ካቶሊኮች የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ደስታን በማሳየት ዓለምን አገልግሉ

Pope Francis General Audience April 3 2013 Credit Stephen Driscoll EWTN"ዓለም ዓይኖቹን ወደ እግዚአብሔር ማንሳት ተስኖታልና" ካቶሊኮች "የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን ደስታን" ለዓለም በማሳየት የሰው ልጆችን ያገለግሉ ዘንድ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ አሳሰቡ።

"የእግዚአብሔር ልጆች የመሆናችንን ደስታና በክርስቶስ እንኖር ዘንድ የሰጠንን ነጻነት እናሳይ፣ ወደ አምላክ ማየት ለተወው ዓለም ይህ ውድ የሆነ አገልግሎት ነው" በማለት ትላንትና ረቡዕ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት 40 ሺህ ሰዎች ተናግረዋል።

"ይህ ማለት በእያንዳንዷ ቀን ክርስቶስ ይለውጠንና እርሱን እንዲያስመስለን መፍቀድ አለብን ማለት ነው፤ ይህም ደካማነታችንን እና ጉድለታችንን ብናውቅም እርሱን ለመከተል በመጣር እንደ ክርስቲያኖች ለመኖር መሞከር ማለት ነው" በማለት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ አብራርተዋል።

ሲቀጥሉም "በውድቀቶቻችን ተስፋ ሳንቆርጥ በእርሱ መፈቀራችንን ሊሰማን ይገባል፤ ይህ ሲሆን ሕይወታችን በደስታና በርጋታ መንፈስ የተሞላ አዲስ ይሆናል። እግዚአብሔር ብርታታችን ነው! እግዚአብሔር ተስፋችን ነው!" ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ የእግዚአብሔር ልጅነታችንን ከክርስቶስ ትንሣኤና የማዳን ዋጋ ጋር በማስተሳሰር ካቶሊካዊ እምነት በትንሣኤ ላይ የተመሠረተና ከዚህም ውጪ ሲሆን ከንቱና እንደሚፈርስ ቤት መሆኑን አስታውሰዋል።

ር.ሊ.ጳ. የእለተ ረቡዕ አስተምህሯቸውን ሐዋሪያዊ ቡራኬ በመስጠት ከደመደሙ በኋላ ከ15 ደቂቃ በላይ ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅለው በመጨረሻም ለሕጻናትንና አካል ጉዳተኞችን ሰላምታን ሰጥተዋል።

ምንጭ፡- http://www.catholicnewsagency.com/

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።