የካህናት ቁጥር እድገት አሳየ

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 1743

tn_Priestswww.ewtn.com - በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2009 ዓ.ም. ከ 1999 ዓ.ም. ጋር ተነጻጽሮ የ5 ሺህ አዲስ ካህናት ቁጥር ብልጫ መመዝገቡን ከቅድስት ወንበር የወጣው አኀዛዊ ዘገባ ገለጸ።

ዘገባው በሚያሳየው መሠረት ከ11 ዓመታት በፊት 405, 009 የነበረው የካህናት ቁጥር አምና 410,593 ሲሆን የሰበካ ካህናት ቁጥር በ10 ሺህ ሲጨምር የማኅበራት ካህናት ቁጥር ደግሞ በ5 ሺህ መቀነሱ ታውቋል።

በሰሜን አሜሪካ አውሮፓና ውቅያኖሳውያን ሀገሮች (አውስትራሊያና በዙሪያዋ የሚገኙ ደሴታማ አገሮች) የሰበካም ሆነ የማኅበራት ካህናት

ቁጥር የቀነሰ ሲሆን በአፍሪካና እስያ ግን ከጠቅላላ ቁጥሩ ውስጥ የ30 በመቶ  የመጨመሩን ድርሻ ተጋርተዋል። በዚህም መሠረት ከአፍሪካና እስያ ቁጥራቸው የበዛ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በሂደት ላይ ሲሆኑ ከአውሮጳ ግን አናሳ ቁጥር መሆኑ ተዘግቧል። ይህም ሆኖ ግን ከዓለም ካህናት ወደ ግማሽ እጁ አውሮፓውያን ሲሆኑ ቀስ በቀስ ግን ይህ ሁኔታ እየተለወጠ መሆኑም ዘገባው ያስረዳል።

በአውሮጳና በአፍሪካ እስያ ያለው የእድሜ አማካይ ሲታይ የአውሮጳውያኑ ካህናት እድሜ ከፍ ያለ ስለሆነ በአውሮጳ አዲስ ሢመተ ክህነት የሚቀበሉት ቁጥር በሞት የሚለዩትን መብለጥ ያለመቻሉ የቁጥሩ መበላለጥ አንድ አስረጂ መሆኑ ተገልጿል። የሰሜንና የደቡብ አሜሪካ ካህናት ቁጥር በአሥር ዓመታት ውስጥ አሉታዊ ሚዛን የጠበቀ ሂደት ማሳየቱና በውቅያኖሳውያን አገሮች የአዲስ ካህናትና በሞት የሚለዩት ቁጥር የማይበላለጥ መሆኑም ታወቋል።

በቫቲካን አኀዛዊ ጥናት የሚያደርገው ቢሮ በተለያዩ ሐዋርያዊ እንቅስቃሴዎች ዙርያ በየዓመቱ ዘገባ የሚያወጣ ሲሆን የካህናት ቁጥርንም በተመለከተ በ2008 ዓ.ም. እና በ2009 ዓ.ም. የ809 ቁጥር ልዩነት ታይቷል።

ባለፉት አሥርት ዓመታት የታየው የካህናት አኃዝ እመርታ ከቀደም ዓመታት የላቀ መሆኑ ወደፊትን በጥሩ ተስፋ ለማየት አንድ ምክንያት ነው ሲል ቢሮው ዘገባውን ደምድሟል።