እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት መንፈሳዊ ትምህርቶች፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ ታሪክ፣ ሥርዓተ አምልኮ፣ ጸሎቶችና መንፈሳዊነትን ወደ ምንካፈልበት፤ የቤተ ክርስቲያናችን ዜና ወደ ሚነገርበት፣ እንዲሁም በተቀደሰ ጋብቻም ሆነ በምንኩስና ሕይወት ወደ ቅድስና ጥሪ ለመጓዝ የሚያግዙ እውነታዎች ወደሚጋሩበት፣ የቅዱሳን ሕይወት፣ ሀብትና ትሩፋት ወደ ሚነገርበት፣ ባጠቃላይ የአምላካችን መልካም ዜና ወደሚታወጅበት ይህ ድረ ገጽ እንኳን በደህና መጡ!!

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

17 - የመሰቃየት ዋጋ

17 - የመሰቃየት ዋጋየእግዚአብሔር ቃል፤ ሮሜ 8፡ 31-35፣ 37-39

Mariamእናታችን ማርያም፣ በመስቀሉ ሥር በመቆም፣ ለመልአኩ በሰጠች ቃል መሠረት ተልዕኮዋን እየፈጸመች ነበር፤ ‹‹እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ አንተ እነዳልህ ይሁንልኝ›› ኤልሳቤጥ፣ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ፣ ለእናታችን ማርያም ሰላምታ መልስ ስትሰጥ ‹‹አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ፤ ከአንቺ የሚወለደውም ልጅ የተባረከ ነው›› አለቻት፡፡ በነዚህ በሁለቱ የእናታችን ማርያምና የኢየሱስ ቡራኬዎች፣ ኤልሳቤጥ በድንግል ማርያምና በኢየሱስ ተልእኮ መካከል ያለውን ጥብቅ ትስስር ትገልጻለች፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አንድን ሰው በሚባርክበት ጊዜ ለዛ ሰው የሚያስፈልገውን ፀጋና ኃይል የሚሰጠው የእርሱን የማዳን ተልእኮውን ለመፈጸም ነው፡፤ በተባረኩ ሰዎች ትብብር አማካይነት እግዚአብሔር አዳኝ ነው፡፡ አብርሃምና ዮዲት የተባረኩ ናቸው ምክንያቱም ለሕዝቡ የመዳን ሥራ ከእግዚአብሐር ጋር ተባብረዋል፡፡

ዘፍጥረት 14፡ 19-20 ዮዲት 13፡ 18 ሉቃስ 1፡ 42

ሰማይንና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብርሃምን ይባርክ ልጄ ሆይ፣ በዓለም ላይ ካሉት ሴቶች ይበልጥ በታላቁ አምላክ የተባረክሽ ሁኚ፡፡ አንቺ ከሴቶች ሁሉ የተባረክሽ ነሽ፡፡

በጠላቶችህ ላይ ድልን ያደዳጀህ ልዑል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡ ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የጠላቶቻችንን አለቃ አንገት ለመቀንጠስ የመራሽ እግዚአብሔር አምላክ የተባረከ ይሁን፡፡ ከአንቺ የሚወለደውም ልጅ የተባረከ ነው፡፡

በሉቃስ ቅድስት ማርያም ከማሕፃኗ ፍሬ ጋር ተባረከች ነበረች፡፡ ይህም ማለት በሉቃስና በጥንት ክርስቲያኖች እምነት፣ በደህንነት ታሪክ ውስጥ እናታችን ማረያም ከልጇ ጋር በጥብቅ እየተባበረች ነበር፡፡

እመቤታችን ማርያም ራሷን ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን በሙላት ሰጥታለች፡፡ በተለይም በመስቀል ሥር ከልጇ ጋር ተሰቃይታለች፣ እንዲሁም ለእኛ ደህንነት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማለች፡፡ እናታችን ማርያም ለእግዚአብሔር በመታዘዝ እስከ መጨረሻ እዚያ ነበረች፡፡ የኢየሱስ መስቃየትና መሰጠት ለማርያም መሰቃየት ዋጋ ሰጥቶአል እና የእናታችን ታዛዥነት የሞላበት መሰጠት በክርስቶስ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር አብ ደርሶአል፡፡ እርሷ የቅዱስ ጳውሎስን ቃላት መድገም ትችላለች፤ ‹‹ ›› (ቆላ 1፡ 24)፡፡

