የገዳመ ሲታውያን ማርያም ጽዮን አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
በኢትዮጵያ ውስጥ ማኅበራችን ባሉት አራት ገዳማት ከአፀደ ሕጻናት እስከ ተግባረ እድ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶችን ያስተዳድራል። ከነዚህም ትምህርት ቤቶቻችን መካከል አንዱ <<የገዳመ ሲታውያን ማርያም ጽዮን አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት>> በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ካቶሊካዊ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር ሆኖ በሲታውያን ማኅበር መነኮሳን የሚተዳደር ካቶሊካዊ ትምህርት ሲሆን የሚገኘውም በምሥራቃዊ አዲስ አበባ በቦሌ ክፍለ ከተማ ነው።
ማርያም ጽዮን ትምህርት ቤት የተመሠረተው በ1975 ዓ.ም. ሲሆን የተመሠረተውም በሲታውያን መንኮሳን በአንድ አነሰተኛ ቤት ውስጥ የአካባቢውን ሕጻናት ሰብስቦ ያለምንም ክፍያ በማስተማር ነው። ብዙም ሳይቆይ አሁን ካሉት አምስት ህንፃ /ብሎክ/ የመጀመሪያው ተገንብቶ ሥራውን መሥራት ጀመረ።
የገዳመ ሲታውያን ማርያም ጽዮን ካቶሊካዊ ትምህርት ቤት ዓላማ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕጻናትን ያለምንም ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ጎሳዊና ፆታዊ ልዩነት ተቀብሎ ሰብአዊ፣ ግብረገባዊና ፈሪኀ እግዚአብሔር የተሞላ እውቀት እንዲገበዩና አገራቸውን በቅንነት የሚያገለግሉ ዜጎችን መፍጠር ነው።
በዚህ ዓመት ማለትም በ2000 ዓ.ም. የትምህርት ቤቱ ተማሪዎችና መምህራን ቁጥር እንደሚከተለው ነው፡
የመጀመሪያ ሳይክል ማለትም ከ1ኛ እስከ 4ኛ 495 ተማሪዎች
የሁለተኛ ሳይክል ማለትም ከ5ኛ እስከ 8ኛ 595 ተማሪዎች
ጠቅላላ የተማሪዎች ቁጥር ድምር 1089 ሲሆን፤
መምህራን 47
ሕንፃ 5 ብሎክ
የትምህርት ቤቱ ክፍለ ጊዜ የሙሉቀን መርኀ ግብር የተከተለ ነው።

የገዳመ ሲታውያን ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ካቶሊካዊት አፀደ ሕፃናት፣ አንደኛና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት