የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር

ቫቲካን ሬድዮ- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ለአፍሪቃ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት ተገኝተው ንግግር ማሰማታቸው ከሲኖዶስ አዳራሽ የተላለፈልን ዜና ገለጸ።
የፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ጳውሎስ ንግግር:- "በስም አብ ወወልድ ወንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፣...
ክቡራን ብፁዓን ካርዲናላት እና ብፁዓን ጳጳሳት የዚህ ጉባኤ ተሳታፊዎች፣ በዚህ ዓቢይ ሲኖዶስ እንድሳተፍ እና ንግግር እንዳቀርብ የተደረገልኝ የክብር ጥሪ ለእኔ ትልቅ ክብር እና ልዩ እድል ነው። በተለይ ደግሞ፣ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛ በናነተ መካከል እንድገኝ ላቀረቡልኝ ጥሪ እና እ.ኤ.አ. ባለፈው ሰኔ ወር በሮማ ባካሄድነው የጋራ ግኑኝነት ለአፍሪቃ ያላቸው ፍቅር እና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስትያን ያላቸውን አክብርቶ የሰጡት የግል ምስክርነት በማስታወስም ምስጋናዬን አቀርባለሁኝ”።
“አፍሪቃ በስፋቷ ሁለተኛ ክፍለ ዓለም መሆኗንም ገልጠው፣ በስምምነት እና በእኩልነት የሚኖሩት የተለያዩ የኅብረ አሕዛብ አገር ነች። ይህ የኅብረ ብዛቱ እግዚአብሔር ለአፍሪቃ የሰጣት ጸጋ ነው። የአፍሪቃ ውበት መግለጫም ነው። በሌላ ረገድም አፍሪካ እያንዳንዱ ሕዝብ አለ ቀለም እና ጎሳ ልዩነትም ሁሉም በእኩልነት የሚኖርባት ምድር ነች” ብለዋል።
የሥነ ሰብእ፣ የፍልስፍና እንዲሁም ምሁራን፣ በጠቅላላ አፍሪቃ በተለይም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መሠረት መሆኗ ያረጋገጣሉ። በኢትዮጵያ መርኀ እለት መሠረት፣ ታሪክ ከአዳም እና ከኖሕ የሚጀምር መሆኑ ያወሳል። ይኽ ማለት ደግሞ ለኛ ኢትዮጲያውያን የፍጥረት አጀማመር፣ ያለንበት ጊዜ መጪው ጊዜ ዛሬም ሁሌም በእግዚአብሔር እና በእርሱ የማዳን ታሪክ አማካኝነት የተመለክተ ነው”።
“በአክሱም ሐወልት፣ በግብጽ ፒራሚድ፣ በተለያዩ በአፍሪቃ በሚገኙት ጥንታውያን ብራናዎች ዘንድ ተቀርጾ የሚገኘው የአፍሪቃ ሕዝብ ጥንታዊው ክብር የሥልጣኔ ምንጮች ብቻ አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለን በረሃብ ለተሰደደ ሕዝብ አፍሪካ መጠጊያ ነበረች፤ ይህም በያዕቆብ ጊዜ የነበሩት የአይሁዳውያን በግብጽ ሰባት ዓመት የመሰደድ ታሪክ ነው።
በመካከለኛው ምስራቅ ይኖር የነብረው ሕዝብ ከሚደርስበት ድርቅ እና ረሃብ ለመላቀቅ በግብጽና በኢትዮጵያ መጠጊያ ያገኝ ነበር። በጠቅላላ አፍርቃ በእርሃብ ለሚጠቃው ሕዝብ መጠጊያ ነበረች። ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚያረጋገጠውም አይሁዳውያን እና ነቢይ ኤርሚያስ በባቢሎናውያን ወረራ ዘመን በኢትዮጵያና በግብጽ መጠለያ እንዳገኙ እንረዳለን። በተመሳሳይ መልኩም ከሄሮዶስ ጭካኔ ለመተረፍ ኢይሱስ ክርስቶስ እና ቅድስት ድንግል ማርያም በግብጽ መጠጊያ እንዳጉኝ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህም አፍሪቃውያን ሰዎችን እንደሚንከባከቡ የሚያረጋገጥልን ሓቅ ነው። አፍሪቃ በከሃሌ ኵሉ እግዚአብሔር ለዘመናት ያመኑ የአማኞች ክፍለ አለም ነች፣ ቅድስት ሳባ ለአገሯ ሕዝቦች ከእስራኤል የተቀበለችውን ብሉይ ኪዳን አስተምራቸዋለች ከዚያን ጊዜ ጀምሮም የሙሴ ጽላት በኢትዮጵያ በአክሱም ከተማ ይገኛል”።
