ጸሎት ወደ ንጹሕ ልበ ማርያም

የማርያም ንጹሕ ልብ ሆይ! ስግደት የሚገባው ተወዳጅ ልጅሽ ልቡን የሰጠሽ፤ ሊነገር የማይቻል ሥልጣንሽን አስበሽ፣ በረድኤትሽ ተማምኜ  እንድትረጂኝ እለምናለሁ፤ አንቺንም ለተማጸነ ሁሉ እገዛሽን አብዢለት።

ሰማያዊ ሃብትና የማይደርቅ የጸጋ ምንጭ የሆነውን የኢይሱስን ልብ የከፈትሽ ማርያም ሆይ! ይህ ልብ የያዘውን ፍቅርና ምሕረት፣ ብርሃንና ደኅንነት ሁሉ በሰው ሁሉ ላይ ልታፈሽው ትችያለሽና የምንለምንሽን ሁሉ እንድትፈጽሚልን እንለምንሻለን።

የአብ ማረፊያ፣ የወልድ ማደርያ የመንፈስ ቅዱስ ቤት የሆንህ የማርያም ንጹሕ ልብ ሆይ! ልመናችንን በደስታ ተቀበል። እመቤታችን ሆይ! ልባችን ልብሽን እንደሚመስል አድርጊ።

አሜን።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ክብር ላንቺ የሚለውን መዝሙር ለማዳመጥ ከታች ያለውን ማጫወቻ ይጠቀሙ።