የክህነት የብር ኢዮቤልዩና ሢመተ ዲቁና በማኅበረ ሲታውያን

A Adnew

D Yosef
ወንድም ዮሴፍ ፍቅረማርያም
ወደ መንዲዳ ዘርአ ምንኩስና የገቡት በ1989 ዓ.ም. ሲሆን ከዚያም በኋላ የተመክሮ ሕይወትን አድርገው ሕይወታቸውን እንደ ሲታዊ መነኩሴ በመሐላ ለእግዚአብሔር በመስጠት የፍልስፍናና የነገረ መለኮት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በመፈጸም ራሳቸውን ለክህነት አገልግሎት ሕይወት ሲያዘጋጁ ቆይተዋል፡፡ እነሆም በእግዚአብሔር ጸጋ በብፁእ አባታችን አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ እጅ ብዙ ካህናት፣ ደናግላን፣ ምእመናን፣ ቤተሰቦችና ወዳጆች በተገኙበት ሐምሌ 15 ቀን 2004 ዓ.ም ምስጢረ ዲቁና ተቀበሉ፡፡ መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት ብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ ቃለ እግዚአብሔር ባሰሙበት ወቅት ስለ ጥሪ አጽንዖት በመስጠት ‹‹ጥሪ የእግዚአብሔር ነው፡፡ እኛ ደግሞ የምንቀበለው እግዚአብሔርን በመታመን ነው እንጂ በራሳችን ኃይልና ዕውቀት በመተማመን አይደለም›› በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ መስዋዕተ ቅዳሴ ከተፈፀመ በኋላ ገዳሙ ባዘጋጀው የምሳ ግብዣ የዕለቱ መርኃ ግብር ተጠናቀቀ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ክቡር አባ አድነው ሎሬንሶ የክህነታቸው 25ኛ የብር ኢዮቤልዩ አከበሩ

ሐምሌ 19 ቀን 2004 ዓ.ም በሆሳዕና ቅድስት ሥላሴ ሲታውያን ገዳም ክቡር አባ ባዘዘው ግዛው የሲታውያን ገዳም ኃላፊ፣ ሌሎችም ብዙ ካህናት፣ ሲስተሮች ምእመናን፣ ቤተሰቦችና ወዳጆች በተገኙበት በድምቀት አከበሩ በዕለቱ መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት ክቡር አባ አድነው ሎሬንሶ ባሰሙት ቃለ እግዚአብሔር ‹‹የዛሬው ቀን በሕይወቴ ትልቅ ቦታ የምሰጠው ነው፡ እለቱ የቅድስት ሐና አመታዊ ክብረ በዓል ሲሆን እኔ ደግሞ ያደግኩበት ቁምስና የተሰየመው በቅድስት ሐና ነው፡፡ በልጅነቴ እንደማንኛውም የገጠሪቱ የኢትዮጵያ ልጅ ወላጆቼን በእረኝነት አገለግል ነበር፡ ከእለታት አንድ ቀን ግን የተለየ ዜና ሰማሁኝ ይኸውም ከሰዳማ ቅድስት ሐና ቤተ ክርስቲያን እጅግ ርቆ በሚገኘው ዋሰራ ቅድስት ተሬዛ ቤተክርስቲያን ሃበሻ ካህናት ከመንዲዳ በመምጣት የመጀመሪያ ቅዳሴ ይቀድሳሉ የሚል ነበር፡፡ የተባለው ቀን ደግሞ ከብቶችን የመጠበቅ ተራ የእኔ ነበር፡፡ ስለዚህ በጠዋቱ ከብቶቹን ይዤ በመውጣት ሜዳ ላይ አንድ ጥላ ስር ስብስቤ ቅድስት ሃናን እባክሽን ዋስራ ደርሼ እስክመለስ ድረስ ክብቶቼን አደራ ብያት ወደ ዋሰራ ሄድኩኝ ስመለስም ከብቶቼን በሰላም አገኘኋቸው፡፡ እዛም ያየኋቸው የሲታውያን ካህናት እነ ነፍሰ ኄር አባ ሩፋኤል እና ቁጥራቸው የበዛ የዘርአ ምንኩስና ተማሪዎች ነጭና ጥቁር ለብሰው ሳይ ቅድስት ተሬዛን እንዲህ ስል ለመንኳት ‹‹እባክሽን እነዚህ ሰዎች ያሉበት ቦታ ሄጄ እንዳይ ፍቀጅልኝ፡፡ እነሆ ዛሬ ለእግዚአብሔር የሚሳነው የለምና የክህነቴን ማለትም የምዕመናን እረኛነቴን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ ለማክበር በቃሁ፡፡ ክብር ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን>> በማለት ስብከታቸውን ደመደሙ፡፡ ክቅዳሴ በኋላ በነበረውና ሁሉንም ባሳተፈው የቁርስ ግብዣ የዕለቱ መርኃ ግብር ተጠናቀቀ፡፡

ከመ በኩሉ ይሴባህ እግዚአብሔር!!

አባ ተሻለ ንማኒ/ዘሲታውያን/

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።