If our pages are illegible, please download fonts here: Visual Geez Unicode

 

 

 

የኢትዮጵያ የሃይማኖት መሪዎች ሕግ አርቃቂዎች በግብረሰዶማዊነት ላይ እገዳ የሚጥል ህግ እንዲዘጋጅ ጥያቄ አቀረቡ፡፡

December 24 2008 -  http://www.ethiopianreporter.com/content/view/3808/54/ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት የሃይማኖት ሰዎች ከትላንት በስቲያ በአዲስ አበባ ስብሰባ ካካሄዱ በኋላ ባወጡት የአቋም መግለጫ በግብረሰዶማዊነት ላይ ሕገ መንግሥታዊ እገዳ እንዲጣል ጠይቀዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትንም "የሞራል ዝቅጠት የመጨረሻ ደረጃ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ግብረሰዶማዊነት በህፃናትና በወጣት ወንዶች ላይ ለሚፈፀም የወሲብ ጥቃት መንስዔ መሆኑንም የሃይማኖት መሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ አቡነ ጳውሎስ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሲሰጡ "ይህ ድርጊት ግብረ ሰዶማዊነትሪ ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተለመደ ነው፡፡ ይህች የመጽሀፍ ቅዱስ አገር ይህንን ድርጊት አጥብቃ ታወግዛለች፡፡ ይህንን ድርጊት የሚፈፅሙ ሰዎች እንደ እንስሳ ማሰብ የተሳናቸው ናቸው" ብለዋል፡፡

"ይህንን ባህሪ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡ ግብረሰዶማውያን ሊታረሙ ይገባቸዋል" ግብረሰዶማዊ የሆነ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ ቢያንስ የስድስት ወር የእስር ቅጣት ይጣልበታል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በአገሪቱ ወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሕገ ወጥ ድርጊት ተደርጐ የተጠቀሰ ቢሆንም በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ግን የተጠቀሰ ነገር የለም፡፡

"በግብረሰዶማዊያን እንቅስቃሴ ላይ ሕገ መንግሥታዊ እገዳ እንዲደረግ ፓርላማውን አበክረን እንጠይቃለን" ይላል የሃይማኖት መሪዎቹ የአቋም መግለጫ፡፡

ከዚህ በተጨማሪም መንግሥት ብዙ የማገገሚያ ማዕከላትን እንዲገነባና የወሲብና ወሲብ ነክ ፊልሞችን በሚያሳዩ ማቴሪያሎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ የሃይማኖት መሪዎቹ ጠይቀዋል፡፡

ዩናይትድ ፎር ላይፍ ኢትዮጵያ የተሰኘው አገር በቀል መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ኃላፊ አቶ ስዩም አንቶኒዮስ በበኩላቸው ግብረሰዶማዊ መሆን የሰብአዊ መብት ጉዳይ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

"ግብረሰዶማዊነት የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው ብለን አናምንም፤ ከሰው ልጅ አፈጣጠር ጋርም የሚገናኝ አይደለም፤ ምንም ዓይነት ባዮሎጂካዊ መሠረት የለውም፡፡ ድርጊቱ ተቀባይነት የለውም፤ የዘቀጠ ተግባር ነው፡፡ እያንዳንዱ የሃይማኖት መሪ ድርጊቱን የዘቀጠ ግብረ ገብነት የመጨረሻ ደረጃ መሆኑን ይናገራሉ" ብለዋል፡፡

ር.ሊ.ጳ. በሽብር ወደ ተረበሸችው ሕንድ መልእክት ላኩ

Vatican City, Nov 27, 2008 / 11:02 am (CNA).- በሕንዷ ሙምባይ ከተማ በተለያዩ ስምንት ቦታዎች ላይ ታጣቂ ሰዎች በከፈቱት ተኩስ በወቅቱ ዘገባ መሠረት ከ100 በላይ ሰዎች በመገደላቸውና ከ300 በላይ በመቁሰላቸው ቤኔዲክቶስ 16ኛው የተሰማቸውን ኀዘን ለሙምባዩ ሊቀ ጳጳሳት የቴሌግራም መልእክት የላኩ ሲሆን፤ በመልእክታቸውም የተሰማቸውን ልባዊ ኀዘን ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች እንዲያደርሱላቸው ሊቀ ጳጳሱን በመጠየቅ በጸሎታቸውም እንደሚያስታውሷቸው ገልጸዋል።

ር.ሊ.ጳ. በቴሌግራማቸው ፤ “አሸባሪነት በሰው ልጅ ቤተሰብ ላይ የሚደረግ ጥቃት ነው፤ እንዲሁም ሰላምንና አንድነትን በማናጋት የሰው ልጅ ክቡር ጥሪ የሆነውን እግዚአብሔርንና ሰውን የማፍቀር ዓላማ ግብ ያደናቅፋል” በማለት ብየአሸባሪነት ተግባር በቶሎ እንዲቆም ጠይቀዋል።

መልእክታቸውን በሽብር ጥቃቱ ለሞቱት ምሕረትና ዘላለማዊ ዕረፍትን፣ ለቆሰሉትና በኀዘን ውስጥ ላሉት ደግሞ እግዚአብሔር ብርታትና መጽናናቱን እንዲሰጣቸው በመጸለይ ደምድመዋል።

"ከትምህርት ይልቅ የጦር መሣሪያን ማግኘት ይቀላል"

NEW YORK, NOV. 20, 2008 (Zenit.org).- ከምግብ፣ ከመጠለያና ከትምህርት ይልቅ የጦር መሣሪያ በቀላሉ የሚገበትን የዓለማችን ተጨባጭ ሁኔታ ቫቲካን አወገዘች።

ኅዳር 10 ቀን 2001 ዓ.ም. በኒውዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው “የዓለም አቀፍ ሰላምና ደኅንነት ጥበቃ” በሚለው የጦር መሣሪያ ቁጥጥርና ቅነሳ ላይ በማተኮር በተደረገው ስብሰባ ላይ ነው በተባበሩት መንግሥታት የቫቲካን ቋሚ ተጠሪ ሊ.ጳ. ቸለስቲኖ ሚሊዮሬ ይህን መልእክት ያስተላለፉት።

በዚሁ ስብሰባ ላይ ሊቀ ጳጳሳቱ ስለ ኮንጎ ሰላም በአጽንዖት የተናገሩ ሲሆን “በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዓይን ፊት በኮንጎ ዴሞክራቲክ የሚደረገውን ግድያ ቫቲካን ታወግዘዋለች” ካሉ በኋላ በሰው ልጅ ላይ እየደረሰ ያለው አሳዛኝ ሁኔታ እንዲያቆም ጥረት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።

ቤኔዲክቶስ 16ኛው ለአዲሱ የአሜሪካ ርእሰ ብሔር እንደሚጸልዩ ቃል ገቡ

VATICAN CITY, NOV. 5, 2008 (Zenit.org).-  ቤኔዲክቶስ 16ኛው አዲስ የተመረጡት የአሜሪካ ርእሰ ብሔር <<የፍትሕ፣ የአንድነትና የሰላም ዓለም >>ይገነቡ ዘንድ አበረታቱ።

ር.ሊ.ጳ. ይህን የገለጹት ባራክ ኦባማ የርእሰ ብሔርነቱን ምርጫ በማሸነፋቸው ለርሳቸው፣ ለባለቢታቸውና ለቢተሰቦቻቸው በላኩላቸው የመልካም ምኞት መግለጫ ቴሌግራም መልእክታቸው ሲሆን ርእሰ ብሔሩ ሕዝባቸውንና ዓለም አቀፉን ኅብረተሰብ ለማገለገል ለተጣለባቸው ከባድ ኀላፊነት እግዚአብሔር ያግዛቸው ዘንድ እንደሚጸልዩላቸውም ቃል ገብተዋል።

