የብጹእ አባታችን ብርሃነየሱስ ሱራፌል ካርዲናልነት ሥያሜ ሥርዓት ተከናወነ

Category: ዜናዎች Written by Super User Hits: 3625

New Cardinal Brhaneyesus of Ethiopiaቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ መሪነት በተካሄደው የቅርብ አማካሪዎቻቸው ማለትም የካርዲናሎች ስብሰባ ሀያ አዳዲስ ካርዲናሎች የሥያሜያቸው ሥርዓት ተፈጽሞላቸዋል። በዚህም ሥርዓት ታኅሣሥ 26 ቀን 2007 ዓ.ም. ካርዲናለነታቸው የታወጀላቸው በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤ/ያን የአዲስ አበባ ኤጳርኪያዊ ሊ.ጳጳሳት ብጹእ አባታችን ብርሃነየሱስሱራፌልና ሌሎች አሥራ ዘጠኝ ካርዲናላት የተለመደው ቀይ ቆብና ልብስ የተሰጣቸው ሲሆን ር.ሊ.ጳጳሳትም በሥርዓቱ ላይ  ጥልቅ ትርጉም ያለው መልእክት አስተላልፈዋል።

“የተጠራችሁበት የካርዲናልነት ሥያሜ የማዳመቂያ ወይም የጌጥ አይደለም፤ ምክንያቱም እንደመሪ ቃል ሊኖራችሁ የሚገባ ብቸኛ ቃል ፍቅር የሚለው ነውና።” በማለት ካርዲናልነት “የአንድ የአዛዥ ሰው ምልክትነት ሳይሆን ከፍ ላለ አገልግሎት ማለትም ለክርስቲያናዊ ፍቅር አገልግሎት” መጠራት መሆኑን አብራርተው ይህም መገለጫው በጎ ፈቃደኛነት፣ ወደ ፍትሕ የሚያዘነብል፣ በተስፋ የተሞላና የይቅርታ ሰው መሆኑንና “ካርዲናልነት የከበረ ኀላፊነት ቢሆንም ግን የከበሬታ አገልግሎት” አለመሆኑን ገልፀዋል።

በመቀጠልም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአገልግሎት ኀላፊነት ከፍ እያለ ሲመጣ ልባችንም እንዲሁ እየሰፋ መምጣት አለበት፤ የክርስቶስን ልብ ያህልም መስፋት ይኖርበታል። ሰፊና ሁሉን አቀፍ መሆን ማለት ከ«ካቶሊክ»ነት ጋር ተመሳሳይ ቃላት ናቸው፤ ይህም ድንበር የለሽ አፍቃሪ መሆን መቻልና በተመሳሳይ ሁኔታም በቅርባችን ላሉ ተጨባጭ ሁኔታዎች ታማኝ መሆን ማለት ነው።” ሲሉ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በኀላፊነታቸው መጠን የክርስቲያናዊ ፍቅራቸው አድማስ ይሰፋ ዘንድ መክረዋል።  

አዲሱ ካርዲናል ብጹእ አባታችን ብርሃነየሱስሱራፌል የፊታችን ቅዳሜ፣ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።

ምንጭ፡- http://www.news.va/it/news/concistoro-francesco-cardinale-e-uomo-di-carita-e