የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዕለተ ሮቡዕ አስተምህሮ (እ.አ.አ. ሰኔ 3 ቀን 2009)

 ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ኣሥራ ስድስተኛ ዛሬ ረፋድ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ አደባባይ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ስለ ነበረው ትልቁ የምንኵስና አብነት የሆነው ራባኑስ ማውሩስ ላይ ያተኮረ ጉባኤ አስተምህሮ አቅርበዋል። ቅዱሱ አባታችን ጉባኤ አስተምህሮውን በጸሎት ከከፈቱ በኋላ የሚከተለው ከመዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 25 ከቍ. 4-10  

 

 

‘‘አምላክ ሆይ! የአንተን መንገድ አስተምረኝ፤ በእኔም ዘንድ የታወቀ ኣንዲሆን አድርገው። አንተ የምታድነኘ አምላኬ ስለሆንህ፦ እውነትህን ተከትዬ እንድኖር አስትምረኝ፤ እኔ ዘወትር የምታመነው በአንተ ነው። እግዚአብሔር ሆይ! ከጥንት ጀምሮ የምታሳየውን፤ ምሕረትና ቸርነት አስብ። የወጣትነቴን ኃጢአትና ስሕተት ይቅር በልልኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ! በማያቋርጠው ፍቅርህና ቸርነትህ አስበኝ። እግዚአብሔር ደግና ቅን ስለሆነ፦ ሊከተሉት የሚገባቸውን መንገድ ለኃጢአተኞች ያስተምራል። ትሑቶችንም በትክክለኛው መንገድ ይመራቸዋል፤ ፈቃዱንም ያስተምራቸዋል። ቃል ኪዳኑን የሚጠብቁትንና ትእዛዙን የሚፈጽሙትን ሰዎች፤ እግዚአብሔር በእውነትና በፍቅር ይመራቸዋል።” 
 

 

 

የሚል ተነበበ። ይህ ቃለ እግዚአብሔር በተለያዩ ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ፣ የዕለቱ ትኩረት በራባኑስ ማውሩስ መሆኑን አስመልክተው ቅዱስነታቸው በጣልያነኛ ቋንቋ ሰፊ ኣስተምህሮ ካቀረቡ በኋላ በተለያዩ ቋንቋዎች በአስተዋጽኦ ኣጭር ኣስተምህሮዎችም ሰጥተዋል። በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡት እንደሚከተለው ነው።

 

 


 
“የተከበራችሁ ወንድሞቼና እኅቶቼ፤ ዛሬም የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶሳችን በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ስለ ነበረው ትልቁ የምንኵስና አብነት የሆነው ራባኑስ ማውሩስ ይሆናል። ራባኑስ የምንኵስና ሕይወት የተከተለው ገና ወጣት ሳለ ነው። በገዳሙ ይማር በነበረበት ጊዜ ሥነ ጥበብ ማለትም ሊበራል ኣርትስ እና ሰፊ የክርስትያን ባህል ትምህርት ቀስመዋል። የፉልዳ ገዳም ኣበምኔትና የማይንዝ ሊቀ ጳጳስ በነበረበት ጊዜ ባደረገው ሰፊ ጥናትና በነበረው የግብረ ኖልዎ ቅናት ያኔ የነበረው ግዛት ኣንድነት ትልቅ ኣስተዋጽኦ አድርገዋል። እንዲሁም በቅዱስ መጽሓፍና በቤተ ክርስትያን አበው ትምህርት የበለጸገ የክርስትያን ባህል ለማስተላለፍም ረድተዋል። ከወጣትነቱ ጀምሮ ብዙ ቅኔ ይደርስ ነበር፣ ምናልባትም ነዓ መንፈስ ቅዱስ የሚለው እጅግ የታወቀ መዝሙር ደርሲ እርሱ ሳይሆን አይቀርም። የመጀመርያ የንባበ መለኮት ጽሑፉ ለቅዱስ መስቀል የጻፈው ቅኔያዊ ግጥም ነበር። በመሀከለኛው ዘመን ይደረግ እንደነበረም ቅኔው በተለያዩ የኢየሱስ ስቁል ምስሎች ተሸኝተዋል። ይህ አገባብ ሰው በምልአተ አካል ማለት በአእምሮ ልብ እና ሕዋሳት በእግዚአብሔር ቃል ያለውን እውነት እንዲያስተነትን ለማለት ይደረግ የነበረ ልማድ ነው። ራባኑስ በዚህ መንፈስ ተገፋፍቶ ሃብታሙን የክርስትያን ባህላዊ ልማድ ከትውልድ ለትውልድ ለማስተላለፍ ስለ ቅዱስ መጽሓፍ በጻፋቸው ሓተታዎች፣ ስለ ሥርዓተ አምልኮ የሰጣቸው መግለጫዎችና የግብረ ተልእኮ ጽሑፎቹ ተጠቅመዋል።
 

ይህ ዓቢይ የቤተ ክርስትያን ሰው በጥናት፣ ጥልቅ በሆነ ኣስተንትኖ እና በማያቋርጥ ጸሎት በተሰኘ ሕያው ግብረ ተልእኮው አብነት በመሆን ዛሬም መንፈሳችንን ያነቃቃል። 

 

 


 
ቅዱስነታቸው ከራባኑስ ጽሑፍ በመጥቀስ የዘመናችን ሰው ለእግዚአብሔር ጊዜ መስጠት እንዳለበት በማስመልከት፤ ‘‘በሕይወቱ ዘመን ለእግዚአብሔር ጊዜ የማይሰጥ ሰው ገዛ ራሱን የእግዚአብሔር ብርሃንን ከማየት ይከልክላል፣ አሳቡ በዓለምና በጭንቀትዋ በማትኮርም የእግዚአብሔርን ምሥጢሮች ከማወቅ በፍጹም ይታገዳል።” ብለዋል፣ 
 

 


 
በመጨረሻም ‘ፋታ በማይሰጥ የሥራ ጊዜም ይሁን በዕረፍት ግዜ በሕይወታችን ዘመን ውስጥ ለእግዚአብሔር ጊዜ መስጠት አለብን። በኅሊናችን በማስተንተን ወይንም ትንሽ ጸሎት በማሳረግ ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር እንክፈት። በተለይም ዕለተ እሁድ የእግዚአብሔር ዕለት መሆንዋን በማስተወስ መንፈሳዊ ነገሮች በማስተንተን እንቀስድሳት፣ በዚህ መንገድ ብቻ ነው ሕይወታችን ዓቢይና እውነተኛ የሚሆነው” በማለት ሁሉንም በተለያዩ ቋንቋዎች አመስገነው ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት የዛሬው ጉባኤ ትምህርታቸው ፈጽመዋል።
 

 

 

 

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።