<<እርስዎንና የአሜሪካን ሕዝብ በጎ ፈቃድ ያላቸውንም ሰዎች ጨምሮ ለፍትሕ፣ ለሰላምና ለአንድነት በሚያደርጉት ጥረት ሁሉ የጌታ በረከት ያግዝዎ ዘንድ እመኛለሁ>> በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Catholic News Service PHOTO

ሁለት ኢየሱሳውያን ካህናት ሞስኮ ውስጥ ተገደሉ

MOSCOW - 30 October 2008 Independent Catholic News - ሁለት የኢየሱሳውያን ማኅበር ካህናት ሞስኮ ከተማ ውስጥ ማክሰኞ ዕለት መገደላቸውን የሩስያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባዔ ጠቅላይ ጸሐፊ አሳወቁ።

የካህናቱ አስክሬን በበከባድ ሁኔታ በስለት ተወግቶ በመኖሪያ ሕንጻቸው ውስጥ የተገኘ ሲሆን በቢቢሲ ዘገባ መሠረት አንደኛው ካህን አባ ኦቶ መስመር ሩስያዊ ሲሆኑ ሁለተኛው አባ ቪክቶር ቤታንኮርት ኤኳዶራዊ መሆናቸው ታውቋል። 

የሞስኮ ፖሊስ ወንጀሉን እየመረመረ ሲሆን፤ የሩስያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት <<በሩስያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ኀዘን ላይ ናት፤ በሕዝባቸው የሚወደዱ ታታሪ  እረኞች ተገድለዋል። ቤተ ክርስቲያን መሐሪ ጌታ ነፍሳቸውን በሰማያዊ መንግሥቱ ያሳርፍ ዘንድ ፤ እንዲሁም ይህን ዘግናኝ ወንጀል ለፈጸሙትም ጌታ የንስሐን ጸጋ እንዲሰጣቸው ትጸልያለች። ግድያ ከባድ ኃጢአት ነውና ፍትሐዊ ውሳኔም መፈጸም አለበት>> ብለዋል።  

<<እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ መጽሐፍ ቅዱስ ሊኖረው ይገባል>>

Independent Catholic News የሚጸለይበትና የሚነበብ መጽሐፍ ቅዱስ ክብር ባለውና በሚታይ ሁኔታ በያንዳንዱ ቤተሰብ ቤት ውስጥ መኖር አለበት በማለት በእግዚአብሔር ቃል ዙሪያ በቫቲካን ሲካሄድ የነበረው የጳጳሳት ሲኖዶስ መደምደሚያ መልእክት በማስተላለፍ ጥቅምት 16 ቀን ር.ሊ.ጳጳሳት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ተጠናቀቀ።

ከ100 ሀገራት በላይ የተሰባሰቡ 253 ጳጳሳትና ሌሎች ተወካዮች  የሲኖዶሱን ጠቅላላ መልእክት በአንድ ድምጽ ያጸደቁት ሲሆን፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው ሀብታም መልእክትን ለሕዝበ እግዚአብሔር ማዳረስ ለሦስት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የሲኖዶሱ ዋና መልእክት ነው።

 

በጳጳሳቱ ጉባኤ ላይ የቻይናዊቷ ምእመን ጥቆማ

VATICAN CITY, OCT. 14, 2008 (Zenit.org).- በቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው የጳጳሳት ሲኖዶስ ላይ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዴክቶስ 16ኛው የእግዚእብሔርን ቃል በጥሩ ሁኔታ የሚያካፍሉበት የራሳቸው ብሎግ (የኢንተርኔት ግለ ገጽ) ይኖራቸው ዘንድ ተጠቆመ።

በሆንግ ኮንግ የካቶሊካዊ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ፕሬዝዳንት የሆኑት አኘስ ላም ከጠቆሟቸው ሀሳቦች አንዱ የሆነው ይኸው ብሎግ የመክፈት ጉዳይ የእግዚአብሔርን ቃል ይበልጥ ለማስፋፋትና ምእመናንም ክርስቶስን እንዲያውቁ ለማወቅ እንደሚያግዝ በማሰብ ነው።

እንደ አኘስ አስተያየት <<የዘመኑን ዓለም መንጋ ለማሰማራት ቅዱስ አባታችን በተለያየ ቋንቋ ሊነበብ የሚችል፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አጠር ካለ አስተንትኖ ጋር በተለያየ ስዕሎች ታጅቦ የሚያቀርብ  ብሎግ ቢጀምሩ ጥሩ ነው።>>

የመጀመሪያዋ ሕንዳዊት ቅድስት

 Independent Catholic News - ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ለሕንዳውያን የመጀመሪያ ወጋዊ ቅድስት ሴት ቅ. አልፎንሳ የቅድስና እወጃ ጥቅምት 2 ቀን  በደመቀ ሥርዓት አወጁ።

በመሥዋዕተ ቅዳሴው ላይ ር.ሊ.ጳ. በሕንድና ኢራቅ ክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው ጸረ ክርስቲያናዊ ጥቃት ይቆም ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

በስብከታቸውም የቅድስት አልፎንሳን ሕይወት በመጥቀስ እሷ ፈቃደኛ ላልሆነችው ትዳር ሲያስገድዷት ለማምለጥ ስትል በእሳት እግሯ እንደተቃጠለና በዚህም ሁኔታ በቀሪው ዕድሜዋ በአደጋው ብትሰቃይም ውስጧ የነበረውን የምንኩስና ሕይወት ምርጫ መኖር መቻሏንና በ35 ዓመት ዕድሜዋ በ1939 ዓ.ም. ማረፏን አስታውሰው ያደረገችውን ውሳኔዋን አድንቀዋል። <<እሷ በሕይወቷ የተሰቃየች ልዩ ሴት ናት፤ አንድ ቀን በመንግሥተ ሰማይም እንገናኛት ዘንድ የየራሳችንን መስቀል በመሸከም እርሷን መምሰል ይኖርብናል>> ብለዋል።

በዕለቱ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰብት በ10 ሺ ለሚቆጠሩ ሕንዳውያን <<ይህች  ቅድስት በጥልቅ ስቃይ ጊዜ የነበራት ትእግሥት፣ ብርታትና ጽናት ስቃይን የምንቋቋምበት ኃይልን እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እንደሚሰጠን ያስታውሰናል።...>> ካሉ በኋላ ሕንዳውያን ክርስቲያኖች ስለዚች ቅድስት እግዚአብሔርን በሚያመሰግኑበት በአሁኑ ሰዓት እየተንገላቱ መሆኑን ጠቅሰው እሳቸውም በጸሎት አንድ ላይ መሆናቸውን ተናገረዋል። እንዲሁም በኢራቅም የሚደረገው ግፍ ክርስቲያኖችን ለሞትና ለስደት እየዳረገ መሆኑን አስታውሰዋል።   ጥቃት ፈጻሚዎቹ ወደ ፍቅር ስልጣኔ እንዲራመዱና  ይህን ድርጊታቸውን እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

የጳጳሳት ሲኖድ ተከፈተ

Independent Catholic News - ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው መስከረም 26 ዕለተ ሰንበት የጳጳሳት ሲኖድ ጥቅላይ ጉባዔ መጀመርን በማስመልከት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳረጉ።  ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ ወደ 250 የሚገመቱ ሊቀ ጳጳሳት፣ ጳጳሳትና ካርዲናሎች በዚህ ሲኖድ ለመጪዎቹ ሦስት ሳምንታት <<የእግዚአብሔር ቃል በቤተ ክርስቲያን ሕይወትና ተልእኮ>> በሚል ሃሳብ ላይ እንደሚወያዩ ታውቋል።

