የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ . “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛ ተከታታይ መጽሓፍ

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 1559

መጋቢት 2 2003 ዓ.ም. “ኢየሱስ ናዝራዊ” የተሰኘው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛ መድበል መጽሐፍ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ቅዱስ ማኅበር ተወካይ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦውሌት፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ፕሮፈሶር ክላውዲዮ ማግሪስ እና የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ጉዳይ ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በይፋ ለንብባብ በቅቷል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. “ኢየሱስ ናዝራዊ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሐፍ ሁሉም ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ለመገናኘት ለሚፈልግ የሚጠቅም መሆኑ ሲገለጥ፣ “ኢየሱስ ናዝራዊ” ሁለተኛው መጽሐፍ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰላም ንጉሥ መሆኑን የሚገልጠው ወደ ኢየሩሳሌም መግባት ከሚለው ታሪክ በመጀመር እንደ አንድ አብዮታዊ ፖለቲከኛ ጸረ ክርስቶስ በሆነው አመጽ ላይ የተመሠረተ እንዳልሆነ ከሚገልጠው ታሪክ በመንደርደር ቅዱስ አባታችን፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥነ ፍጻሜን የሚገልጥ ንግግር በማስቀደም ስለ የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ መፈራረስ እንዲሁም ስለ ፍርድ ቀን እና የዓለም ፍጻሜ በመናገር፣ “እግዚአብሔር የታሪክ ጌታ የሆነው ለሰው ልጅ የሰጠው ነጻነት ትርጉም እና ኢየሱስ እውነተኛ መቅደስ የድንጋዩን ቤተ መቅደስ መቅደሙን የመሰከረ እሱ ራሱ እውነተኛ እና አዲስ ቤተ መቀደስ መሆኑና በእርሱ አማካኝነትም እግዚአብሔር እና ዓለም እንደሚገናኙ አብራርተዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን እድፈት ለማንጻት መለኮታዊ ክብሩን ትቶ
ራሱን ዝቅ በማድረግ የሁሉም አገልጋይ በመሆን በማንም የሃይማኖት ታሪክ ዘንድ የሌለ አዲስ እርሱም ልብን የሚያነጻ ሕግ እና ሥርዓት ሳይሆን እምነት መሆኑን የሚገልጥ አዲስ ሥር ነቀላዊ ለውጥ በቃል እና በሕይወት በማስተዋወቅ፣ አንዳንድ ነጻ የቅዱስ መጽሓፍ ተንታኞች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንጻት ሥርዓት በግብረ ገብ እንደ ተካው ይናገራሉ፣ እንዲህ ቢሆን ኖር ክርስትና መሠረታዊ ትርጉሙ እና መግለጫው ግብረ ገብ ሆነ በቀረ ነበር። ስለዚህ አዲስ ሕግ፣ አንድ አዲስ ሕግ ወይንም ደንብ ሳይሆን የመንፈስ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ የሚሰጠው አዲስ ውስጣዊነት ነው። ክርስትና ጸጋ ነው። ጸጋ በመሆኑም እያደገ እና ከፍ ከፍ የሚል በተሰጠው ጸጋ መሠረት በንቃት የሚኖር እና የሚተገበርም መሆኑ ቅዱስ አባታችን በደርሱት መጽሓፍ በጥልቀት ያስረዳሉ።
በመቀጠልም ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ስለ ይሁዳ ሲተነትኑ፣ እነዚህ ሁለቱ ሰዎች ሁላችን የተሰጠንን ጸጋ በሁለት ዓይነት መንገድ ለመኖር እና ተግባር ላይ ለማዋል እንደሚቻል የሚያመለክት መሆኑን ሲገልጹ ጴጥሮስ ክርስቶስን ክዶ ሲያበቃ ነገር ግን በእውነት በመጸጸት በምሕረት ላይ ያለውን እምነት ይመሰክራል፣ ይሁዳ ምንም’ኳ በፈጸመው ግብረ ክህደት ቢጸጸትም ነገር ግን በምሕረት ላይ እምነት የሌለው በመሆኑ ጸጸቱ ተስፋ ቢስነት ሆኖ ቀርቷል። ስለዚህ የቤተ ክርስትያን እና የቅዱሳት ምሥጢራት ተካፋይ ማኅበረሰብ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ እና ደም የሚቀበሉ ናቸው። ሆኖም ስንቱ ነው ይኸንን ምሥጢር ቢቀበልም ሲክደው የሚታየው የሚል ጥያቄን መመለስ እንዳለበት ጠቁመዋል።
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክህነታዊ ጸሎት፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ የዓለምን ኃጢአት የሚያነጻ በመሆን የመላ ታሪክ ትርጉም እርሱም ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ የሚለውን መሠረት ያደረገ መሆኑ ያረጋግጣል።
