እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!

ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሚናገረው ይህ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ካቶሊካዎት ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊ መገናኛ መምሪያ ቢሮ በየወሩ ከሚታተመው "ፍቅርና ሰላም" ከተሰኘው ጋዜጣ ግንቦት/ሰኔ 2001 ዓ.ም. እትም "የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!" ከሚል ርእስ በከፊል የተወሰደ ነው።

"የሰማይ ንግሥት ሆይ ለምኝልን!"

በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ላይ የተገለጸው የመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ብሥራት የሚተርከው ማርያም የልዑል እግዚአብሔርን ልጅ እንደምትወልድና እርሱም በብሉይ ኪዳን ስለ መሲሑና ዘላለማዊ መንግሥቱ  ተነግሮ የነበረው ተስፋ እንዲፈጸም እንደሚያደርግ ነው። (2ሳሙ.7:፤ መዝ.2:72፣89፤ ሉቃ.1:33)።

እመቤታችን ቅ.ድንግል ማርያም ንግሥተ ሰማይ

ጥንታዊ አይሁዳውያን አንዲት እናት ከዳዊት ዘር የሆነና ወደፊት በንጉሡ ዙፋን ላይ ሊቀመጥ የሚችል (አልጋ ወራሽን) የወለደች እንደሆነ ወዲያውኑ ንግሥት እንደሆነች አድርገው ይቀበሏታል። ማርያምም በብሥራቱ ጊዜ የተቀዳጀችው ይህንኑ አክሊል ነበር። እርሷ ባባቱ በዳዊት ዙፋን የሚቀምጥና ለመንግሥቱም ማለቂያ የሌለውን ኢየሱስን ጸንሳለችና።

የቅድስት ድንግል ማርያም የእናት ንግሥትነት ማዕረግ የበለጠ ጉልህ ሆኖ የሚታየው ደግሞ በ ሉቃ.1:43 ላይ ነው። ይህም ቅድስት ኤልሳቤጥ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማች ጊዜ የመሰከረችው ነው። "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል!"። ይህ የኤልሳቤጥ "የጌታዬ እናት" የሚለው አባባል የመነጨው በጥንት ጊዜ በንጉሡ ሸንጎ ፊት "ጌታዬ ሆይ!" ማለት "ንጉሥ ሆይ!" እንደማለት የነበረ በመሆኑ ነው። "የጌታዬ እናት" ማለቷ ኤልሳቤጥ የንጉሡ እናት ንግሥቲቱ ቤቷ ድረስ መምጣቷ አስገርሟትም አስደንግጧትም ጭምር ነው። በንግሥት መጎብኘት ያውም እቤት ድረስ መጥታ ያስደንግጣልና ነው። በመሆኑም ኤልሳቤጥ የማርያምን ልዕልና የተረዳችና የመሰከረች ሰው ናት።

ሌላው ቢዚህ የማርያም ንግሥትነት ላይ ብርሃን የሚፈነጥቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ደግሞ ራዕይ 12:1-2 ነው። "ታላቅ ምልክት በሰማይ ታየ ፤ ፀሐይን ተጎናጽፋ ጨረቃ ከእግሮቿ በታች ያላት በራስውም ላይ የአስራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ጸንሳ ነበር።"

ይህች ሴት ማናት? አንዳንዶች እስራኤልን ወይም ቤተ ክርስቲያንን የምትወክል ሴት ናት ይላሉ። ነገር ግን ይኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በ12:5 ላይ ይህች ሴት የመሲሑ እናት እንደሆነች ይገልጻል። "አሕዛብን ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋን ተነጠቀ።" ስለዚህ ይህ "አሕዛብን ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለው" ተብሎ የተገለጸለት ንጉሥ ማነው? ንጉሡ ኢየሱስ ነው። ሴቲቱ ደግሞ እናት ንግሥቲቱ እምነ ማርያም ናት።

ድስት ድንግል ማርያም በዮሐንስ ራዕይ ላይ የተገጸችው በሰማያት እንደተቀመጠች ንግሥት ነው። በደፋችው ዘውድ ላይ 12 ከዋክብት ከ12ቱ የእስራኤል ንገዶች በተወለደችው በ12ቱ ሐዋርያት ላይ በታነጸችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ያላትን የንግሥትነትን ማዕረግ ይገልጻሉ። ፀሐይን መልበሷ ደግሞ የእግዚአብሔር ክብር በርሷ እንደሚገለጽ ያስረዳል። ጨረቃን ከእግሮቿ በታች ማድረጓ የንግሥትነት ሥልጣኗን ይገልጻል (መዝ.8:6፤ 110:1)።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዛሬም በእግዚአብሔር መንግሥት የምእመናን ጠበቃ ሆና ታገለግላለች። በልጇ ዙፋን ፊትም የኛን ጸሎታና ለመና በማቅረብ ጎልህ ሚና የምትጫወት ጽኑ አማላጅ ናት። ጸሎታችንን ይዘን "አያሳፍርሽምና" በሚል መተማመን ወደ መንበሯ እንቅረብ። ኢየሱስም ሰሎሞን ለቤርሳቤህ እንደመለሰላት "እናቴ ሆይ! አላሳ{jcomments on}ፍርሽምና ለምኚ" በሚል ማረጋገጫ ቃል ሰሎታችንን ከአንደበቷ ይቀበላል(1ነገ.2:20)።


 

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት