እኛ ማነን

በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሥር የምንገኝ ሲታውያን መነኮሳን በአገራችን በአዲስ አበባ፣ በመንዲዳ፣ በሆሣዕናና በጎንደር ገዳማት ሲኖሩን፤ ዓላማችንም በወንጌል ላይ የተመሠረተውን የቅዱስ አቡነ ቡሩክ ደንብን (The Rule of St. Benedict) በመከተል ክርሰቲያናዊ የጥምቀት ጸጋችንን በምልአት በሲታዊ ትውፊት መኖር ነው።.....

ይህም በምንኩስና ሕይወታችን፤ በግላዊም ሆነ ማኅበራዊ ጸሎትና ሥራ በቀጣይነት እግዚአብሔርን የመፈለግና የማመስገን ሕይወት ነው። በአጭር ቃላት ሕይወታችን “ጸሎትና ሥራ” (Ora et Labora) በሚለው ዘመን ጠገብ ትውፊታችን ይገለጻል።

ለዚህም ግብ መሳካት “ከክርስቶስ ፍቅር ምንም ነገር ያለማስበለጥ” የሚለውን ደንባችንን በማሰላሰል ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋትና ምስክርነት በጸጋው ተማምነን ለመኖር የወሰንን ነን።

ከመ በኲሉ ይሴባሕ እግዚአብሔር!- እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ፤ አሜን።1ጴጥ.4:11

Map St Joseph Cistercians

Top Panel

ር.ሊ.ጳ. በኩባ ሃቫና ለአንድ ሚሊየን የሚጠጋ ሕዝብ መስዋእተ ቅዳሴ አሳረጉ

«ማገልገል ያለብን ሃሳቦችን ሳይሆን ሰውን ነው… ክርስቶስም ከቁሳዊና ስግብግባዊ ራስ ወዳድነት ባሻገር የእያንዳንዱን ሰው የሕይወት ለውጥ ይሻል» ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

Pope Cubaር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በኩባና በሰሜን አሜሪካ የሚያደርጉትን ይፋ ጉብኝት የጀመሩ ሲሆን በዚህም መሠረት ባለፈው እሑድ በኩባ ዋና ከተማ በሃቫና በሚገኘው «አብዮት አደባባይ» ወደ አንድ ሚሊየን የሚገመቱ ሰዎች በተገኙበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገዋል። ይህ ከዓመታት በፊት ሊታሰብ የማይችል ክስተት ነበር፤ ምክንያቱም አደባባዩ ኮሚኒስታዊ በዓላትን የሚያስተናግድ ብቻ ነበርና ነው። በዚህ አጋጣሚ ግን የክርስቶስና የእመቤታችን ትላልቅ ስዕሎች በትላልቁ ተሰቅለው አደባባዩና ከተማዋ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ሃይማኖታዊ ክንዋኔ አስተናግደዋል።

ያለፈው ቅዳሜ ከአሥርት ሺህ በላይ በሚቆጠሩ ሰዎች በደመቀ አቀባበል ኩባ የገቡት ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ በኩባና አሜሪካ የስምንት ቀናት ቆይታ የሚያደርጉ መሆኑም ታውቋል።

ከመሥዋዕተ ቅዳሴውም በተጨማሪ የቀድሞው የኩባ ርእሰ ብሔር የነበሩት ፊደል ካስትሮ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስን የተገናኙ ሲሆን በዚህም ወቅት ር.ሊ.ጳ. በኩባ መንግሥት የአገዛዝ ሁኔታ ቅሬታን የሚጠቁም ነጥቦችን አመልክተዋል። ፊደል ካስትሮም በሥነ ምሕዳር ጉዳዮች፣ የሰዎች የእኩልነትን ጉዳይና ለሰላም ጥረት የማድረግ አርእስትን ያወሱ ሲሆን ር.ሊ.ጳ. በስብከታቸው ወቅት ማገልገል ያለብን ሃሳቦችን ሳይሆን ሰውን መሆኑንና ክርስቶስም ከቁሳዊና ስግብግባዊ ራስ ወዳድነት ባሻገር የእያንዳንዱን ሰው የሕይወት ለውጥ እንደሚሻ አበክረው ተናግረዋል።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ መሥዋዕተ ቅዳሴ ከማሳረጋቸው አስቀድመው በሕዝቡ መካከል ለሰላምታ በሚያልፉበት ወቅት ወደ ተሽከርካሪያቸው በመቅረብ አንድ ወጣት መልእክት ሲወረወርላቸው በጸጥታ አስከባሪዎች ተይዞ እንዲመለስ ቢደረግም መልእክቱ በድረ ገጾች ይፋ ሆኗል፤ እንዲህም ይነበባል «ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ባለዎት ግብረ ገባዊ ኀላፊነትና አስተዋይነት አብዛኛውን ኩባውያን ተጨቁነው ይገኛሉና ስለነዚህ ሰዎች መብት ጣልቅ እንዲገቡና እንዲማጠኑልን»። ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ስለዚህ ሁኔታ የሚያውቁት ነገር ስላለ በንግግሮቻቸው ተገቢውን ጥቆማ አድርገዋል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ከተናገሩት መካከል ሀብት ለማካበት ሲባል በድኾች ላይ የሚደርሰውን እንግልት ለማስወገድ በማሰብ «እግዚአብሔር ቅድስት እናቱ ማርያም ድኻ እንደሆነች ሁሉ ቤ/ያንም ድኻ ትሆን ዘንድ ይፈልጋል» ብለዋል።

አብዛኛው ኩባውያን ካቶሊክ ባይሆኑም እያንዳንዱ ኩባዊ ለር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስን አክብሮት ያላቸውና በኩባም ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ ያምናል። ከወራት በፊትም በር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ጣልቃ ገብነት የብዙ ጊዜ የሻከረ የአሜሪካና የኩባ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየዘበ መምጣቱ ሲታወቅ ይህም በኩባውያን ዘንድ ጥሩ ተቀባይነትን ያገኘ ጅማሬ ነው።

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ይህንን የኩባ ጉብኝት ጨርሰው ወደ አሜሪካ የተጓዙ መሆኑም ታውቋል። 

ምንጭ፡- http://www.herald.co.zw/nearly-1-million-attend-popes-havana-mass/

        http://www.catholicnewsagency.com/news/nine-things-you-missed-from-pope-francis-time-in-havana-24488/

         http://www.catholic.org/news/international/americas/story.php?id=64039

http://www.bbc.com/news/world-latin-america-34318632

አድራሻችን

logo

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን webpageorganizers@gmail.comን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።   

መልእክት ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ

pope"ይቅርታን እና ምሕረትን ማድረግ የሰላማዊ ሕይወት መሠረት ነው"።

“ይቅር ማለት እና ምህረትን ማድረግ የሕይወት ዘይቤያችን ቢሆኑ ኖሮ፥ ስንት ጦርነት፣ ስቃይ እና መከራን እናስቀር ነበር! በግንኙነቶቻችን ሁሉ ይቅርታን የሚያደርግ ፍቅር ያስፈልጋል። ይኸውም በባል እና ሚስት፤ በወላጆች እና በልጆች መካከል እንዲሁም በአካባቢያችን፣ በማኅበረሰባችን እና በፖለቲካውም ማለት ነው። እንዲሁም ይቅርታን ለማድረግ ጥረት የማናደርግ ከሆነ፥ ይቅር አይባልልንም” ማለታቸው ተገልጿል።

ምንጭ - ቫቲካን ራድዮ አማርኛ ዝግጅት