ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ለኢራቃውያን ስደተኞች ገና በዓል በስልክ ያስተላለፉት መልእክት

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 3104

xmas iraq2014ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በፈረንጆቹ የገና በዓል ዋዜማ ላይ በኢራቅ በሚገኘው አንካዋ ተብሎ ወደ ሚጠራው የስደተኞች ካምፕ ስልክ በመደወል፣ ንግግራቸው 

በአካባቢው በሚገኙ ካህን አማካኝነት በአረብኛ ተተረጉሞ መልእክት አስተላልፈዋል።

የስልክ መልእክታቸውን “እንደምን አመሻችሁ” ብለው በመጀመር “በዚህች የገና ምሽት ሁላችሁም ሰላምታየ ይድረሳችሁ። አሁን የገናን በዓል ቅዳሴ ለማሳረግ ዝግጁ ናችሁ፤ እኔም በዚህ መሥዋዕተ ቅዳሴ ከእናንተ ጋር አብሬ ነኝ፤ እናንተ በአሁኗ ሰዓት ልክ ኢየሱስ እንደተወለደባት ሌሊት ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ናችሁ። እሱ ሲወለድ ተገቢ የሆነ ማረፊያ ቦታ አላገኘም ነበር፤ ከዚያም ሊያጠፉት ይፈልጉት ስለነበር ራሱን ለማዳነ ወደ አገረ ግብጽ መሰደድ ነበረበት። እናንተም በዚህች ምሽት እንደ ኢየሱስ ናችሁ፤ እኔም አጅጉን እባርካችኋለሁ፤ በጣምም ከናንተ ጋር ቅርብ ነኝ። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንደ ኢየሱስ መሆናችሁን ማሰቡ ስለናንተ ይበልጥ እንድጸልይ ያደርገኛል።”

“ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ! በዚህች ምሽት በልዩ ሁኔታ ከናንተ ጋር ቅርብ እንደሆንኩ ይሰማኛል፤ በሙሉ ልቤ ከናንተ ጋር ነኝ፤ ኢየሱስንም በርኅራኄው ይዳብሳችሁ ዘንድ፤ እመቤታችንም ብዙ ፍቅርን ትሰጣቸሁ ዘንድ እጸልያለሁ…በዚህች ምሽት ወደ እኛ መጥቷል፤ የዋህና ደግ የሆኑ እንዲሁም በግፍ እንደተሰቃዩትና እንደሞቱት ሕፃናቶቻችሁ ርኅሩኅና የዋህ ሕፃን ሆኖ ይመጣል። ኢየሱስ ወደኛ የእግዚአብሔርን ፍቅርና ቸርነት ይዞ ይመጣልና ይህንን በትልቅ ፍቅር ትቀበሉ ዘንድ ጸጋ እንዲያበዛላችሁ እጸልያለሁ። እንዲሁም ደግሞ ሙሉ ሕይወታቸውን ኖረው አሁን ይህን መስቀል የሚካፈሉትን በመካከላችሁ ስላሉት አያቶችና አረጋውያን አስባለሁ፤ እነርሱ ከሕይወት ያገኙትን ጥበብ ለሁላችን እንደሚያካፍሉ ተስፋዬ ነው። በዚህች ምሽት ሕፃናትና አረጋውያን በልቤ ውስጥ አሉ። እነሆም ሁላችሁን፣ በተለይም ሕፃናትንና አረጋውያንን ከልቤ እባርካችኋለሁ።” በማለት መልእክታቸውን ደምድመዋል።