“የቅድስት ሳባ ልጅ ሚኒሊክ ቀዳማዊ የእርሷን አብነት በመከተል የሙሴን ጽላት ወደ ኢትዮጵያ አፍሪቃ ለማምጣት ችሏል። የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ታሪክ፣ በኢትዮጵያ የሚገኘው መሠረት ያለው የሙሴ ሕግ እና በሚገባ ሥር የሰደደ የእምነትና ባህል ሕይወት ህላዌ ከእስራኤል ይልቅ በኢትዮጵያውያን ሕይወት ዘንድ ሕገ ሙሴ በሚገባ ይኖር እንደነበር ይመሰክራል። ይህንን እውነታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባህልና ያኗኗር ዘይቤን በማጥናት ማረጋገጥ ይቻላል”።
በግብጽ እሌክሳንድሪያ ቅዱስ መጽሓፍ ከእይሁድ ቋንቋ ውጭ መተርጎሙ እና ይኽ ትርጉም ደግሞ የሰብአ ሊቃውንት ትርጉም ተብሎ የሚጠራ መሆኑ አስታውሰው፣ የአፍሪቃ ህዝቦች ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚያመለክተውም ከብሉይ ኪዳን ዘመን ጀምረው፣ በአዲስ ኪዳን ዘመንም በህሊና ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔር ስግደት የማቅረብ ልምድ እንደነበራቸው እናረጋገጣለን”። የኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥት ባዜን ለኢየሱስ ሕጻን ስግደት ለማቅረብ ወደ ቤተልሔም ከተጓዙት ነገሥታት አንዱ መሆኑንና እንዱሁም ኢየሱስ በሕማማቱ ወደ ጎልጎታ ተራራ መስቀል ተሸክሞ በመውጣት ላይ እያለ፣ አዲስ ኪዳን እንደሚናገረውም፣ አንድ ከሊቢያ የመጣ ስምዖን ቀረናዊ የተባለው አፍሪቃዊ መስቀሉን እንደተሸከመም እንገነዘባለን። ልብ እንበል በ 34ኛው ዓ.ም. አንድ ኢዮጵያዊው ጃንደረባ እንደ ሙሴ ሕግ መሠረት ለእግዚአብሔር ሥግደት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም መሄዱ እና በመንፈስ ቅዱስ ትእዛዝ መሠረትም በፊሊጶስ መጠመቁ እንረዳለን። የተጠመቀው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ወደ አገር ተመልሶ ክርስትናን ሰበከ፣ ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ከእስራኤል ቀጥላ በክርስቶስ ያመነች ሁለተኛ አገር እና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን በአፍሪቃ የመጀመሪያ ቤተ ክርስትያን ለመሆን እንዳበቃት የሚያረጋገጥ ታሪክ ነው”።
“በመጀመሪያ የእምነት ዘመኖች ታሪክ፣ የአፍሪቃ የክርስትና መለያ ይኽም አፍሪቃውያን ዘወትር ፍቅር እና ለአዲስ ኪዳን ያላቸው አክብሮት በጥልቅት እንደሚኖሩት ያመለክትልናል። አፍሪቃ በአፍሪቃ እና በመላው ዓለም የሚከበሩት የታላላቅ የቤተ ክርስትያን ምሁራን እና አበው የሚባሉት፣ የቅዱስ አጎስጢኖስ፣ የቅዱስ ተርቱሊያን የቅዱስ ቅጵሪያኖስ የቅዱስ አናስታዚዮ የቅዱስ ቄርሎስ አገር ነች፣ ዓለም በሞላ በታልቅ ችሎታው የሚያደንቀው የመዝሙር ደራሲው ቅዱስ ያሬድ አፍሪቃዊ፣ የኢትዮጵያ ልጅ፣ ድርሰቶቹ ኢትዮጵያ በዓለም ዙሪያ እንድትታወቅ ያደረጋት ነው። የእነዚህ የቤተ ክርስታይን አበው ድንቅ ሥራዎች የአፍሪቃን መግለጫ እና መለያ ናቸው” ብለዋል።
