ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክቶስ 16ኛው ትላንትና ጧት በቫቲካን የሪፐብሊካዊት ሊባኖስ ርእሰ ብሔር ሚሸል ስለይማንን ተቀብለው እንዳነጋገሩ የቅድስት መንበር የማህተምና ዜና ክፍል ካሰራጨው መግለጫ መረዳት ተችሏል። በሊባኖስ በሙስሊሞች እና በማኅበረ ክርስትያን መካከል ያለው ሰላማዊ ማኅበራዊ ኑሮ ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በዓለማችን ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች በነጻነት እና ተከባብሮ መኖር የሚል ክቡር መልእክት መሆኑን ቅዱስ አባታችን በመግለጥ፣ ይህን እውነታ ለማረጋገጥ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት እና ትብብር ዘወትር እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም አመልክተዋል።

የሃይማኖት መሪዎች እና የመንግሥት የበላይ አካላትና ባለ ሥልጣናት የሕዝባቸውን ኅሊና ለሰላም እና ለእርቅ በማነጽ በሊባኖስ በጉጉት የሚጠበቀው መረጋገት እና ሰላም የሚደግፍ ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ፈታኝ ሁኔታዎችን የሚቋቋም መንግሥት እንዲጸና ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል የሚል መልእክት ቅዱስ አባታችን ማስተላለፋቸውን የቅድስት መንበር የማኅተም እና ዜና ክፍል መግለጫ አስታወቋል።
በመጨረሻም በተካሄደው ግኑኝነት ስለ መካከለኛው ምሥራቅ እና በአሁኑ ወቅት
በአንዳንድ ዓረብ አገሮች እየታየ ያለው አንገብጋቢ ሁኔታን በመጥቀስ፣ የተቀሰቀሱት ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ ማግኘት ይገባቸዋል የሚለው የጋራ እማኔ እንደተሰመረበትና በመካከለኛው ምሥራቅ ለማኅበራዊ ጥቅም አቢይ ሚና የሚጫወተውን የማኅበረ ክርስትያን ሁኔታ ትኵረት ይሰጠውም ዘንድ ጥሪ መተላለፉን የቅድስት መንበር የማህተም እና የዜና ክፍል በመግለጥ፣ አክሎም የሊባኖስ ርእሰ ብሔር ስለይማን ከቅዱስ አባታችን ከተሰናበቱ በኋላ ከቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ ጋር መገናኘታቸው ታውቋል።

 

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።