የሲኖዱ ቀዳሚ ትኩረት የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ሕይወት ሰጪና ሕይወት ለዋጭ በሕዝበ እግዚአብሔር ዘንድ ይበልጥ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ነው።  

ለመጀመሪያ ጊዜም በዚህ ሲኖድ ላይ እስራኤላዊ ረቢ የአይሁዳውያን መጽሐፍ ቅዱስ አተረጓጎምን በማስመልከት ገለጻ የሚያደርጉ መሆኑ ሲዘገብ የሆንግ ኮንግ ጳጳስ በሲኖዱ ላይ ቢገኙም ሌላ ከቻይና የተጋበዙ ሁለት ጳጳሳት መንግሥት ከሀገር ለመውጣት ስላልፈቀደላቸው ሊገኙ ያለመቻላቸው ተነግሯል።

ሲኖዱ ከመስከረም 25 እስከ ጥቅምት 16 ይካሄዳል።

የካቶሊክ ርዳታ አገልግሎት (CRS) ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የምግብ ርዳታ በማድረግ ላይ ነው።

www.catholic.org - በመላ ሀገሪቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ለድርቅ በተጋለጡበት በአሁኑ ሰዐት ይህ ካቶሊካዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ወኪል (USAID) ጋር የ53.4 ሚሊየን ዶላር ስምምነት መፈራረሙና ወደ ሦስት ሚሊየን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የድርቅ ጉዳተኞችን ሊያግዝ የሚችል 75,140 ሜትሪክ ቶን ምግብ በፍጥነት በማዳረስ ላይ መሆኑ ተዘገበ።

 

የርዳታው ስርጭት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በተደረገ እገዛ የተመረጠ ሲሆን በዚህም መሠረት በይበልጥ ለረሃብ ተጋልጠዋል በተባሉት በአማራ፣ ኦሮምያ፣ ሶማልያ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰባት መንግሥታዊ ክልልና በትግራይ ክልል ለማዳረስ ታቅዷል።  

 

በኢትዮጵያ የድርጅቱ ኀላፊ የሆኑት አቶ ሌን በንከርስ እንደገለጹት ከአሁን በፊትም በተለያየ ሁኔታ ርዳታ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ በነሐሴና መስከረም ወርም ከተባበሩት መንግሥት ጋር በመተባበር በኦሮምያ ክልል ለሚገኙ ከ16,000 ለሚበልጡ አርሶ አደሮች ዘር መከፋፈሉን ገልጸዋል። አያይዘውም በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ ውስጥ እህል ለመግዛትም ሆነ ከመንግሥት ለመዋስ ማግኘት ያለመቻሉ ይህ ድርጅት 1500 ሜትሪክ ቶን እህል በ USAID የተከማቸ እህል በጂቡቲ በቅርቡ እንደሚመጣና በዚህ ወር ውስጥ በ 34 አውራጃዎች ለሚገኙ አረጋውያን፣ ነፍሰ ጡሮችና እመጫቶች እንደሚዳረስ አስረድተዋል።

ድርጅቱ በእርሻና መስኖ በኩል ድጋፍ ያደረገላቸው አካባቢዎች ከሌሎቹ ጋር ተነጻጽሮ ድርቁን በተሻለ ሁኔታ የተቋቋሙ መሆናቸውን አውሥተው አስቸኳይ ርዳታ ማድረጉንና ለወደፊትም ከተመሳሳይ ረሃብ ለመታደግ የረጅም ጊዜ የልማት እቅድ በማዘጋጀት አጋዥ ድርጅቶችን ርዳታ እንዲያደርጉ ጥረቱ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል።

 

የካቶሊክ ርዳታ አገልግሎት ዘር ሃይማኖት ወይም ዜግነት ሳይለይ በ100 ሀገራት ውስጥ ባጠቅላይ ሰብአዊነትን የሚረዳ ድርጅት ሲሆን በኢትዮጵያም ከ1950 ዓ.ም. ጀምሮ እያገለገለ ነው። በሀገሪቱ በ9 ክልሎች 123 ሠራተኞችን ቀጥሮ 589 ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ በማድረግ ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። http://crs.org/ethiopia/

 

ሕንድ ውስጥ እንደገና ሌላ ካህን ተገድለው ተገኙ።

ሙምባይ - AsiaNews - በገዳም ውስጥ ሕንዳዊ ሥርዓት የተላበሰ የምነና ሕይወት ይኖሩ የነበሩ ካቶሊካዊ ካህን ተገድለው መገኘታቸው ታወቀ።

አባ ሳሙኤል ፍራንሲስ ወይም በአካባቢው <<ስዋሚ አስቴያ>> ማለትም ቸር፣ለጋስ በመባል የሚታወቁ ሲሆን መስከረም 11 ቀን ጠዋት ኮታ ራምፑር በሚባለው መንደር በሚገኘው ገዳማቸው ጸሎት ቤት ውስጥ እጃቸው የኋሊት ታስሮ፣ አፋቸው በጨርቅ ታፍኖና ግንባራቸውም ቆስሎ አስክሬናቸው ተገኝቷል።

ነፍሰ ኄር አባ ሳሙኤል ፍራንሲስ

የ50 ዓመት ዕድሜ የነበራቸው መነኩሴው ልብሳቸው የሕንዳውያን መነኮሳን የሚለብሱት ሳንያዚን የተባለ ሲሆን በገዳማቸውም ዮጋና የተመስጦ ጸሎት ትምህርት ይሰጡ ነበር። በዚህም ሁኔታ በክርስትናና በሂንዱ እምነት መካከል የአንድነትን መንፈስ በማሳዳግ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ሲሆን በአካባቢው በሁሉም እምነት ተከታዮች ዘንድ አክብሮትና ተቀባይነት የነበራቸው መነኩሴ ነበሩ

ነሐሴ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. አንድ ካህን በዘግናኝ ሁኔታ መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን ፖሊስ ወንጀሉ እንዴትና ለምን መደረጉን እያጣራ ሲሆን አንድ የኮሌጅ መምህርም <<ለኅብረተሰቡ ዕድገት በከፍተኛ ሁኔታ ያገለግሉ የነበሩ ሰውን እንዲህ ጭካኔ በተሞላው ሁኔታ መግደል ማለት ባጠቃላይ በሰብአዊነት ላይ ወንጀል መፈጸም ማለት ነው>> በማለት ሁኔታውን ገልጸውታል።

 

የጃፓን መንግሥት የመጀመሪያውን ካቶሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር መረጠ

ቶኪዮ መስከረም 12 - Independent Catholic News- በሀገሪቱ አናሳ ቁጥር ካላቸው ካቶሊካውያን አንዱ የሆኑት ቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት ታሮ አሶ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ።

በሊበራል ዴሞክራት ፓርቲ ሊመረጡ የቻሉት ያሱዎ ፉኩዳ በድንገት ሥልጣናቸውን በመተዋቸው ሲሆን ከንጉሣዊ ቤተሰብ ጋር የጋብቻ ትስስር ያላቸው ታሮ ጠቅላይ ሚኒስትር መመረጣቸው በጃፓን ታሪክ ውስጥ ካቶሊካውያን ከፍተኛ ሥልጣንን የመጋራት ሁኔታ የመጀመሪያው አድርጎታል።

<<ማርያም ዓይናችንን ወደ ክርስቶስ እንድንመልስ ታደርገናለች>> ቤኔዲክቶስ 16ኛው

ሉርድ-ፈረንሣይ (CNS) - እሑድ መስከረም 4 2001 ዓ.ም. ጠዋት ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ፈረንሣይ ውስጥ በሚገኘው ሉርድ ማርያም መካነ ንግደት ከመላው ዓለም ለተሰባሰቡ 150, 000 ለሚያህሉ የሉርድ ነጋድያን(መንፈሳዊ ተጓዦች) መስዋዕተ ቅዳሴ አሳረጉ።

