የቀድሞው የሲታውያን ጠ. አበምኔት ዜና እረፍት

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 3215


Abbot-Mauro-Estevaየ81 ዓመት እድሜ ባለጸጋ የነበሩት የቀድሞው የሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔት ክቡር ማውሮ ኤስቴቫ በአጭር ጊዜ ሕመም ኅዳር 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ስፔን በሚገኘው ፖብሌት ገዳማቸው ከዚህ ዓለም ወደ ጌታቸው እቅፍ ተሻግረዋል።

ነፍሰ ኄር ጠቅላይ አበምኔት ማውሮ ኤስቴቫ እንደ መነኮስ ለ55 ዓመታት፣ ከዚህም ውስጥ እንደ ካህን ደግሞ 47 ዓመት ያሳለፉ ሲሆን፤ ከ1963-1991 ዓ.ም. ድረስ የፖብሌት ገዳም አበምኔት፤ በመቀጠልም ከ1987-2003 ድረስ የሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔት ሆነው አገልግለዋል። የቀብር ሥርዓታቸው ኅዳር 8 ቀን በገዳማቸው ተከናውኗል። 

ነፍሰ ኄር ጠቅላይ አበምኔት ማውሮ ኤስቴቫ በተለየ ሁኔታ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሲታውያን መነኮሳት ልዩ ቦታ የሚሰጡና ለገዳሞቻችንም ብዙ በማቀድና ያቀዱትም ከግብ እንዲደርስ የሚቻላቸውን የጣሩ ሲሆን እኛም እኚህን አባት ለሰጠን አምላክ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ በቅንነት ያገለገሉት እግዚአብሔር በእቅፉ እንዲቀበልልን ጸሎታችን ነው።

ሀቦ እግዚኦ እረፍተ ዘለዓለም፤ ወአብርህ ሎቱ ብርሃነ ዘለዓለም። ወይኩን እረፍቱ በሰላም አሜን።