የሲታውያን አባቶች ፳፭ኛ የክህነት የብር ኢዮቤልዩ

“በልባችሁ ያፈቅር ዘንድ፣ በእጃችሁ ይፈውስ ዘንድ በእግራችሁም ለመልካሙ ዜና ብስራት ይራመድ ዘንድ እሱ አሁንም ገና ይፈልጋችኋል”

Untitled-4ሐምሌ ፰ ቀን ፳፻፫ ዓ.ም. ጣልያን በሚገኘው የኢትዮጵያና ኤርትራ ሲታውያን ዋና ቤት በካዛማሪ  አራት የሲታውያን መነኮሳት የሢመተ ክህነታቸውን ፳፭ኛ የብር ኢዮቤልዩ ቅዳሴ በታላቅ መንፈሳዊነትና አጀብ አከበሩ።

፳፭ኛ ሢመተ ክህነታቸውን ካከበሩት አራት መነኮሳት ውስጥ ሁለቱ ክቡር አባ ገብረወልድ ወርቁ ከቅዱስ ዮሴፍ ገዳም አዲስ አበባና ክቡር አባ ወልደ ትንሣኤ ባለወልድ ከቅድስት ሥላሴ ገዳም ሆሳእና ሲሆኑ የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ አባ ሰባሰቲያኖና አባ ጆርጆ የሚባሉ ጣልያናውያን የካዛማሪ መነኮሳት ናቸው።

፲፰ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሲታውያን ካህናት በጠቅላላም ፵፮ ካህናት የተሳተፉበት መስዋእተ ቅዳሴ ላይ በነበረው የስብከት ጊዜ ኢዮቤልዩ የምሕረትና የምስጋና ዓመት መሆኑ ተወስቶ

እንደካህንና ክርስቲያን በነዚህ ፳፭ ዓመታት ውስጥ ለተደረጉት መተላለፎች ሁሉ ከአምላክ ምሕረትንና ላደረገላቸው ድንቅ ነገሮችና ለዚህ ታላቅ ክህነታዊ አገልግሎት ደግሞ የምስጋና ዘመን መሆኑ ተብራረቷል። የካዛማሪ ክፍለ ማኅበር አበምኔት ሲልቬስትሮ ቡታራጺም በበኩላቸው እነዚህን አራት ካህናት “ክርስቶስ አሁንም ይፈልጋችኋል” በሚል አጽንዖታዊ ንግግር “በልባችሁ ያፈቅር ዘንድ፣ በእጃችሁ ይፈውስ ዘንድ በእግራችሁም ለመልካሙ ዜና ብስራት ይራመድ ዘንድ እሱ አሁንም ገና ይፈልጋችኋል” ሲሉ ቀጣይ የተቀደሰ የክህነት አገልግሎትንና ለክርስቶስ ምርጥ መሣሪያ ይሆኑ ዘንድ ምኞታቸውን ለአራቱ ካህናት ገልጸዋል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ ወንድማማቻዊ ጠበል ጻድቅ በመቋደስ “በከመ ይቤ ዳዊት በመዝሙር አንተ ካህኑ ለዓለም” በሚል ወረብና ሽብሸባ ተደምድሟል።

Jubilee3


አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።