ብዙ ጊዜ መሰቃየትንና ሕመምን ለቤተሰቦቻችን እንደ አሉታዊ የሕይወት ልምድ እናያለን፡፡ እንደ ክርስቲያን የችግርን ጊዜ አዎንታዊ ዋጋ ለመስጠት መሞክር አለብን፡፡ በሰብአዊነት፣ የኢየስስ ሞት ለክርስቶስና ለእናቱም በጣም አስደንጋጭ ጊዜና ኢ-ፍትሐዊ ነበረ፡፡ ነገር ግን የክርስቶስ ፍቅር ይህን ኢ-ፍታዊነት በመለወጥ እንዲሁም ስለእኛ ሕይወቱን አሳልፎ መስጠቱ ለእኛ ሕይወትን አስገኘ፡፡ የእኛ ሥቃዮች፣ ድህነት፣ የኢ-ፍትሐዊነትና የበሽታ ውጤቶች ሲሆኑ ሁልጊዜ አሰቃቂ የሕይወት ልምዶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ከክርሰቶስ መስቀል ጋር ከቀረቡና የሕይወት ልምዶች ናቸው፡፡ ነገር ግን ከክርስቶስ መስቀል ጋር ከቀረቡና ከተገናኙ፣ ለዓለም መልካምነት ትልቅ ሀብት ይሆናሉ፡፡ እናታችን ድንግል ማርያም ምሳሌ ሰጥታናለች፡፡ በሕይወታችን ከባድ ችግር በሚደርስበት ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መማረር እንጀምራለን፡፡ ለክርስቶስም እንደነበረ ሁሉ ችግር ሁል ጊዜ የሚያምን /የሚያሰቃይ/ ነው፡፡ መጸለይን እንማር፤ ‹‹አባት ሆይ በልጅህ ሞት ንጹህ መሥዋዕት እንዳደረግህ የሕይወቴን መሥዋዕት ተቀበል››፡፡ በቁምስና ውስጥ ብዙ እንቅስቃሴዎች አሉ፡፡ በአካባቢያችን ያሉ ሰዎች በራሳቸው ጉዳይ የተጠመዱ ናቸው፡፡ የማያገለግል፣ በጣም የታመመ ሰው ምን ሊያደርግ ይደችላል? እርሱ እስከ አሁን ጥቅም የሌለው ነው? እርሱ ለዓለም ሸክም ይሆናል፤ ነገር ግን ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ፣ ምንም ማድረግ ባልቻለ ጊዜ፣ ዓለምን እንዳዳነ እናውቃለን፡፡ እርሱ ሥቃዩንና ሞቱን ብቻ ለአባቱ ማቅረብ ይችል ነበር፤ ‹‹አባት ሆይ ነፍሴን በእጆችህ አስረክባለሁ››፡፡

በበሽታ፣ በጭንቅ፣ በሐዘንና በከፍተኛ ሥቃይ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች በሚያደርጉት መስዋዕትነትና ጸሎት ሐዋርዊ ሥራችን ፍሬ ሊያፈራና የሰዎችን ልብ ሊውጥ ይችላል፡፡

በቁምስናና በቤተ ክርስትያናችን ውስጥ ጸሎታቸውንና ሥቃያቸውን በጸጥታ የሚያቀርቡ ሰዎች ለሰላምላም፣ ለለውጥና ለተሻለ ዓለም ዋና ሥራ ይሰራሉ፡፡ በሉርድና በፋጡማ የተገለጸች እናታችን ማርያም በግልጠቷ ጸሎትንና ሥቃይን ለሰላምና ለኃጢአተኞች መለወጥ እንዲቀርብ ሁል ጊዜ ትጠይቅ ነበር፡፡

እንጸልይ፡-

አባት ሆይ፤ እኛ ከእናታችን ማርያም ጋር፣ ሕይወታችንን ደስታችንን፣ ተሰፋችንና ሥቃያችን በሙሉ እናቀርባለን፡፡ የልጅህን ንጹሕ መስዋዕት እንደተቀበልክ የእኛንም የሕይወታችንን መሥዋዕት ተቀበል ብለን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             https://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት