“የእግዚአብሔርን ምሕረት የመሰከሩና ያስተማሩ የ፳ኛው ክ.ዘ. ር.ሊ.ጳጳሳት”

2 saintsበትላንትናው እለት በቫቲካን የሚገኘው የተንጣለለው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አራት የቅዱስ ጴጥሮስ ተኪዎችን ያስተናገደበት ልዩ መንፈሳዊና ታሪካዊ ክስተት ነበር፤ ሁለቱ በእለቱ ቅድስናቸው በይፋ የታወጀላቸው ቅዱሳን ዮሐንስ ፳፫ኛውና ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ የቀድሞው ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክቶስ ፲፮ኛውና ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ናቸው።

ወደ አንድ ሚሊየን የሚጠጋው ሕዝበ ክርስቲያን በስምንት መቶ ቀዳስያን ታጅቦ መስዋዕተ ቅዳሴውንና ሥርዓተ ቅድስናውን በልዩ መንፈሳዊነትና ካቶሊካዊነት ማለትም ከዓለም አገራት የተወጣጡና በሰማይና በምድር ያሉ የቤተክርስቲያን ልጆች ህልውና በሚሰማበት መልኩ ተሳትፏል።

ጣልያናዊው ቅዱስ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ፳፫ኛው ከአምሳ ዓመታት በፊት ያረፉና ለ፮ ዓመታት ር.ሊ.ጳ. የነበሩ ሲሆን ቅዱስ ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ደግሞ ፖላንዳዊ ሲሆኑ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ወደ ጌታ የተሻገሩና ለ፳፯ ዓመታት ር.ሊ.ጳ. ሆነው ያገለገሉ ናቸው። ሁለቱም ቅዱሳን ለክፍለ ዘመኑ የቤተ ክርስቲያን መነቃቃት ትልቅ ሚና የነበራቸውና በቢሊየን በሚቆጠሩት የቤተ ክርስቲያን ምእመናን ውስጥ ጥልቅ ስፍራን የያዙ ናቸው።

የእለቱን ሥርዓት የመሩት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ስለነዚሁ ቅዱሳን ሲናገሩ “ሁለቱም በክፍለ ዘመኑ አሳዛኝ ወቅት ላይ የኖሩ ናቸው፤ ሆኖም ግን አልተሸነፉም። ለእነርሱ እግዚአብሔር፣ እምነት ማለትም የሰው ልጆች አዳኝና የታሪክ ጌታ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ያላቸው እምነት ኃያል ነበር” ብለዋል። በተለይም ቅ.ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ፳፫ኛውን የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጠሪና ከፋች መሆናቸውን ተመረኩዘው “ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት የነበሩ” በማለት ከገለጹ በኋላ ቅ.ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊን ደግሞ “የቤተሰብ ር.ሊ.ጳ.” ብለዋቸዋል። በመቀጠልም ሁለቱም ቅዱሳን “ብርቱዎች፣ በመንፈስ ቅዱስ ግልጽነት የተሞሉና የእግዚአብሔርን መልካምነትና ምሕረት ለቤተ ክርስቲያንና ለዓለም የመሰከሩ” እንደነበሩ ሰብከዋል። {jathumbnail off}

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ “የክርስቶስን ቁስል ቀና ብለው መመልከት ያልፈሩ የ፳ኛው ክ.ዘ. ር.ሊ.ጳጳሳት” ያሏቸውንና ቅድስናቸውን ያወጁላቸውን የእነዚህን ሁለት ቅዱሳን አማላጅነት ለቤተ ክርስቲያን ምሪት በመለመን ስብከታቸውን የጨረሱ ሲሆን፤ በሥነ ሥርዓቱ መጨረሻ ላይ በምእመናን የታጨቀውን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ዝግ ብላ በምትሄደው ልዩ መኪናቸው በማቋረጥ ቪያ ኮንቺሊያሲዮኔ ተብሎ የሚታወቀውን ጎዳና ጥግ ድረስ በመጓዝ ሕዝቡን ሰላም በማለትና በመባረክ ደምድመዋል።

የሕዝቡን ብዛትና ዙሪያ ገባውን የሚያስቃኘው ፎቶ ይኸው

Large Vatican

 

http://www.google.com/hostednews/getty/article/ALeqM5g8dWRiaINhO9kxlICcAcqVhIa1uQ?docId=487086797

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።