የሲታውያን ገዳም በኢትዮጵያ አዲስ መዋቅር አገኘ

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 2022

Ocist Ethiopiaከቅድስት መንበር (ቫቲካን) በተገኘው ፈቃድ መሠረት በሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔት ኀላፊነት በኢትዮጵያ የሚገኘው የሲታውያን ገዳም በአዲስ መልክ የተዋቀረ የመነኮሳን አስተዳደር ሂደት ጀመረ።

የሲታውያን ማኅበር ጠቅላይ አበምኔትና በዚህ ውሳኔ መሠረት የቅዱስ ዮሴፍ ገዳም ሾላ የበላይ ኀላፊ የሆኑት ማውሮ ጁዜፔ የማኅበሩ አስተዳዳሪ የሆኑትን አባ ሜይንራድ ጆዜፍ ቶማንን በመወከል ወደ ኢትዮጵያ ልከው ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. በቅዱስ ዮሴፍ ገዳም ኀላፊ መነኮሳት አባቶች ተሰባስበው ውሳኔው ተግባራዊነቱን ጀምሯል። በዚህም መሠረት በአዲስ አበባ የሚገኘው የቅዱስ ዮሴፍ ገዳም በክቡር አባ ባዘዘው (ወልደ ገብርኤል) ግዛው አባታዊ ኀላፊነት የተቀሩት ገዳማት ማእከል እንዲሆን ተደርጓል።

በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሳእናና በጎንደር የሚገኙት አራት የሲታውያን ገዳማት ስድስት በተመካሪ ደረጃ ላይ ያሉ መነኮሳትን አካትቶ በጠቅላላ ሠላሳ ሦስት መነኮሳት ያሉት ሲሆን በሥሩም ከመዋእለ ሕፃናት እስከ ተግባረ እድ ድረስ የሚያካትቱ በድምሩ ከአምስት ሺህ በላይ ተማሪዎችን የሚያስተናግዱ አብያተ ትምህርትን ያስተዳድራል፤ በቁምስና ደረጃም ሐዋርያዊ አገልግሎትን በሚመለከት በአራቱ ገዳማት አምስት ቁምስናዎችን የሚያገለግል ማኅበር ነው።

የሲታውያን ገዳም በኤርትራና በኢትዮጵያ እንዴት እንደተጀመረና ከ ፶፮ ዓመታት በፊት የመጀመርያው ገዳማችን የመንዲዳ ደብረ ጽንሰታ ዘሲታውያን ገዳም በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተገደ ይበልጥ ለመረዳት ከታች ያለውን ገጽ እንዲጎበኙት እየጋበዝን ለሕይወታችን ቅድስናና ለሐዋርያዊ ሥራ አበርክቷችን በጸሎታችሁ ታስታውሱን ዘንድ አደራ እንላለን። http://www.ethiocist.org/index.php?option=com_content&;view=article&id=284&Itemid=669