አፍሪቃ የመጀመሪያ የመጽሐፍ ቅዱስ ቀኖና የተደነገገባት ምድር፣ የሰሜን አፍሪቃ ሰማዕታት እንዲሁም በተለያዩ አገሮች ስደት እና መከራ ይደርስባቸው የነበሩት ክርስትያኖች በአፍሪቃ መጠጊያ ያገኙ እንደነበር እና በዚህች ክፍለ ዓለም በሰላም ለመኖር መቻላቸውንም ታሪክ ይመስክራል፣ ኢትዮጵያ በኤውሮጳ ስደት እና መከራ ይደርስባቸው ለነበሩት ክርስትያኖች መሬት መሆኗ፣ የነዚህ ክርስትያኖች የኢትዮጵያ ክልሎች ተጠብቆ እና ተከብሮ የሚገኝ የመቃብር ሥፍራ ይመሰክረዋል”።
“በኢትዮጵያ የቅዱስ መስቀል ትሩፋት ደብረ ግሸን ተብሎ በሚጠራው ሥፍራ ይገኛል፣ የአፍሪቃ ክርስትያኖች መስቀልን የተሸከሙ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያንም በነበረው የኮሙኒዝም ሥርዓት ወቅት ስደተ እና መከራ እንደደረሰባት፣ ብዙ የደም ምስክርነ የተከፈለባት ስትሆን፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቴዎፍሎስ ከሳቸውም በፊት በቅኝ ግዛታ ዘመን ሰማዕትነት የተቀበሉት ብጹዕ ወቅዱስ ጴጥሮስ” ካወሱ በኋላ ራሳቸውም መጀመሪያ “በእሥር እንደተሰቃዩ እና ለብዙ ዓመታት ስደት መዳረጋቸውን” ገልጸው “የኮሙኒዝም ሥርዓት ተገርስሶ ፓትሪያርክ ሆኜ ከተሾምኩኝ ወዲህ የወደመውን ዳግም ለመገንባት ዓቢይ ኃላፊነት እንዳለን ተገንዝበን በእግዚአብሄር፣ በገዳማውያን እና በሁሉም አማኞች ጸሎት አማካኝነት ይህን ኀላፊነት እየተወጣን ነው” ብለዋል።
“አፍሪቃ እምቅ ኃይል ያላት የለ መሬት እና በተፈጥሮ ሃብት የታደለች የተስተካከለ ውብ ያየር ጸባይ፣ ገና ላገልግሎት ያልዋለ ሃብት የተሸከመ መሬት ባለቤት፣ ብዙዎች ዓይናቸውን የሚጥሉባት” መሆኗ ገልጠው፣ “በተለያዩ አገሮች የሚታየው እድገት እና ብልጽግና የአፍሪቃ ድካም እና ተፈጥሮ ሃብት መሠረት የተረጋገጠ ነው ካሉ በኋላ፣ አፍሪቃውያን ብዙ ቅዱስ ሥራዎች ለዓለም አከናውነዋል፣ ባንጻሩ ግን ዓለም ለአፍሪቃ ምን አደረገላት? ቅኝ ግዛት ደርሶባታል፣ የተፈጥሮ ሃብቷ ተበዝብዘዋል፣ የተፈጥሮ ሃብቷን እንጂ አፍሪቃ ለምታደርገው የእድገት ጎዳና ለመደገፍ የሚያስብ ሃብታም አገር እንደሌለ፣ የአፍሪቃ አገሮች በተለያየ መልኩ ብዙ ማህበራዊ ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና መንፍሳዊ ነክ ችግሮች ተጋፍጠው ይገኛሉ፣ የአፍሪቃ ህዝብ በዓለም አንጻር ሲታይ በዝቅተኛ ኑሮ የሚተዳደር፣ የህዝቡ የኑሮ ደረጃ ከዕለት ወደ ዕለት እያሽቆለቆለ፣ የትምህርት እድል እጥረት ወጣቱን ምንኛ እይጎዳ መሆኑም፣ አለ ሕንጸት እና የትህምርት ዕድል ማንም ህዝብ እና አገር ዕድገት ለማረጋገጥ አይችልም” ብለዋል።
“ብዙ ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ቅሉ አፍሪቃን በእጅጉ እያሰቃየ ያለው የኤይድስ በሽታ ለመቆጣጠር እጅግ አዳጋች እየሆነ መምጣቱንም ገልጠው፣ በአፍሪቃ የሚታዩት ችግሮች በተቻለ መጠን ይቃለል ዘንድ የተለያዩ የአፍሪቃ አቢያተ ክርስትያን ምክር ቤቶች የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ መነሳታቸው” መስክረው፣ “በተለይ ደግሞ አክራርያን እና ፀንፈኞች የሚቀሰቅሱት ችግር ለማገድ አቢይ ጥረት እያደረጉ ናቸው፣ ይኸንን ሁሉ እግብ ለማድረስ የሃይማኖት መሪዎች እና ምእመናን በጠቅላላ እጅ ለእጅ ተያይዘው መሥራት ይገባቸዋል” ብለዋል።
