<<ሰላም ለኪ>> ሰላም ላንቺ- የሚለው ሲታውያን መነኮሳን በንዋም ጸሎት ማለትም ከመኝታ በፊት የሚያደርጉት ጸሎት መደምደሚያ ሲሆን፤ የሚዜመውም መብራቶች ጠፍተው ትኩረታቸውን በእመቤታችንና በተባረከው ፍሬዋ አንድ ልጇ ክርስቶስ ላይ በማድረግ በጨለማና በሸለቆ በሚመሰለው የሰው ልጅ የሕይወት ጉዞ ታሪክ ውስጥ እርስዋ ተስፋ ሆና ክርስቶስን ለሰው ልጆች ደኅንነት እንዳስገኘች ሁሉ በዕለቱ መደምደሚያም የእግዚአብሔርን ምሕረት ዳግም በርስዋ የሚማጠኑበት ጸሎት ነው።......ያዳምጡት፦

 

ሰላም ለኪ! ኦ ንግሥት

ሰላም ለኪ! ኦ እመ ምሕረት፤ ሰላም ለኪ! ኦ ጥዕምት።

ሕይወትነ ወፍስሐነ ወተስፋ መድኃኒትነ፤ ኀቤኪ ንጸርኅ ንሕነ ስዱዳን፣ ውሉደ ሔዋን።

ወንትማሕፀን ብኪ እንዘ ንበ ወናስቆቊ ምስለ አንብዕ በዝንቱ ቆላተ ብካይ።

ወበእንተዝ አጽንኢኀቤነ በርእየ አእይንተ ምሕረትኪ ኦ ቃውምነ ወእምድኅረ ዝንቱ ስደት አርእይነ ቡሩክ ፍሬ ከርስኪ ዘውእቱ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።

ኦ ርኅርኅት! ኦ ጥዕምት!

ኦ መሐሪት! ድንግል ማርያም።

 

 

የምሕረት እናት ንግሥት ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን!

ሕይወታችን፣ ደስታችን ተስፋችን ሆይ ሰላም ላንቺ ይሁን! እኛ የሔዋን ልጆች ስደተኞች ጩኸታችንን ወዳንቺ እናቀርባለን። በዚህ በለቅሶ ቆላ ሆነንእያዘንንና እያለቀስን ወዳንቺ እንማጠናለን።
እንግዲህ እባክሽ የእኛ ጠበቃ ሆይ በምሕረት ዓይኖችሽ ወደ እኛ ተመልከች። ደጊቱ፣ ቸሪቱ መሐሪቱ ድንግል ማርያም ሆይ! ከዚህ ስደት በኋላ የተባረከውን ፍሬ ኢየሱስን አሳዪን ብለን እንለምንሻለን።
 
 
(ተዛማጅ የአማርኛ ትርጉሙ አባ ገብረሚካኤል መኮንን ካሳተሙት የጸሎት መጽሐፍ የተወሰደ ነው)