የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አስተምህሮ

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ በቅ.ጴጥሮስ ባዚሊካ አደባባይ ለተሰበሰቡት ብዙ ምእመናን ባሰሙት አስተምህሮ በቅርቡ ወደ ቅድስት መሬት አድርገውት ስለ ነበረው ሐዋርያዊ ጉብኝት በሰፊው ገልጠው ምእመናን ለመኸከለኛው ምሥራቅ ቤተክርስትያን እና አገራት ሰላምና ብልጽግና አብረዋቸው እንዲጸልዩ ጠይቀዋል፣ ለጉብኝቱ መሳካት ለተባበሩትና ለረዱት ሁሉም ከልብ አመስግነዋል።
በፊታችን እሁድ በቤትክርስትያን ተስታውሶ የሚውለውን ዓለም አቀፍ የግኑኝነቶች ቀን በመጥቀስም በተለይ ወጣቶች የዘመኑ ሥልጣኔ ውጤት የሆነውን የግኑኝነት ጥበብ ጓደኝነትን ኅብርትን ምሕረትንና የሰላም ውይይትና ባህልን በሚያጎልብቱ አዎንታውያን ግቦች ላይ ለመድረስ እንዲጠቀሙበት አደራ ብለዋል።

በጉባኤ አስተምህሮው መጨረሻም በሥርዓቱ ላይ ለተሳተፉት ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታና ሐዋርያዊ ቡራኬ አቅርበው በሰላም ወደየመጡበት አሰናበቱ።

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።