በስብከታቸውም ወደ ማርያም የሚደረግ ትሑት ጸሎት ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ መሆኑንና እመቤታችን በሉርድ የተገለጠችው አካላዊና መንፈሳዊ ስቃይ ያላቸውን ሁሉ ዓይናቸውን ወደ ኢየሱስ መስቀል በማንሣት ከሞትና ከኃጢአት በላይ የሚበረታውን የክርስቶስን ፍቅር እንዲገነዘቡ ለመጥራት መሆኑን ተናግረዋል።

ወደ ማርያም የምናደርገውን መንፈሳዊነት ትርጉምን በማስመልከት ሲናገሩም <<ማርያም ዓይናችንን ወደ ክርስቶስ እንድንመልስ ታደርገናለች>> በማለት ገልጸዋል። ከ150 ዓመታት በፊት እመቤታችን በግብርና ሕይወት ለነበረችው የ14 ዓመት ልጅ (ለቅድስት ቤርናዴት)  በሉርድ ራሷን ስትገልጽ የመጀመሪያው ነገር የመስቀል ምልክት ማማተብን እንደነበርና ይህም ወደ ክርስቶስ ምሥጢር መግቢያ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን አስታውሰዋል። <<ትሑትና ጥልቅ የሆነ፤ በእምነትና በቀጣይነት የሚደረግ ጸሎት በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ ማዕከላዊ ቦታን መያዝ እንዳለበትና ከክርስቶስ አንዳች ኃይልን መቀበል ከፈለግን የጸሎት ሕይወት እንደሚያስፈልገን ማርያም ታሳውሰናለች>> ብለዋል

ሉርድ ማርያም ያለ አዳም ኃጢአት መጸነሷን የገለጠችበት ቦታና በዓል በመሆኑም ይህ ሃሳብ ክርስቲያኖች ኃጢአተኞች ብንሆንም በተስፋ ግን የዳንን መሆናችንን እንድንገነዘብ ያደርገናል ካሉ በኋላ <<ይህ እመቤታችን የምትከፍትልን ጎዳና ነው፦ ራስን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር መስጠት የእውነተኛው ነጻነት ጎዳና ነው>> በማለት ከእርሷ ለእግዚአብሔር ራሳችንን እንዴት መስጠት እንደሚቻል እንድንማር አሳስበዋል።

ቅዳሴው ላይ የነበሩት ምእመናን ከመላው ባህልና አህጉራት የተሰባሰቡ ሲሆን ጸሎቶችና ንባባት የተደረጉት የቻይናን አካቶ በ10 የተለያዩ ቋንቋዎች ነበር።

በዋዜማው ቅዳሜ ጠዋትም ቅዱስነታቸው በፓሪስ ከ250 ሺ በላይ ለሚሆኑ ምእመናን ቅዳሴ ያደረጉ ሲሆን በስብከታቸውም የሰው ልጅ በምድር ላይ ዘላቂ የሆነ ደስታን ሊያመጣ ይችላል የሚለውን አስሳሰብ ጨምረን ጣዖታትን ማምለክ እናስወግድ።…እግዚአብሔር በፍጹም የሰው ልጅ አእምሮ የማሰብ ችሎታን አይቃወምም፤ እንድንሰዋውም አይጠይቀንም። እውቀት በምንም መልኩ ከእምነት ጋር አይጋጭም! አንድ አምላክ- አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ- አእምሯችንን ፈጠረልን እምነትንም ሰጠን፤ በነጻነትም እንደ ውድ ስጦታ እንቀበለው ዘንድ ሰጠን። ይህንን ትክክለኛ እይታ የሚያበላሸው የጣዖት አምልኮ ነው በማለት በዘመናችን የገንዘብ፣ የሀብት፣ የሥልጣን እንዲሁም የእውቀት ጥማት ሰውን ከእውነተኛ ፍጻሜው እየለየው አይደለምን? ሲሉ በጥያቄ መልክ ጥልቅ ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

 

ር.ሊ.ጳጳሳት ሃይማኖት የአዲሲቷ አውሮፓ ክፍል እንዲሆን ጥሪ አቀረቡ።

ፓሪስ መስከ.2 (CNA)- ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛው ለጉብኝት ወደ ፈረንሣይ የተጓዙ ሲሆን በዚያ እንደደረሱም ቤተ ክርስቲያን በኅብረተሰብ ውስጥ በማንም ሊተካ የማይችል ኅሊናን የመቅረጽና ሥነ ምግባራዊ መመሪያን የማመቻችት ሚና ስላላት የፈረንሣይ ሕዝብ በአዲስ መልኩ ከርስዋ ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

ቤኔዲክቶስ 16ኛውና ኒኮላስ ሳርኮዚ።

ር.ሊ.ጳ. ከርእሰ ብሔር ኒኮላስ ሳርኮዚ ጋር በግል ከተገናኙ በኋላ ለርእሰ ብሔሩ፣ ቁጥራቸው ብዙ ለሆነ ባለሥልጣናትና የሃይማኖት መሪዎች እንዲሁም ለመላው የፈረንሣይ ሕዝብ ንግግር አድርገዋል። ለተደረገላቸው ልዩ አቀባበል ካመሰገኑ በኋላ የጉዟቸው ዋና ዓላማ እመቤታችን ማርያም ፈረንሣይ ውስጥ በሚገኘው ሉርድ ቦታ ለቅድስት በርናዴት የተገለጠችበትን 150ኛ ዓመት ለማክበር መሆኑን አሳውቀዋል።

“በዚህ ዓመት ከመላው ዓለም በእምነትና በፍቅር ተሞልተው መንፈሳዊ ጉዞ በማድረግ ወደዚህ ቦታ እንደሚመጡት ምእመናን መሆን ምኞቴ ነው። በተሰጡኝ በነዚህ አራት የጸጋ ቀናት ውስጥ በሀገራችሁ የማከብረው ይህንን እምነትና ፍቅር ነው” ብለዋል ር.ሊ.ጳ.።

ቤኔዲክት ቤተ ክርስቲያን በፈረንሣይ ታሪክ ውስጥ ያላትን ትልቅ ቦታ ጠቅሰው ይህ እውነታ የዚህ ዘመን ፈረንሣውያን የሀገራቸውንና የቤተ ክርስቲያንን ግንኙነት እንዲያስተውሉና ባለፉት ሁለት ክፍለ ዘመናት ሙሉ ለሙሉ የጠፋውን የእምነት ትርጉም ከዓለማዊ ግንዛቤ ጋር በማስማማት ሁለቱም በጥምረት የሚጓዙበትን ሁኔታ ማሳደግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

"በጣም የሚያሳስበኝ የወጣቶች ሁኔታ ነው" ካሉ በኋላ ር.ሊ.ጳ. ሲቀጥሉ "ምክንያቱም አብዛኞቹ ከቤተሰብ ጋር ግንኙነት ስለሌላቸው ሲሰቃዩ የተቀሩት ደግሞ ለራሳቸው ብቻ የተተወና የተገለለ ዓይነት ሕይወት ይመራሉ" ካሉ በኋላ በተመሳሳይ መልኩ በምዕራቡ ዓለም የሚታየው በድሃና ሀብታም መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ መምጣት፣ ፕላኔታችንን ስለመንከባከብ፣ ከጽንሰት እስከ ሞት ድረስ ያለው የሰው ልጅ መብት፣ የመማርና የቤተሰብ መብትን በመጥቀስ ቤተ ክርስቲያን፣ መንግሥትና ሕዝቡ ለነዚህ ዕሤቶች መተባበር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

