ጸሎት ወደ ቅዱስ ልበ ኢየሱስ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ሆይ! እንደምትወደኝ አምናለሁ - የኢየሱስ ደጉ ልብ ሆይ! ሁልጊዜ እንድወድህ አድርገኝ - የኢየሱስ ልብ ሆይ! ተስፋየ አንተ ነህ - ተወዳጁ ልብ ሆይ! ደካማ ነኝና እምነቴን ባንተ ላይ ጥያለሁ - በደግነትህ ተማጥኛለሁ - የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ሆይ! ሁሉ ያንተ ይሁን። የዋህና በልብ ትሑት የሆንህ ኢየሱስ ሆይ እባክህ ልቤን እንደ ልብህ አስምስልልኝ - ስለ ፍቅር መሥዋዕት የሆንህ የኢየሱስ ልብ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ላንተ የተቀደሰ መሥዋዕት ሆኜ እንድገኝ አድርገኝ። ለአምላካዊው ልብ ክብር ምስጋና ውዳሴ ይሁን - የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ሆይ! ሁሉ ይወቅህ - ሁሉ ይውደድህ - ሁሉ ይከተልህ። የኢየሱስ ልብ ሆይ! መንግሥትህ ይስፋ - ስለኛ ፍቅር የተቃጠልህ የኢየሱስ ልብ ሆይ! የኛም ልብ ስላንተ ፍቅር እንዲቃጠል አድርግልን - የኢየሱስ አምላካዊ ልብ ሆይ! ኃጢአተኞች ወዳንተ እንዲመለሱ አድርግ - በሽተኞችን አድን - የንስሐ ቦታ ነፍሶችን ነጻ አውጣቸው - የኢየሱስ ደግ ልብ ሆይ! ለኛና ከኛ ለተለዩ ወንድሞቻችንም ምሕረትህን ስጠን - የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ሆይ! ቤተ ክርስቲያንን ባርክ - ደጎችን በጽድቅ አጥናቸው - ኃጢአተኞችን መልሳቸው - ለማያምኑትም ብርሃንህን ስጣቸው - ዘመዶቻችንን፣ ወዳጆቻችንንና መልካም አድራጊዎቻችንን ባርካቸው - ፍቅርህ ለሁሉም ይዳረስ። አሜን። |
(አባ ገብረሚካኤል መኮንን ካሳተሙት የጸሎት መጽሐፍ የተወሰደ) |
ገሩ ልብህ የሚለውን መዝሙር ለማዳመጥ ከታች ያለውን ማጫወቻ ይጠቀሙ።