የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያንና መጽሐፍ ቅዱስን የማሟላት እንቅስቃሴ

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 2913

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተጨማሪ የምትቀበላቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለመተርጉምና ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመረች። በይፋ በታወጀው በዚሁ እንቅስቃሴ ብፁዓን የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት በአንድነት አባታዊ ቡራኬያቸውን የሰጡ ሲሆን ይፋ ሆኖ ሥራው እንደጀመረ ሚያዚያ 30 ቀን 2003 ዓ.ም. በልደታማርያም ካቴድራል ቤተክርስቲያን በበፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ታውጇል፡፡

እነዚህ ተጨማሪ የኢትዮጵያን ካቶሊካዊ ቤተክርስቲያን የምትቀበላቸውን መጽሐፍ በተለያየ ጊዜያት የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተረጐሟቸው ቢሆንም የትርጉም ሥራ እጅግ ጥንቃቄ ሚያስፈልገው በመሆኑ በይፋ ሥራው እንዲጀምር ቤተክርስቲያን መፍቀድዋን በመግለጽ ለዚሁ ተግባር ከፍተኛ እገዛ የያደርገውን የኢትዮጰያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበርን አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ሰብሰቢ የሆኑት አቶ ማርቆስ ገብረማርያም ባደረጉት ንግግር ማኅበሩ ሶስቱን

 

 

ዓቢያት ክርስቲያን በማቀራረብ እያደረገ ያለውን ታላቅ አገልግሎት በመግለጽ ከሁሉ በላይ የሆነውን ይህን ታላቅ ሀብታችን እኛም ተገልግለንበት ሌሎች እንዲጠቀሙ የማድረግ ክርስቲያናዊ የውዴታ ግዴታ እንዳለብን በመግለጽ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምእመንም እንደሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ለመጽሐሕፍ ቅዱስ መስፋፋትና ለሁሉ ወገን እንዲደርስ ለአስተባባሪው የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በሚችለው አቅም ሁሉ ድጋፉን እንዲያደርግ ተማጥነዋል፡፡

የማኅበሩ ጸሐፊ አቶ ይልማ ስለመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ዓላማና ተልዕኮ በሀገራችን 81 ቋንቋ መነገሩን ከነዚህ ቋንቋዎች ሙሉ መጽሐፈ ቅዱስ በ5 ቋንቋ ብቻ መተርጐማቸው የትርጉም ሥራ ቀላል እንደመሆኑና ስለሚወስደው ጊዜ በሃገራችን መጽሐፍ ቅዱስን ለማሳተም የሕትመት መሣሪያ አለመኖር መጽሐፍ ቅዱስን ለማሰራጨት ደግሞ ሌላው ከባድ ተግባር መሆኑን በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጠዋል በመጨረሻም መጽሐፍ ቅዱስ ለሕይወታችን ታላቅ ትርጉም እንደሰጠን ሁሉ ሌሎችም የዚሁ ዕድል ተጠቃሚ እንደሆኑ ባደረግን ቁጥር የተሰጠንን ስጦት ባግባቡ መጠቀማችን ገለጻ አድርገዋል፡፡
በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ብርሃነየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር እያከናወነ ያለውን አገልግሎት በማመስገን ለዚሁ ዓላማ በግንባር የቆሙትን ሁሉ በቤተክርስቲያኒቱ ስም አመስግነዋል፡፡

 

ከማንኛው መጽሐፍ በላይ ለተረሱትና ማንም ቦታ ለማይሰጣቸው ወገኖች የመጽሐፍ ቅዱስ ማህበር ቅድሚያ በመስጠት በቋንቋቸው በመተርጐም እያደረገ ያለውን አገልግሎት በገጠራማው የአገራችን ክፍል ለማየት መቻላቸውን ምስክርነት ሰጠዋል፡፡
በድጋሚም ለኢትዮጰያ ካቶሊከዊት ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ መስፋፋት ከማህበሩ ጋር በጋራ ለመሥራት ሁልጊዜ ዝግጁ መሆናዋን ገልጽዋል፡፡

 

 

ምንጭ፡ ራድዮ ቫቲካን