<<ድምጿን የማታሰማ ቤተ ክርስቲያን ምንም የማትጠቅም ናት>> ሊቀ ጳጳሳት ሪቬራ

 

ሜክሲኮ ሲቲ ጳጉሜን 4 (CNA) - የሜክሲኮ ሲቲ ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል ኖቤርቶ ሪቬራ ካሬራ በከተማዋ ጽንስ ማስወረድ ሕጋዊ እንዲሆን የሀገሪቱ ክፍተኛ ፍ/ቤት መወሰኑን በማስመልከት ወንጀል መፈጸም ሕጋዊ ሲሆን ቤተ ክርስቲያን ዝም ማለት እንደማትችል አስታወቁ።

በእሑድ ዕለት ስብከታቸው ካርዲናሉ <<ድምጿን የማታሰማ ቤተ ክርስቲያን ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሰው ምንም የማትጠቅም ናት። ለዓለማችን ትልቅ ክፋት ተልፈስፍሰን ግድ የለሽ መልስ መስጠት አንችልም፤ መደረግ ያለበትን በመጠቆምና ለዚያም ዝግጁነታችንን በመግለጽ ድምጻችንን ከፍ አድርገን በአንድነት ምላሽ መስጠት አለብን>> ብለዋል።

በመቀጠልም <<ቃየል ለእግዚአብሔር የሰጠውን ምላሽ ዛሬም እኛ ማስተጋባትና መቀጠል የለብንም። <እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን?> ማለት የለብንም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በዚያን ጊዜ ቃየልን እንደተናገረው እኛንም <የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮሃል> ይለናል በማለት በቤተሰብ፣ በቤተ ክርስቲያንና በኅብረተሰብ ውስጥ ለውጥ የማምጣት ግዴታ ቤተ ክርስቲያን እንዳለባት በማስመር ተናግረዋል።

<<ታግቼ በነበርኩበት ወቅት የር.ሊ.ጳጳስ ንግግር ለኔ እንደ ብርሃን ነበር>> - ኢንግሪድ ቤታንኮርት

የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ለመሆን ዕጩ  የነበረችውና በቅርቡ ከኮሎምቢያውያን አጋቾቿ ነጻ የወጣችው ኢንግሪድ ቤታንኮርት ነሐሴ 26 ቀን 2000ዓ.ም. ከር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክት ጋር ከተነጋገረች በኋላ ባደረገችው ጋዜጣዊ መግለጫ <<በተስፋ ቁርጠቴና ኀዘኔ መካከል ሳለሁ ር.ሊ.ጳ. የኔን ስም ሲናገሩ በሬድዮ ስሰማ በዚያን ወቅት ድምጹ ለኔ ልክ እንደ ብርሃን ነበር።>> በማለት በአማዞን ደን ውስጥ በእገታዋ ወቅት የተሰማትን ሁኔታ አስረዳች።

200 ለሚሆኑ ጋዜጠኞች፣ ዲፕሎማቶችና የጣልያን ባለሥልጣኖች ከቤኔዲክት 16ኛው ጋር ስለነበራት ቆይታም ስትገልጽ የእገታ ታሪኳን ለር.ሊ.ጳ. እንደተናገረችና  እሳቸውም <<እግዚአብሔርን ፈቃድህ ይሁን ብለሽ ስለጠይቅሽው ወደርሱ መጸለይን አውቀሽበታል>> እንዳሏትም ተናግራለች። <<ወደ ደን ውስጥ በተወሰድን ጊዜ ሁሉ ያለቀልን በሚመስለን ወቅት ይህንን ነገር ከርሳቸው መስማት የፈጠረልኝን ስሜት መግለጡ በጣም ያዳግተኛል>> ካለች በኋላ ከእገታዋ ነጻ ስትሆን ር.ሊ.ጳጳሳትን ለመጎብኘት መመኘቷንና ያም ህልሟ መፈጸሙን ገለጠች።

ቤታንኮርት መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እግዚአብሔር ቀስ በቀስ እንድትቀርብ እንዳገዛትና ለችግሮቻችን ሁሉ መፍትሔ እንደሆነ በመመስከር << ሰኔ 1 ቀን ካቶሊካ ሙንዲያል የተባለውን የEWTN ካቶሊክ ሬድዮ ሳዳምጥ ኢየሱስ ለአንዲት ቅድስት ራሷን ለኢየሱስ ቅዱስ ልብ ከሰጠችና ሦስት ቅድመ ሁኔታዎችን ካሟላች የሆነ ነገር ቃል እንደገባላት ስሰማ እነዚያ ሁኔታዎች ቀጥታ እኔን የሚመለከቱ ነበር። እኔም <ኢየሱስ ሆይ! ከእገታው አሁን ነጻ ልሁን አልልህም ግን ብርታት ይሆነኛልና መቼ ነጻ እንደምሆን እንዳውቀው እጠይቅሃለሁ፤ ይህ ከሆነ እኔም ራሴን ለአንተ እሰጥሃለሁ> በማለት ጸለይኩ>> በማለት እንባ የተናነቀው ንግግር በማድረግ ራሷን ግን በምን መልኩ መስጠት እንዳለባት እንደማታውቅ ለር.ሊ.ጳጳሳት መናገሯንና እሳቸውም <<ራሱ ክርስቶስ ይገልጥልሻል>> እንዳሏትም ለአድማጮቿ አልሸሸገችም።

ቤታንኮርት ይህን ጋዜጣዊ መግለጫ እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ለኮሎምባውያን አጋቾቿ ለመላው ኮሎምባውያን ሰላምና ጥቅም የኃይልና ዓመጽ መንገድን እንዲያቆሙ የፍቅር፣ የምሕረትና የሰላም ጥሪ በማስተላለፍ፤ እሷም ከነዚህ የስቃይ ዓመታት በኋላ ድምጽ አልባ ለሆኑት ድምጽ መሆን ተልእኮዋ መሆኑን በመግለጽ ደምድማለች።

የሕንዱ ካርዲናል በክርስቲያኖች ላይ የሚደረገው ጥቃት እንዲቆም አሳሰቡ

ነሐሴ 24 (CNA)- የቦምቤይ ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል ኦዝዋልድ ግራሺያስ በቅርቡ በሕንድ ውስጥ የተጠናከረውን ኢክርስቲያናዊ  ዓመጽ ምክንያት በማድረግ በሀገሪቱ የሚገኙ ካቶሊካውያን ወደ ክርስቶስ መስቀል ልዩ መንፈሳዊነትና ጸሎት በማዘውተር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው የጥቃቱን መሠረት ማወቅ እንደሚያስፈልግና ወደፊትም ተመሳሳይ ሁኔታዎች እንዳይፈጠሩ  ሁኔታዎችን በሚገባ ማጤን እንደሚያስፈልግ አሳወቁ።

ካርዲናሉ ከቫቲካን ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ መጻኢ ሁኔታውን ስለማያውቁ ክርስቲያኖች በአሁኑ ሰዓት ስጋት የገባቸው መሆኑን ገልጸው እስካሁን ድረስ ሂንዱ አክራሪዎች  ሀያ አምስት ቤተ ክርስቲያናት ማፈራረስቸውንና  ክርስቲያኖችን ይበልጥ ለማጥቃት የጠላትነት ስሜትን እያሳደጉ መምጣታቸውን በመጠቆም መንግሥት በአስቸኳይ ጣልቃ እንዲገባ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል።

