ከሁለት ሳምንታት በኋላ ዓመተ ክህነት መከበር ይጀመራል፡

 

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባወጁት መሠረት ከሁለት ሳምንታት በኋላ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዓመተ ክህነት መከበር እንደሚጀመር በቅድስት መንበር ይፋ መግለጫ ተሰጥተዋል። በቅድስት መንበር የቤተ ክህነት ቅዱስ ማኅበር ዋና ሐላፊ ብፁዕ ካርዲናል ክላውድዮ ሁመስ አራት መቶ ሺ ለሚሆኑ ካህናት ባስተላለፉት መልዕክት እንዳመለከቱት፡ ካህናት በሙያቸው ብቻ ሳይሆን ሁለንትናችው እጅግ በጣም አስፈላጊዎች እና ውድ ናቸው። ምእመናን ካህናትን በሐዋርያዊ ሙያቸው ደስተኞች እና ቅዱሳን እንዲሆኑለት እንደሚፈልግ ብፁዕ ካርዲናል ክላውድዮ ሁመስ ለካህናቱ በጻፉት መልዕክት መግለጣቸውም ተመልክተዋል። 

ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሚጀመረው ዓመተ ክህነት ካህናት ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፡ በአጠቃላይ ቤተክርስትያንንም እንደሚመለከት የቅዱስ ማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንጻ መግለጣቸው የቫቲካን ረድዮ ምንጭ አስታውቀዋል። የቤተ ክህነት ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንጻ እንዳመለከቱት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ፡ የካህናት መንፈሳውነት እና ቅድስና ተልዕኮ የተሳካ እንዲሆን ከልብ ይመኛሉ ለዚህም ይጠልያሉ። በሊቀ ጳጳሱ ገለጣ መሠረ ፡ ዓመተ ክህነቱ የካህን ተልዕኮአዊ ማንነት በቤተክርስትያን ዋነኛ ርእስ ነው። በቤተክርትያን የክህነት ምሥጢር የእግዚአብሔር ሕዝቦች ነፍሳት ማዳን መሆኑ ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንጻ፡ ስለሆነም ተኪ የሌለው ዓቢይ ሐዋርያዊ ሙያ መሆኑ አስታውቀዋል።

ገለጣቸው በማያያዝም ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ ዓመተ ክህነቱ የካቶሊካዊ ካህን ምስጢር ጥልቅ ጥናት እንዲካሄድ እና የማንነቱ አስፈላጊነት በታደሰ መልኩ ገሃድ እንዲሆን ፍጹም አስፈላጊ እና በበለጠ ጠንካራ መንፈስ እና መልካም አርአያነት ንጽህና ተላብሶ በጸሎት ተሸኝቶ የክርስቶስ መስመር ተከታይ መሆኑ የሚያስታውስ ዓመት እንዲሆን ይሻሉ ። ምእመናን በካህናት በኩል ከክርስቶስ እንደሚያገናኙ ያወሱት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንዛ ይህ ራሱ የእግዚአብሔር ፀጋ መሆኑ አስገንዝበዋል። ካህናት የክርስቶስ ታማኝ በመሆን መድኀኔ ዓለም እንደሆነ ሁሉ ካህናትም መንገዱ መከተል እንደሚጠበቅባቸው ሊቀ ጳጳሱ መግለጣቸው ገልጠዋል።

በቅድስት መንበር የቤተ ክህነት ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማውሮ ፒያቸንዛ የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ዓመት አስታውሰው ክርስቶስ ሐዋርያት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት፡ ካህናት ፡ መነኲስያት መነኮሳን ፡ ምእመናን የቤተክርስትያን ሕይወት ናቸው በማለት መግለጣቸው ተመልክተዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ፡ የቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አሥራ ስድስተኛ የግል ጸሐፊዎች ብፁዕ አቡነ ገኦርግ ጌንስታይን እና ብፁዕ አቡነ አልፍረድ ሱረብ ባለፈው ቅርብ ግዜ ማዓርገ ክህነት የተቀበሉበት ሀያ አምስተኛ ዓመት ቫቲካን ውስጥ በድምቀት አክብረው መዋላቸው ተያይዞ የደረሰ ዜና አስታውሰዋል።

 

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።