ያለው ትውልድም ይሁን የሚመጣውም ትውልድ ከፍሎ የማይዘልቀው አፍሪቃ ያለባት የውጭ የብድር ጫና” ዘክረው፣ “በአፍሪቃ የሚታዩት ግጭቶች እና ሕፃን ወታደሮች የሚሳተፉባቸው ጦርነቶች፣ የሕገ ወጥ ስደተኞች ጸዓት የመሳሰሉት አፍሪቃን እያሰቃዩ ያሉት ችግሮች” አስታውሰው፣ “የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ውሳኔ እንደሚያመለክተው ከአሥራ ሥምንት ዓመት በታች በወትድርና ዓለም መቀጠር እንደሌለበት ሲያመለክት፣ ሆኖም ግን ይኽ ሕግ በአሁኑ ወቅት ተጥሶ ይገኛል። ይህ ጉዳይ ጨርሶ እንዲወገድ በጠቅላላ የአፍሪካ አቢያተ ክርስትያን በአንድነት ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ማሰማት ይኖርባቸዋል። ይኸንን አጋጣሚ በመጠቀም ሁሉም የሃይማይማኖት መሪዎች በጋራ ለሰላም እና ለአፍሪቃ እግዚአብሔር የሰጣት የተፈጥሮ ሃብት እንዲጠበቅ እና ሕይወት እና የሕጻናት ሕይወት እንዲጠበቅ ተባብረው በጋራ ይሠሩ ዘንድ” አደራ ብለዋል።
“በአፍሪቃ መሠረታዊ የሰው ልጅ ፍላጎት እንዲከበር” በማሳሰብ “ምንም’ኳ የቅኝ ግዛቱ ሥርዓት ያከተመለት ቢሆንም ቅሉ፣ ገና አሁንም የሃብታም አገሮች ጥገኞች የሆኑ የአፍሪቃ አገሮች እንዳሉም” አስታውሰው “ይህ ደግሞ አፍሪቃ ለብዙ ችግሮች ከማጋለጡም አልፎ ምሁራን እና ድንቅ ምርጥ ልጆቿ ለስደተ በመዳረግ ለከፋው ችግር እንድትጋለጥ እያደረገ ነው። እነዚህ የተጠቀሱት ጉዳዮች ብፁዓን ካርዲናላት እና ጳጳሳት ይወያዩባቸው ዘንድ” አደራ ብለዋል። እኛ ይላሉ ብፁዕ ፓትሪያርክ ጳውሎስ፣ “መልካም የሆነው መደገፍ የሰውን ክብር እና ፍቅርን የሚጻረር የሚነዛውን ሁሉ ለመቃወም የኃላፊነት ግዴታ አለብን። ክርስትያኖች የፍትህ የሰላም የእርቅ እና የእድገት መልእክተኞች ይሆኑ ዘንድም” አሳስበው፣ “በአፍሪቃ እነዚህ የላቁ እሴቶች እግብር ላይ እንዲውሉ የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበር ቆራጥ እና ትህትና የተሞላው ጥረት እንደ አብነት ጠቅሰው፣ የሃይማኖት መሪዎች የማኅበራዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰዎች መንፈሳዊ ጥያቄዎች ምላሽ የመስጠ ኃላፊነት እንዳለባቸው እና የማኅበራዊ የመንፈሳዊው ተነጣጥለው መሄድ የለባቸውም” ብለዋል። “የሰብአዊ መብት ጥበቃ ሰላም ፍትሕ ለማነቃቃት ልኡካነ ወንጌል አበክረው መሥራት ይገባቸውል” ብለዋል።
“የአፍሪቃ አቢያተ ክርስትያን በእግዚአብሔር ኃይል እና በመንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስትያን ቋንቋ ድምጽ መሆን ይገባቸዋል፣ ለቤተክርስትያን ደህንነት ከማን ጋር እና እንዴት መነጋገር እንዳለበትም ጠንቅቀው ማወቅ አለባቸው” ካሉ በኋላ፣ “በዚህ በአፍሪቃ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብጹዓን ጳጳሳት ሁለተኛው ሲኖዶስ በእንግድነት እንድሳተፍ በመጋበዜ እጅግ ደስተኛ ነኝ፣ አፍሪቃዊ ነኝ፣ ቤተ ክርስያኔም የሰማዕታት የቅዱሳን የገዳማውያን ጥንታዊት የአፍሪቃ ቤተ ክርስትያን ነች፣ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይኽ ጥሪ ስላቀረቡልኝ አመሰግንዎታለሁኝ። ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል እንናገር፣ ኢየሱስ በሕጻንነቱ ከማርያም ጋር በግብጽ እንደነበር ሁሉ፣ ሁንም ወደ አፍሪቃ ይመለሳል፣ ከእርሱም ጋር ሰላም ምህረት እና ፍትሕ ወደ አፍሪቃ ይመለሳል። እግዚአብሔር የአፍሪቃን ቤተ ክርስትያን እና አገልጋዮቿንም ይባርክ አሜን። በማለት ያሰሙትን ንግግር ደምድመዋል።

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።