ቤተ ክርስቲያን በሕንድ የተለያዩ ሰላማዊ ውይይቶች ለማድረግ ጥረት ከማድረጓ የተነሣ በብዙ ቦታዎች ጥሩ ውጤት ቢገኝም ኦሪሳ በሚባለው አካባቢ ግን ይህ ውይይት ፍሬያማ ሊሆን እንዳልቻለም ካርዲናሉ ጠቁመው በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚርሰው ስደት ቤተ ክርስቲይን የሰው ልጅ እንደ ሰው ልጅነቱ ይታይ በሚለው ጽኑ አቋሟ መሆኑንና አክራሪዎቹ ቤተ ክርስቲያን ከድሆች ጋር መወገኗንና ለሰው ልጅ መብት መቆሟን አጥብቀው እንደሚቃወሙም አስታውቀዋል።

በመጨረሻም ካርዲናሉ ምንም እንኳ ሁኔታዎች እንደዚህ ቢሆኑም << የሕንድ ክርስቲያኖች ተስፋቸውን በኢየሱስ ትንሣኤ ላይ እንደ ሚያደርጉና ሁል ጊዜም ቢሆን ድሉ የክርስቶስ መሆኑን እንደሚያውቁ>> ገልጸዋል።

ቻይና ሌላ ተጨማሪ ጳጳስ አሰረች

(Zenit.org)(CWNews.com) - ትእይንታዊ ከነበረው የኦሎምፒክ መዝጊያ ሥርዓት ትንሽ ቀደም ብሎ የቻይና ባለሥልጣኖች በፊት ከታሰሩ ስድስት ጳጳሳት በተጨማሪ አንድ ጳጳስ ማሰራቸው ተዘገበ።

ፖሊሶች ጳጳሱን የወሰዷቸው ከካቴድራላቸው ሲሆን ለምን እንዳሰሯቸውና ወዴት እንደወሰዷቸው ግን በግልጽ ያሳወቁት ነገር የለም። አሁን የታሰሩት የ73 ዓመት ዕድሜ ያላቸው አቡነ ጁሊየስ ጃ ጥሩ እንቅስቃሴ ያለውና ከ100,000 በላይ የሚሆኑ ካቶሊካውያን ያሉት የሄቤይ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ሲሆኑ ከ1955-1970 ዓ.ም. ለ15 ዓመታት በወህኒ ቤት ያሳለፉና ከዚያም በኋላ ቢያንስ ለ12 ጊዜያት ዳግም እየታሰሩ የተፈቱ እንዲሁም ከ1981 ዓ.ም. ወዲህ ደግሞ የቁም እስረኛ የነበሩ ጳጳስ ናቸው።

የቻይና መንግሥት የኦሎምፒክ ውድድር እስኪጠናቀቅ ድረስ ማናቸውም ክርስቲያኖች ሕዝባዊ አምልኮ ማለትም ተሰባስበው እንዳይጸልዩ ያስጠነቀቀ ሲሆን አቡነ ጁሊየስ ግን በእመቤታችን ፍልሰታ በዓል ዕለት አንድ ሺህ ከሚጠጉ ካቶሊካውያን ምእመናን ጋር መሥዋዕተ ቅዳሴ አድርገው እንደነበር ታውቋል።

ከኦሊምፒኩ መጠናቀቅ ጋር የመገናኛ ብዙኃን ትኩረት ከቻይና በራቀ መጠን መንግሥት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንን የወትሮ እንግልት በፍጥነት እንደሚጀምር የአካባቢው ካህናትና ምእመናን አስቀድሞም የታወቀ ነገር መሆኑን ይናገራሉ።

የካህኑ መገደል ሕንዳውያን ክርስቲያኖችን አሳዘነ

The Catholic Herald - ነሐሴ 10 ቀን 2000 ዓ.ም. በውል ያልታወቁ ሰዎች አንድ ካህንን ከሞተር ሳይክል ጎትተው በዘግናኝ ሁኔታ ሰባብረውና ወግተው ከገደሉ በኋላ በሕንድ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ይበልጥ ለጥቃት ስጋት የተጋለጠች መሆኗ ተገለጠ።

ባለፉት አሥር ዓመታት ጥቃት እየደርሰባቸው የተቸገሩ ሕንዳውያን ክርስቲያኖች ተቃውሟቸውን ሲገልጹ።

የ38 ዓመት ዕድሜ የነበራቸው አባ ቶማስ ፓንዲፓሊል በሂንዱ ሃይማኖት መሠረት ከሰው እንዲገለሉ ከተደረጉ ሰዎች ጋር ይሠሩና በበጎ አድራጎት ያግዙ ስለነበር ገዳዮቻቸው አክራሪ ሂንዱዋውያን ሊሆኑ እንደሚችሉም ተገምቷል።

ካህኑ ቅዳሴ ለመቀደስ በሞተር ሳይክል በሚጓዙበት ጊዜ በመንገድ አስቁመዋቸው ጎትተው በማውረድ የገደሏቸው ሲሆን በአስክሬኑ ላይ በተካሄደውም ጥናት መሠረት የካህኑ እጅና እግር የተሰባበሩ ሲሆን 18 ቦታ ላይም ተወግተውና ዓይናቸውም በሚዘገንን ሁኔታ በስል ነገር ተጎልጉሎ እንደነበር ፖሊስ አስረድቷል። ሲሆንለቅዳሴ ይጠብቋቸው የነበሩ ደናግል የካህኑ ያለመምጣትን ካሳወቁ በኋላ ነበር አስክሬናቸው ወንጀሉ ከተፈጸም በማግስቱ ሊገኝ የቻለው።

ይህ ሁኔታ በአገሪቱ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው ወንጀል ከፍተኛ መገለጫ መሆኑን የአካባቢው ሊቀ ጳጳሳት ከገለጹ በኋላ ይህ አረመኔያዊ ድርጊት ሕንዳውያን ካቶሊኮችን እንዳስደነገጥና እጅግም እንዳሳዘነ ገልጸዋል። <<አባ ቶማስ ሰማዕት ናቸው፤ ሕይወታቸውን ለድሆችና ከኅብረተሰቡ ለተገለሉ ሰዎች ሰውተዋል። በከንቱና ለከንቱ ዓላማ አልሞቱም፤ ይልቁንም ደማቸው በሕንድ ለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን በተለይም ለዚህ አካባቢ ክርስቲያኖች ማበብ ምክንያት ይሆናል>> በማለትም የሰማዕትነት ሞት ትርጉምን አስረድተዋል።


ክርስቲያኖች ድሆች የሂንዱ እምነታቸውን እንዲቀይሩ በመደረግ ላይ ነው በሚል ሰበብ በሂንዱዎችና በክርስቲያኖች መካከል ጥሩ የሆነ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጥፋት ላይ ይገኛል።

 

ሊቀ ጳጳሳቱ በመጨረሻም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሰውን እምነት ለማስካድና ለማስቀየር ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንደማታደርግ ገልጸው፤ ካህናትና መነኮስን እህቶች ዘወትር ከተናቁና ከተወገኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመተባበር እንደሚሠሩና እነዚህንም የተገለሉ ሰዎች ወደ ተገቢው የኑሮ ደረጃ እንዲደርሱ ማገዛቸውን እንደሚቀጥሉም አስረድተዋል።

 

ር.ሊ.ጳጳሳት የቅድስት ተሬዛ ዘሕፃን ኢየሱስን ወላጆች ብፅዕና አጸደቁ

ቫቲካን -(CNS)- ቤኔዲክት 16ኛው የቅ.ተሬዛ ወላጆችን ሉይስ እና ማሪየ ዘሊየ ጉወሪ ማርቲንን ብፁዕና አጸደቁ።

የፊታችን ጥቅምት መጀመሪያ ላይ በልጃቸው ማለትም በቅድስት ተሬዛ ስም በተሰየመውና ፈረንሣይ ውስጥ የትውልድ ቦታዋ በሚገኘው ትልቅ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚደረግ መሥዋዕተ ቅዳሴ ላይ የወላጆቿ ብፅዕና እንደሚታወጅ ታውቋል።

