16 - ማርያም በኢየሱስ መስቀል አጠገብ ቆማለች
- Category: ከእመቤታችን ማርያም ጋር መጸለይ
- Published: Tuesday, 19 October 2010 17:52
- Written by Super User
- Hits: 6077
- 19 Oct
16 - ማርያም በኢየሱስ መስቀል አጠገብ ቆማለች
የእግዚአብሔር ቃል:- ዮሐንስ 19፡ 24-30
24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው። ለማን እንዲሆን በእርሱ ዕጣ እንጣጣልበት እንጂ አንቅደደው ተባባሉ። ይህም። ልብሴን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ በእጀ ጠባቤም ዕጣ ተጣጣሉበት የሚለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። 25 ጭፍሮችም እንዲህ አደረጉ። ነገር ግን በኢየሱስ መስቀል አጠገብ እናቱ፥ የእናቱም እኅት፥ የቀለዮጳም ሚስት ማርያም፥ መግደላዊትም ማርያም ቆመው ነበር። 26 ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን። አንቺ ሴት፥ እነሆ ልጅሽ አላት። 27 ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት። 28 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ። ተጠማሁ አለ። 29 በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት። 30 ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።
በኢየሱስ መስቀል አጠገብ የቆመች ችናታችን ማርያም የሰማችው፤
- ኢየሱስ ሲናገር ‹‹አንቺ ሴት እነሆ ልጅሽ፡፡ ይህችውልህ እናትህ››
- ኢየሱስ ለወንጀለኛው የሰጠው መልስ፤ ‹‹በእውነት እልሃለሁ፤ ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ!››
- የኢየሱስ ጩኸት ‹‹አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? አባት ሆይ እነሆ ነፍሴን በእጅህ አስረክባለሁ››
- ‹‹ጠማኝ››
- ‹‹ተፈጸመ››
- የመጨረሻ የልጇ ጩኸት፤ ‹‹አየሱስ እንደገና በታላቅ ድምፅ ጮኸና ሞተ››፡፡ ከወታደሮቹ አንዱ የኢየሱስን ጎን በጦር ሲወጋውና ወዲያውኑ ከጎኑ ደምና ውሃ ሲወጣ እመቤታችን ማርያም አይታለች፡፡
- በዚያው ምሽት እናታችን ማርያም፣ ከአርማትያሱ ዮሴፈ፣ ከኒቆዲሞስ፣ ከሚወደው ደቀ መዝሙርና ከአንዳንድ ሴቶች ጋር በመሆን፣ የኢየሱስን አስከሬን ከመስቀል አወረዱትና እንደ ወንጀለኛ እየተጣደፉ ቀበሩት፡፡
- ቅድስ ድንግል ማርያም፣ የተመረጠች፣ በእግዚአብሔር የተወደደች፣ ፀጋን የተሞላች፣ ከሴቶች ሁሉ መካከል የተባረከች፣ የእግዚአብሔር እናት፣ እነዚህን ሁሉ ሥቃዮችና መጥፎ ገጠመኞች እያንዳንዱ ቤተሰብ የሚያሳልፋቸውን አሳልፋለች፡፡ እንደ እግዚአብሔር እናት ልዩ ጥቅም አላገኘችም እንዲሁም እርሷ እግዚአብሔር አባትን በፍጹም አላማረረችም፡፡ ክልጇ ጋር ተሳስራ ኖራለች፡፡ እርሱም እራሱ በብዙ መከራ ማለፍ ነበረበት፤ ‹‹ ›› (ዕብ 5፡ 7-8)፡፡
ተሰቃይቶ ወደ ሞት ደረጃ የደረሰውን ሰው፡- ጸሎቱን፣ የእርዳታ ጥያቄውን መስማት እና መርዳት አለመቻል ለእናታችን ማርያም የሚያሳዝን እንደነበረ አሁን ለቤተሰብ እንዴት የሚያስጨንቅ ነው!
በኢየሱስ አፍ ተስፋ መቁረጥ፣ ፍርሃትና ጭንቀት፣ ጸሎት ሆኖአል፡፡ በጣም ብዙ የተሠቃዩ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው የኢየሱስን ጸሎት በቃሎቻቸው ይደግማሉ፤ ‹‹አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ? ለእርዳታ በብርቱ በምንጮኸበትስ ጊዜ ስለምን ከእኔ ራቅህ? አምላኬ ሆይ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጮኸለሁ አንተ ግን አትሰማኝም፣ ሌሊቱን ሁሉ እጣራለሁ፣ እረፍትም የለኝም … ›› (መዝ 22)
በሥቃይ ጊዜ እናት የሚሠቃዩትን ሰዎች ጥላ አትሄድም፡፡ እርሷ ራሷ በዛ ቦታ መገኘት የሚያስፈልግበትን ጊዜ ታውቃለች፡፡
ማርያም፣ በልጁ መስቀል ሥር ቆማ ነበር፡፡ አሁን እኛን ለብቻችን አትተወንም፣ በተለይም የእርሷን ሕልውና፣ ፍቅርንና ጸሎት በምንፈልግበት ጊዜ፣ እርሷ የእኛን አቤቱታ ትሰማለች፤ ‹‹ለኛ ለኃጢአተኞች አሁንም በሞታችን ጊዜ ለምኝልን››፡፡ እርሷ የእኛን ጸሎት ለልጇ ታቀርባለች፣ በእርሱ አማካይነት ለእግዚአብሔር አብ ጸሎታችንን ታቀርባለች፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ያደረገውን እንድናደርግ ትጋብዘናለች፤
ሀ/ ከእግዚአብሔር ጋር እንድናስታርቅ (ክርስቶስ ለወንጀለኛው ይቅርታ እንዳደረገ)፤
ለ/ የኢየሱስ የመጽናኛ ቃላት እንድንቀበል፤ ‹‹በእውነት እልሃለሁ ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ!››
ሐ/ ሞት አፋፍ ስንደርስ የኢየሱስን ጸሎት እንድንደግም፤ ‹‹አባት ሆይ እነሆ ነፍሴን በእጅህ አስረክባለሁ››፡፡
እንጸልይ፡-
አባት ሆይ፣ አንተ በምህረትህና በፍቅርህ እናተችን ማርያምን በልጁህ መስቀል ሥር መቆም እንድትችል አደረግህ፡፡ እናታችን ማርያም በጭንቃችን፣ በኃጢአታችንና ተስፋ በምነቆርጥበት ጊዜ አጠገባችን እንድትሆንና በዚያው እኛ ሁል ጊዜ በፍቅርህ መታመን እንድንችል፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