ክብር አባ ጸጋዬ ቀነኒ የሶዶ ሐዋርያዊ መንበር ተተኪ ጳጳስ ሆነው ተሰየሙ

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 1655

Sodoጥቅምት 11 ቀን 2006 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ክብር አባ ጸጋዬ ቀነኒን የሶዶ ሐዋርያዊ መንበር ተተኪ ጳጳስ አድርገው ሰይመዋል።

አባ ጸጋዬ ቀነኒ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ካህን ሲሆኑ የነቀምቴ ሐዋርያዊ መንበር ዓቃቤ ሆነውም ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ክቡር አባ ጸጋዬ የተወለዱት በኅዳር 13 ቀን 1936 ዓ.ም. ሲሆን ሐምሌ 6 ቀን 1968 ዓ.ም. ደግሞ ሢመተ ክህነት ተቀብለዋል። አሁን በጵጵስና የተሰየሙበት የሶዶ ሐዋርያዊ መንበር ከአምስት ሚሊየን በላይ የሚሆን ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 145 ሺህ የሚጠጉ ካቶሊካውያን በ39 ካህናትበ23 ቁምስናዎች ውስጥ ይገለገላሉ፤ በዚሁ ሐዋርያዊ መንበር 41 ደናግላትና /ሲስተሮች/ 18 ለምስጢረ ክህነት የሚዘጋጁ ወጣቶች ይገኛሉ። 

ምንጭ፡- http://en.radiovaticana.va/news/2013/10/11/a_coadjutor_named_for_soddo_in_ethiopia/en3-736537