የብፅዕናቸው ሂደት የተጀመረው ቀደም ብሎ ቢሆንም በ1986 ዓ.ም. ክቡራን ተብለው ተሰይመው በነርሱ አማላጅነት አንድ ተአምር እስኪደረግ የተጠበቀ ሲሆን በ1994 ዓ.ም. በሚላን ከተማ ጣልያን አገር ውስጥ ገና ሲወለድ ከሳንባው ሁኔታ የተነሣ የመተንፈስ ችግር የነበረበት አንድ ሕፃን ልጅ በእነሱ አማላጅነት ከተፈወሰ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ጥናት ስታደርግ ቆይታ በሐምሌ ወር ተአምርነቱን ካረጋገጠች በኋላ ብፅዕናቸው ተቀባይነት አግኝቷል።

አባቷ ከ1815-1886 እናቷ ደግሞ ከ1823-1869 የኖሩ ሲሆን ባጠቃላይ ዘጠኝ ልጆች የነበሯቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አምስቱ የምንኩስና ሕይወትን መርጠው የኖሩ ናቸው።

 

መነኮሳኑ ተሸለሙ


http://www.totalcatholic.com/tc/ በአውስትሪያ ቪየና ዉብስ የሚገኙ መነኮሳን ባሳተሙት 'Chant' (ዜማ) በተሰኘው አልበማቸው የዘንድሮ 2008 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ ፖፕ ሙዚቃ ኮከቦች መሆናቸው ተገለጸ።

በአውሮፓ ውስጥ ከሚገኙት የሲታውያን ገዳማት ሁሉ ይበልጥ በቀጣይነት በመነኮሳን የተሞላ ገዳም መሆኑ የሚነገርለት ስቲፍት ሄሊገንክሩዝ የተባለው ይኸው ገዳም በሙዚቃ ዓለም ስኬቱ አልበሙን ባሳተመ በአሥር ሳምንታት ውስጥ ብቻ ከራሳቸው አገር አስትሪያ የደብል ፕላቲኒየም ፣ ከእንግሊዝ፣ ከፖላንድና ቤልጂየም የወርቅ ዲስክ ሲያገኝ ከአየርላንድም የብር ዲስክ ተሸላሚ ሆኗል።
በጎርጎርያውያን የቤተ ክርስቲያን ዜማ የተሞላው ይህ አልበም በአስትሪያና በእንግሊዝ በፖፕ የሙዚቃ ቻርት ውስጥ ታዋቂ ከሆኑት የሙዚቃ ሰዎች ሥራ  እስካሁን ድረስ በመሪነትና በተፎካካሪነት ደረጃ ላይ መገኘቱም ታውቋል።
ይህን የመነኮሳኑን ዜማ አልበም ያሳተመው Universal Music (UCJ) በመጪው ኅዳር ወር የገና (የጌታችን ልደት) ዜማን ጨምሮ ልዩ እትም እንደሚያሰራጭም ዘግቧል።

 

በላቲን አሜሪካ የካህናት ቁጥር እየጨመረ ነው

ቦጎታ- ኮሎምቢያ(Zenit.org) - ምንም እንኳን የክህነት ጥሪ ቁጥር እንዳይጨምር የሚፈታተኑ ሁኔታዎች እየበዙ ቢመጡም በላቲን አሜሪካና በካሪቢያን የካህናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በአምስት ዓመታት ውስጥ በሃያ ሁለት ሀገራት ከተደረገ ጥናት መታወቁን የላቲን አሜሪካ ጳጳሳት ምክር ቤት ቡድን አስታወቀ።
ባጠቃላይ 11.93% የሰበካውያን ካህናት ቁጥር ሲጨምር (ከነበረው 37,884 ወደ 42,405) የማኅበራት ካህናት ቁጥር ደግሞ በጣም አነስተኛ መቀነስ አሳይቷል (ከ 24,186 ወደ 23,945)።

በነዚህ አምስት ዓመታት ውስጥ 10 አዲስ አሥር ካህናት በሆኑ ቁጥር አራት ካህናይ የመሞት ወይም ደግሞ ራሳቸውን ከክህነት አገልግሎት የማግለል ሁኔታ ነበር ማለት ነው። በዚህ በሃይ ሁለት ሀገራት በተደረገው ጥናት መሠረት በአምስቱ ዓመታት ውስጥ 1,080 ካህናት አገልግሎታቸውን እንደተዉ ሲታወቅ በበሊዘ እና ፑየርቶ ሪኮ ብቻ ምንም ካህናት አገልግሎታቸውን እንዳልተዉ ተዘግቧል።  

በሰበካውያን ካህናት በኩል በጥሩ ሁኔታ የቁጥር መጨመር የታየው በኒካራጓ እና ጓቴማላ ሲሆኑ ብራዚል፣ ሜክሲኮና ኮሎምቢያ ብዙ ሢመተ ክህነት ያሳዩ ሀገሮች መሆናቸው ታውቋል። በተመሳሳይ ጥናት መሠረትም የደናግላን እህቶች (እማሆዮች) ቁጥርም የ0.91% አነስተኛ እድገት አሳይቷል።

በመጨረሻም የጥናት ቡድኑ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የቁጥሩ መጨመር ላይ ሳይሆን ካህናትንና መነኮሳንን ለመኮትኮት የሚደረገው ጥረት ላይና ለጥሪ አጋዥና ጎጂ የሆኑ ነገሮች እንዲስተዋሉ በማሳሰብ ዘገባውን ደምድሟል።



ካቶሊካዊ አቡኑ ሙስሊም ካልሆኑ ጥቃት እንደሚሰነዘርባቸው የሙስሊም <<ጦረኞች>>ዛቱ

ማኒላ ሐምሌ 16 (CNA) - በደቡብ ፊሊፒን የባሲላን አውራጃ ካቶሊካዊ ጳጳስ ራሳቸውን <<የሙስሊም ጦረኞች>> ብለው ከሚጠሩ ቡድኖች ጳጳሱ ካልሰለሙ ወይም ለነርሱ ቀረጥ ካልከፈሉ በስተቀር በሕይወታቸው ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝሩባቸው የሚገልጽ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ተገለጸ።

በተያያዘ ዜናም ባለፈው ሳምንት ከዚያው አካባቢ ታፍነው የተወሰዱትን አምስት ሰዎች ለማስመለስ የአካባቢው ባለሥልጣናት ጥረት እያደርጉ ሲሆን፤ ከአምስቱ ታፋኞች ካቶሊካውያን ውስጥ ሁለቱ ሕፃናት መሆናቸውም ታውቋል።

የዛቻ ደብዳቤ የደረሳቸው አቡነ ማርቲን ጁሞአድ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሬዲዮ ጣቢያ የደብዳቤውን ግልባጭ ልከው የተነበበ ሲሆን፤ መልእክቱ የተላከው በአንድ ተማሪ በኩል ለትምህርት ቤቱ ጸሐፊ ከዚያም ለርሳቸው እንዲደርስ በማድረግ እንደሆነ ተነግሯል። የደብዳቤው ጸሐፊዎች ራሳቸውን <<ከቁራን ሕግ በስተቀር ለሌላ ምንም ዓይነት ሕግ የማይገዙ ሙስሊም ጦረኞች>> መሆናቸውን በመግለጽ ጳጳሱ በሙስሊሞች አካባቢ እስካሉ ድረስ ወደ ሙስሊምነት መለወጥና ጂዚያ በመባል የሚታወቀውን የነርሱን ቀረጥ መክፈል እንደሚኖርባቸው ይህን ካላደርጉ <<ኃይል፣ መሣሪያና ጦርነት>> እንደሚጠቀሙ ገልጸዋል። እንዲሁም በሌሎች የፊሊፒንስ ከተሞች የደረሱትን የቦምብ ፍንዳታዎች በማስታወስ በወታደራዊ ጥበቃም ቢሆን አቡኑ ሊድኑ እንደማይችሉ ዝተዋል።

