4 - እመቤታችን ማርያም የተትረፈረፈ ሕይወት መንገድ ታሳየናለች
- Category: ከእመቤታችን ማርያም ጋር መጸለይ
- Published: Monday, 09 August 2010 08:58
- Written by Super User
- Hits: 4878
- 09 Aug
4 - እመቤታችን ማርያም የተትረፈረፈ ሕይወት መንገድ ታሳየናለች
የእግዚአብሔር ቃል፡- የመልአኩ ገብርኤል ብስራት፤ ሉቃስ 1፡ 26-38
‹‹ ›› (ማር 8፡ 34-35)
ከመልአኩ ገብርኤል ቃል በኋላ ቅድስ ድንግል ማርያም የሕይወቷን ዕቅድ በጥልቀት ተረዳች፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም፣ የእርሱ አገልጋይ በመሆን፣ ሕይወቷን ሙሉ ለእርሱ ሰጠች፡፡ ቅድስት ማርያም ለእግዚአብሔር ‹እሺ› አለች፣ እሺታዎንም አላጠፋችም፤
‹‹ ›› (ሉቃስ 9፡ 62)
እርሷ፣ እንደ ነቢያ፣ የእግዚአብሔር ቃል አገልጋይ ነበረች፡፡ እርሷ ለራሷ ምንም አልፈለገችም እግዚአብሔር እንዲከብር እንጂ፡፡ እመቤታችን እንዲህ የሚሉትን የጳውሎስን ቃላት መድገም ትችላለች፤
‹‹ ›› (1ቆሮ 2፡ 2)፡፡
በቤተሰብ ውስጥ ብዙ ችግሮችና ፈተናዎች አሉ፤ ለምሳሌ ያለን ሀብት በእኩልነት አለመጠቀም አንዳንድ ጊዜ ወደ እነዚህ ነገሮች ይወስደናል፤ እግዚአብሔር አባታችንን እንድንረሳ፣ ገንዘብን ያለአግባብ እንድንጠቀም፣ ሱሰኞች ያደርገናል፣ በፈተና ይጥለናል፣ የወንጌልን መንገድ እንድንረሳ ያደርገናል፡፡ ብዙ በቤተሰብ ውስጥ ያሉ ስቃዮች የሚመጡት ከነዚህ ችግሮች ነው፡፡ ይህ መንገድ የተትረፈረፈ ሕይወት እንድንወርስ አያደርገንም፡፡
ክርስቶስ የመጣው ሕይወት እንድናገኝና የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲኖረን ነው (ንጽ. ዮሐ 10፡ 10)፡፡ ቅድስት ማርያም ራሷን በመካድ፣ የራስዋንና የክርስቶስን መስቀል ተሸክማ እርሱን ተከትለዋለች፡፡ እንደ አብዘኞቹ እናቶቻችን፣ የእርሷ ሕይወት ቀላል አልነበረም፤ አለመረዳዳት፣ ብቸኝነትና ሞት ነበረ፡፡
‹‹ ›› (ሉቃ 2፡ 35)፡፡ ማርያም ተስፋዋን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስላደረገች፣ እርሷ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች ናት፣ መንፈሷ አዳኟ በሆነው በእግዚአብሔር ደስታ የተሞላችና ፍጽምት፣ ብስል፣ በሕይወት የተሞላችና ለሰው ልጅ ምሳሌ ናት፡፡
በቤተሰባችን ውስጥ አባቶች፣ እናቶች፣ ወጣቶ፣ ሽማግሎዎች ማርያም ያለችውን ለማለት ከወሰኑ፤ ‹‹እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ፤ አንተ እንዳልህ ይሁንልኝ›› ከእናታችን ጋር መንገድ የሆነውን ክርስቶስን ከተከተሉ፣ የሚመኙትንና የተትረፈረፈውን ሕይወት ያገኛሉ፡፡
እንጸልይ፡-
ሁሉን የምትችል አባት ሆይ፣ እምነታችንና ተስፋችንን እውነተኛ አምላክና እውነተኛ ሰው በሆነው፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደው በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አጠንክርልን፡፡ በትንሣኤው ኃይል ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ለመድረስ እንድንችል በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንለምንሃለን፡፡ አሜን፡፡