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻው ማዕድ፣ በሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላውያን (ማቴዎስ፡ ማርቆሰና ሉቃስ) እና እንዲሁም በዮሐንስ ወንጌል ጭምር፣ በተለይ ደግሞ በዮሓንስ ወንጌል የመጨረሻ የእራት ማዕድ፣ ከፋሲካ ዋዜማ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የተፈጸመ ሲሆን፣ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው በፋሲካ ቀን ሳይሆን በፋሲካ ዋዜማ ቀን መሆኑ ይገልጣል። ስለዚህ እወነተኛ የእግዚአብሔር በግ መሆኑ በመግለጥ የፋሲካ እውነተኛ ትርጉሙ እራሱን አሳልፎ በመስጠት ይገልጣል።
በጌተሰማኒ በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሱን አሳምኖ እንዳንተ ፈቃድ በማለት ኃጢኣት የሌለው ሆኖ በኃጢኣት ድቅድቁን ጨለማ በማለፍና በራሱ ላይ በማኖር መስቀልን ተሸከመ። ሆኖም ጌታችን መስቀል እንዳይሸከም ጴጥሮስ ያሳየው ጥረት ብዙውን ግዜ በክርስቲያኖች እንደውም አንዳንዴ ቤተ ክርስትያንም ሳትቀር የሚያጋጥማት ፈተና ነው። ስለዚህ ይህ የማንቀላፋቱ ጉዳይ እንዳያጋጥም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሚለው መንቃትን ይጠይቃል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍርድ ፊት መቀረብ፦ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተበየነው የሞት ፍርድ ተጠያቂ አይሁዳውያን እንዳልሆኑ ቅዱስነታቸው በማስረዳት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና ደቀ መዛሙርቱ ጭምር አይሁዳውያን እንደነበሩ ያስገነዝባሉ። ስለዚህ ጌታችን ለሞት ፍርድ አሳልፎ በመስጠት ተጠያቂው የወቅቱ ልኡላዊ አምባገነን ሥርዓት ነው ብለዋል።
ጲላጦስ፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተከፈተውን ችሎት ሲመራ፣ እውነት ምን ማለት ነው ሲል ጥያቄ ያቀርባል፣ ብዙዎችም ይህንን መሠረት በማድረግ እውነት ምን ማለት ነው የሚለው ጥያቄ እስካሁን ድረስ ገና መልስ ያላገኝ ክፍት ጥያቄ ወይንም ያልተፈታ ጥያቄ ነው ብለው ይናገራሉ፣ ቅዱስ አባታችን በዚህ በተነተኑት ሀሳብ ላይ በማከል ሆኖም ግን ማንኛውም ሰው አለ እውነት የሕይወትን ትርጉም ሊቀበልም ሊያስተናግድም ሊረዳም አይችልም፣ እውነት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የሚታወቅ ሲሆን፣ እውነት ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብለዋል።
ስቅለት፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ እያለ በቅድሚያ የሚያደርጉትን አያውቁም በማለት ምንም’ኳ አለ ማወቅ የልብ ማደንደንን ወይንም የተለያዩ የእውቅት ዘርፎች ባለ ቤትነትን እና ግኡዛዊ እውቀትን የሚያመለክት ቢሆም ቅሉ አክሎም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያደርጉት አያውቁም በማለት ለአባቱ የተናገረው ቃል ለሁሉም ሰው ልጅ እና ታሪክ ማጽናኛ ነው።
ጌታችን በተሰቀለበት መስቀል በስተቀኝ በኩል የተሰቀለው ወንጀለኛ፣ የእግዚአብሔር ምሕረት በመጨረሻ ሰዓት ላይም መቀበል እንደሚቻል ያሳየናል።
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት፣ የዓለም ኃጢአት ፍጹም ንጹሕ በሆነው ሰው እንደሚለወጥ ይህም በፍጹም ፍቅር እና ስቃይ አማካኝነት በኃጢኣት ያደፈው ሰው እንደሚነጻ፣ መልካም ከክፋት እጅግ የላቀ እና ትልቅ መሆኑንያረጋግጥልናል።
ትንሣኤ፣ ያለትንሳኤ እምነት የክርስትና ባዶ ትርጉም አልቦ ነው። የጌታችን ክርስቶስ ትንሣኤ ዳግም ሕይወት የዘራ ሬሳ ማለት ሳይሆን ሞትን ፈጽሞ የደለዝ ወሳኝ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት፣ ለሰው ልጅ አዲስ መጪ ሕይወት የሚያረጋግጥ ነው። ትንሣኤ በሥነ ምርምር የሚደገፍ እውነት ሳይሆን፣ ከሥነ ምርምር ጋር የማይጻረር እርሱም የሰው ልጅ በውስጡ የሚያስተነትነው የህልውና ዝንባሌ ነው።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አሳልፈው ለሰጡት ሳይሆን ለአንዳንድ ሰዎች ብቻ ለምን ተገለጠ የሚለውን ጥያቄ ቅዱስ አባታችን ሲያስረዱ፣ እግዚአብሔር በሰው ልጅ ታሪክ ታሪክን ሲሠራ የሰው ልጅ እንደሚያደርገው ትምክህተኝነት የሚያጎላ ሳይሆን ዝቅ ብሎ ትሑት እና ቀስ በቀስ የሚሠራና ዘወትር በያንዳንዱ ልብ የሚያንኳኳ በሩን ለሚከፍትለት እንዲያዩት የሚፈቅድ መሆኑ የሚያረጋጥ እውነት ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን በመጽሐፉ ማጠቃለያ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን አሸንፎ መነሣቱ የተረጋገጥ ነው፤ እናምናለንም ምንም’ኳ ፍርሃት የሚከተለን ማዕበል የሚያናውጠን ቢሆንም በዓለም ፍጻሜ ዳግም በክብር እንደሚመጣ በእርሱ ላይ ያለን እማኔ ከለላችን ደስታችን ነው የሚለውን ጥልቅ ሀሳብ ማእከል በማድረግ ዕርገት ምን ማለት መሆኑን ተንትነዋል።