በአካባቢው ያሉ ካቶሊካውያን ላይ የጥቃት ዛቻዎች እየተሰነዘሩና ስጋት እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ ከጥቂት ቀናት በፊት ማለትም ሐምሌ 14 በማኒላ ከተማ በተደረገ የካቶሊካዊት አቡናትና ሙስሊም ምሁራን ጉባኤ ላይ ጥቃትና ዛቻን ሁለቱም ወገኖች አውግዘዋል። እንዲሁም ሙስሊማን ምሁሮች <<ሕይወትን የሰጠው ፈጣሪ ነው፤ ሥልጣንም ያለው እርሱ ብቻ>> ካሉ በኋላ በእስላም ሕግ በሚተዳደር አገር ውስጥ የሚኖር ማንም ሙስሊም ባይሆንም ጂዚያ የመክፈል ግዴታ እንዳለበትና ይህ ክፍያ ግን በእስላማዊ ሕግ ለማይተዳደር አገር እንደማይሠራ ተወያይተው እንደነበርም ተዘግቧል።

 የዓለም ወጣቶች ስብሰባ ሳምንት መደምደሚያ ቅዳሴ

ሲድኒ ሐምሌ 13   (CNA) - በአውስትራልያዋ ዋና ከተማ ሲድኒ ውስጥ ሲካሄድ የሰነበተው ዓለም አቀፍ የካቶሊካውያን ወጣቶች ስብሰባ ሳምንት መደምደሚያ ቅዳሴ ለአገሪቱ በተሳካ መልኩ የተከናወነ ሲሆን፤ በቅድሴ ደረጃም ይሁም ከቅዳሴ ውጭ በሆኑ ክንዋኔዎች በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ ብዙ ሰው የተሳተፈበት ይህን መሰል ጊዜ እንዳልነበረ ተገለጸ።

በዚሁ ቅዳሴ ላይ 26 ካርዲናላት፣ 420 ጳጳሳት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ካህናትና ከስድስት መቶ ሺ የማያንሱ ወጣቶች መሳተፋቸውም ተዘግቧል። ይህንን የወጣቶች ጉባኤ ቃል አቀባዩ ሲገልጹ <<ሙሉ ሳምንቱ እምነትና እግዚአብሔር ባጠቃላይ በወጣቶች ዘንድና በአውስትራልያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሕያው እንደሆነ ያሳያል>> ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክት 16ኛው በቅዳሴው ስብከት ለወጣቶቹ <<ዓለም ይህን መታደስ ይፈልጋል፤ ባብዛኛው በኅብረተሰባችን ዘንድ ከቁሳዊ ብልፅግና በተጓዳኝ የመንፈሳዊ ሕይወት በርሃነት ፣ ውስጣዊ ባዶነትና ስም የለሽ ማለትም ይህ ነው ብለን መለየት የማንችለው ፍርሃት፣ የተስፋ ቁርጠት መቃወስ እየተስፋፋ ነው፤ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቤተ ክርስቲያንም መታደስ ይኖርባታል፤ መላ ወጣቶችም ያስፈልጓታል>> ካሉ በኋላ ከሦስት ዓመታት በኋላ የሚደረገው ይህን መሰል የወጣቶች ጉብዔ በስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ እንደሚደረ በመግለፅ ደምድመዋል።

 

 

የቤኔዲክት 16ኛው የስልክ አጭር ጽሑፋዊ መልእክት ለወጣቶች

“ወጣቱ ጓደኛዬ ሆይ! የታላቁ የእግዚአብሔር ስጦታና፣ የክርስቶስ መንፈስ በአንተ ላይ ስላለ፤ እግዚአብሔርና ሕዝቡ ከአንተ ብዙ ይጠብቃሉ።” ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ በሲድኒ ለተሰበሰቡት ከ 140,000 በላይ ለሚሆኑ ከዓለም ሁሉ ለተሰበሰቡ ካቶሊካውያንና ካቶሊክ ያልሆኑ ወጣቶች የጻፉት አጭር መልእክት (sms)

 

በፈረንጆቹ 2007 ዓ.ም. ሀገረ ስብከቶች ሠላሳ ሚሊየን የሚጠጋ የአሜሪካ ዶላር አስተዋፅዖ አደረጉ

ሐምሌ 2, 2000 ዓ.ም. (Zenit.org) - በጀርመን፣ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካና በጣልያን የሚገኙ ሀገረ ስብከቶች ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ቅድስት ወንበር ካወጣችው የገንዘብ ወጪ ከፍተኛውን ድርሻ መሸፈናቸው ተገለጸ።

የቅድስት መንበር የቁጠባና አስተዳደር ጉዳዮች ምክር ቤት ከስብሰባው በኋላ እንዳሳወቀው ዓለም አቀፍ ሀገረ ስብከቶች ባለፈው ዓመት በጠቅላላው $29,552,843 ለቅድስት ወንበር አስተዋፅኦ ሲያደርጉ፤ ከዚህ ገቢ ውስጥ የጀርመን ሀገረ ስብከቶች 31.57%፣ ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ 28.31% ጣልያን 18.9% አውስትሪያ፣ ካናዳና ስፔን እያንዳንዳቸው 3% እንዲሁም ኮሪያ 2.31% ሸፍነዋል።
ምክር ቤቱ አያይዞም ይህ የዓመቱ ጠቅላላ ገቢ ከሌላ ዓመታት ዝቅ ያለ መሆኑን ገልፆ ለዚህም ምክንያቱ ቅድስት ወንበር አብዛኛው ገቢዋ በዶላር ሲሆን ወጪዋ ደግሞ በዩሮ ስለሆነ የአሜሪካ ዶላር ምንዛሪ እየቀነሰ መምጣቱና የዩሮ ምንዛሪ ደግሞ መጨመሩ መሆኑን አሳውቋል።

 

ካህን አስመሳዩ በቫቲካን ቅ. ጴጥሮስ ውስጥ ተያዘ

Independent Catholic News ሰኔ 30- ልብሰ ክህነት በመልበስ ራሱን ካህን አስመስሎ በቅ. ጴጥሮስ ቤ/ያን ውስጥ ምሥጢረ ኑዛዜ ለማስደረግ ሲል አንድ ግለሰብ መያዙን የቫቲካን ደኅንነት ቡድን ገለጸ።

በቫቲካን ከተማ የሚያገለግሉ አንድ የፍርድ ቤት ዳኛ ለኦዘርቫቶሬ ሮማኖ ጋዜጣ እንደገለጹት ሰኔ 28 ቀን የተያዘው ይህ ሰው ከአለባበሱም በተጨማሪ የያዛቸው ሰነዶችም ካህንነቱን የሚመሰክሩ እንደነበሩ ተናግረዋል። እንዲሁም "ለማናዘዝ ወደ መንበረ ኑዛዜ ውስጥ ሊገባ ሲል ያሳያቸው ከነበሩት ሁኔታዎች በመነሣት ካህን ያለመሆኑን ለመረዳት ለድኅንነት ቡድናችን ምንም ጊዜ አልወሰደባቸውም" ብለዋል ዳኛው።

ሰውዬው ወደ መንበረ ኑዛዜው እንዳይገባ በማስቆም ግለ ሰነዱን በደኅንነቶች ሲጠየቅ መረጃዎቹ በቫቲካን በኩል ያለፉና ሕጋዊ የሚመስሉ ቢሆኑም እና በርግጥም ካህን መሆኑን ቢያሳዩም የተቆጣጣሪዎቹ ስጋት ግን ከዚያም በላይ ስለነ