቃይ እንኳን ቢመጣብኝ እግዚአብሔር እኔን መውደዱን ማመኔን አላቋርጥም፡፡ የደስታ ቀን ቀርቦ ይሆን? እግዚአብሔር አሁን አሁንም ይወደኛል፡፡

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ስለእኔ ሁሉን ነገር ያውቃል፤ ያለኝን ሐሳብ ሁሉ ይካፈልልኛል፤ ደስታና ምኞትን በሕይወቴ ውስጥ እያፈራ ጭንቀትን ችግሮችን ሁሉ ከእኔ ጋር ሆኖ ይሸከምልኛል፡፡

“እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፤ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው፡፡” /መዝሙር ዳዊት 145፡18/

በእኛ ውስጥ ያለውን እምነታችንን እንዴት ልናሳድስ እንችላለን? ከዚህ ቀጥሎ ጠቃሚ የሆኑ ሐሳቦች ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ሐሳቦች እግዚአብሔርን እንዴት ልንጠራው እንደሚገባን ይነግሩናል፤ ጴጥሮስና ሌሎች ደቀመዛሙርት ውሃ ላይ በጀልባ እየሄዱ ኃይለኛ ማዕበል ሲነሣ ጌታ ተኝቶ ስለነበረ ብቻቸውን መሆናቸውን አስበው በድንጋጤ ጌታ ሆይ አድነን እያሉ ጮኹ፡፡ /ማቴ 8፡25/ ጌታም ማዕበሉን ፀጥ አደረገው፡፡

ኢየሱስ ራሱ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት አባቱ ለእርሱ የነበረው ቅርበት አልተሰማውም፤ ነገር ግን ጭንቀት በተሞላበት ጸሎት “አምላኬ ሆይ! አምላኬ ሆይ! ለምን ተውከኝ?” እያለ ጮኸ፡፡ ማቴ 27፡46 በአባቱ ፍቅር መተማመኑንም ቀጠለ፤ መላ ሕይወቱን ለአባቱ አደራ ሰጠው፤ አብም ከሞት አስነሳው፡፡

እርሱ በእኛ ውስጥ መገኘቱን በመገንዘብ እምነታችንን የምናድሰው እንዴት ነው?

በመካከላችን እርሱን በመፈለግ “ሁለት ወይም ሦስት ሆናችሁ በስሜ ብትለምኑኝ እኔ በመካከላችሁ እገኛለሁ” በማለት ቃል ስለገባልን በዚህ ሁኔታ እምነታችንን ሕያው ልናደርገው እንችላለን፡፡ ማቴ 18፡20 የጋራ በሆነው በወንጌል ፍቅር በዚህ በሕይወት ቃል መኖሩን እና ብርታቱን እንዴት በተግባር ልንፈጽመው እንችላለን? ፍሬውንስ እንዴት ልናየው እንችላለን?

ጌታ በሁላችን ውስጥ ይኖራል፤ እኛም ይህንን አውቀን ወደ እርሱ በመጠጋት ሁልጊዜ ከእርሱ ጋር እንሥራ፡፡

የፎኮላሬ እንቅስቃሴ

አባ ጳውሎስ አንቤበን

 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት