ር.ሊ.ጳ. በአሜሪካ ለምክር ቤቶች አባላትና በኒውዮርክ - በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤት ያደረጉት ንግግር

ር.ሊ.ጳ. በአሜሪካ ለምክር ቤቶች አባላትና በኒውዮርክ - በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤት ያደረጉት ንግግር

pope Un NewYorkየቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ አስረኛው ዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ጉብኝት በአሜሪካ እጅግ ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑንና በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤትና ተቀባይነት እያሳየ መሆኑን አብሮዋቸው የተጓዙት የቅድስት መንበር የኅትመትና ዜና ኃላፊና እንዲሁም የቫቲካን ሬድዮ ጠቅላይ ኃላፊ ገልጠዋል። ሐሙስ እለት በዋሺንግተን ዲሲ በአሜሪካው ርእሰ ብሔር ቤተ መንግሥት ንግግር በማድረግ በቅዱስ ፓትሪክ ቍምስና በጎ አድራጎት የሚረዱ ቤት አልባዎችን ከጎበኙ በኋላ ወደ ኒውዮርክ አቅንተዋል።

ቅዱስነታቸው ትናንትና ከሰዓት በኋላ በኒውዮርኩ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱ የኒው ዮርክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዶላን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሳ አቡነ በርናርዲቶ እና የብሩክሊን ጳጳስ የኒው ዮርክ ከንቲባ የሚገኙባቸው ባለሥልጣኖች የተቀበሏቸው ሲሆን፤ ወዲያውኑ በሄሊኮፕተር ወደ መሀል ከተማ ተጉዘው፣ በማንሃተን ከሚገኘው የሄሊኮፕተር ማረፍያ ወደ ቅዱስ ፓትሪክ በመኪና ተጉዘዋል፣ እንደልማዳቸውም የዚሁ ስምንት ኪሎሜትር ጉዞ ግማሽ በክፍት መኪና ሆነው ሕዝቡን እየባረኩና ሰላምታ እያቀረቡ ወደ ካቴድራሉ ሲደርሱ የካቴድራሉ ኃላፊ ብፁዕ ካርዲናል ዶላንና ተቀብልዋቸዋል።

በካቴድራል ውስጥ ይጠባበቋቸው ከነበሩ አንዳንድ ሕመምተኞችና ቤተሰቦች ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡና ከባረኩ በኋላ እቅፍ አበባ በመንበረ ታቦት አኑሮው በቅዱስ ቍርባን ፊት የግል ጸሎት አሳርገው ከመላው ውሉደ ክህነት ካህናት፣ ደናግል ገዳማውያንና ገዳማውያት እንዲሁም ምእመናን ጋር በካቴድራሉ መዘመራን ተሸኝተው የጸሎተ ሠርክ መዝሙረ ዳዊት ደግመዋል።

ከቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት በተወሰደው “በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።” (1ጴጥ 1፤6) በሚለው ቃል ላይ ተመርኵዘው የሚከተለውን ስብከት አቅርበዋል፣

“ወንድሞቻችን ሙስሊሞችን በሚመለከት ሁለት ስሜቶች ይፈራርቁብኛል፣ አንደኛው ዛሬ ዕለት የመሥዋዕት በዓል ዒል አድሃን ስለሚያከብሩ የሞቀ መልካም ምኞቴን ለማቅረብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በመካ ዛሬ ባጋጠመው አደጋ ለተጉዱ ወገኖቻቸው ቅርበቴን ለመግለጥ ነው፣ አሁን በዚህ ጸሎታችን ሁሉን ቻይና መሓሪ የሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው አብረን እንለምናለን።

ሓዋርያው የሚለን “ምንም እንኳ አሁን አጠር ላለ ግዜ ብዙ ፈተና ቢገጥማችሁ እጅግ ደስ ይበላችሁ!” እነኚህ ቃላት አንድ መሠረታዊ የሆነ ነገር ያሳስቡናል፣ የእኛ ጥሪ በደስታ እንድንኖር ነው፣ ይህ እጅግ ቆንጆ የሆነ የቅዱስ ፓትሪክ ካቴድራል በብዙ ሴቶችና ወንዶች መሥዋዕት ከረዥም ዓመታት በኋላ የተገነባ የካህናት ደናግልና ምእመናን ሥራ ምሳሌ በመሆን እነኚህ ሰዎች የአመሪካ ቤተ ክርስትያንን ለመገንባት ምን ያህል እንዳበረከቱ ያሳየናል፣ ብዙ ጀግኖች መንፈሳዊም ይሁን ቍሳዊ እርዳታ ለማበርከት እስከ መሥዋዕትነት እንደደረሱም የማይዘነጋ ነው፣ ለምሳሌ ቅድስት ኤልሳቤጥ አና ሰቶን የመጀመርያ ነጻ ትምህርት ለዚህ አገር ልጃገረዶች እንደከፈተች እንዲሁም ለመጀመርያ የካቶሊክ ትምህርት ቤትን የከፈቱት ቅዱስ ዮሓንስ ኒውማን ሊጠቀሱ ይቻላል።

እዚህ የመጣሁትም ከእናንተ ካህናት ገዳማውያንና ገዳማውያት ጋር አብሮ ለመጸለይ ሲሆን ምክንያቱም ጥሪያችሁ ታላቁን የእግዚአብሔር መንግሥት በዚህ አገር መገንባት መቀጠል ነው፣ ብዙ እንደተሳቀያችሁ አውቃለሁ፣ በአንዳንድ ወንድሞቻችን ባቈሰሉትና ባደረሱት ዕንቅፋት በዮሓንስ ራእይ እንደሚለው “ከታላቅ መከራ የመጣችሁ ናችሁ” (7፡14) እላችኋለሁ፣ በዚሁ የሥቃይና ከባድ ጊዜ ከጐናችሁ ሆኜ እሸኛችኋለሁ፤ እግዚአብሔርንም በምትሰጡት አገልግሎት አመስግናለሁ፣ በማለት ስለአጠቃላይ ሁኔታቸው ከተናገሩ በኋላ ለአስተንትኖ እንዲረድዋቸው ደግሞ ከሁሉ አስቀድመው የምስጋና መንፈስ እንዲኖራቸው በተለይ መጀመርያ የተጠሩበት ሁኔታ በትምህርታቸው ያደርጉት ጉዞ ወዘተ ስለብዙ ነገር ማመስገንና ዘወትር እግዚአብሔር ያደረገላችውን ማስታወስ እንዳለባቸው፥ በሁለተኛ ደረጃ ድግሞ ልባቸው ጌታን ለማገልገል የሥራ መንፈስ እንዲሞላበትና ሁሌ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነው እንዲገኙ፣ ይህን ሁሉ ሲያደርጉ ደግሞ ከመስቀል የመሸሽ ፈተና እና ቅናት እንዳያሸንፋቸው አደራ በማለት ስብከታቸውን ደምድመዋል፣

እንደገና ስለመላው ዓለም ጸሎተ ምእመናን ቀርቦ ብፁዕ ካርዲናል ድናልድም ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው በመጡበት ሁኔታ ወደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቋሚ ታዛቢ መኖርያ ቤት በመሄድ የራትና የዕረፍት ግዝያቸው አሳልፈዋል።

ዓርብ ጥዋት በከተማዋ ወደሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ሲደርሱ፣ የጽሕፈት ቤቱ ዋና ጸሓፊ የሚገኙባቸው ብዙ ሰዎች ተሰልፈው ተቀብለዋቸዋል፣ ከሕጻናት የአበባ ጉንጉን ተቀብለው ከተሰለፉ ሰዎች አንዳንዶቹ ከባረኩና ሰላም ካሉ በኋላ ከዋና ጸሓፊውና ተባባሪዎቻቸው ጋር መጀመርያ በግል ተገኛኙ፣ በመቀጠልም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል፣

«ውድ ጓደኞች እንደምን አደራችሁ! በዚሁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉብኝቴ ሁላችሁን አመስግናለሁ፣ ላደረገላችሁኝ ደማቅ አቀባበል እንዲሁም ይህ እውን እንዲሆን ለዝግጅቱ አመሰግናለሁ፣ ሰላምታዬን ዛሬ እዚህ ለመገኘት ላልቻሉ ለቤተሰቦቻችሁና ለጓደኞቻችሁ አቅርቡልኝ፣

በዚህ ሕንጻ ውስጥ ከሚሠራው አብዛኛው ለዜናና ለወሬ ብቻ የሚሆን አይደለም፣ ነገር ግን ብዙ ዲፕሎማስያዊ ባህላዊ ምጣኔ ሃብታዊና ፖለቲካዊ ግኑኝቶች እውን የሚሆኑት እናንተ በምታበረክቱት ጥረት ነው፣ ለዚህም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፣ ሲሉ ስለጠንቃቃ ሥራቸው አመስግነው ለሚመጣ ከመጨነቅ ይልቅ ዛሬውኑ አንዱ ለሌላው እንዲያስብና እርስ በእርሳቸው በመቀራረብና እየተረዳዱ ድርጅቱን እንደ አንድ ቤተሰብ እንዲገነቡት፣ ለሰላምና ለፍትህ መሥራት ብቻ ሳይሆን በሰላምና በፍትህ መንፈስ እንዲሠሩ አደራ ብለዋል፣ በመጨረሻም ሁሉንም አመስግነው ለእነርሱና ለቤተሰቦቻቸው እንደሚጸልዩ ቃል ገብተው እነርሱም ስለቅዱስናቸው እንዲጸልዩ የማያምኑም ካሉ መልካም እንዲመኙላቸው አደራ በማለትና በቡራኬ ንግግራቸውን ከፈጸሙ በኋላ በድርጅቱ ሥር ከሚያገልግሉ በዚህ ዓመት በተለያዩ ቦታዎች የሞቱትን ለማስታወስ የአንድ ደቂቃ ጸጥታ የኅሊና ጸሎት ከተደረገ በኋላ ከመላው ዓለም ተሰብሰበው የሚገኙ የመላው ዓለም መሪዎቻችና ተወካዮቻቸው በሚገኙበት የድርጅቱ አደራሽ ሄድዋል፣ በቦታ የነበሩ በጭብጨባ ተቀብለዋቸውል፣ የድርጅቱ አፈጉባኤ

“ዛሬ ጥዋት የድርጅታችን ታዛቢ አባል የሆነችውን የአገረ ቫቲካን መሪ የካቶሊካዊት ቤትክርስትያን ር.ሊ.ጳጳሳት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮስን እናዳምጣለን፣ ካሉ በኋላ መልካም ምኞታቸውን ገልጠው ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እንዲሁም ር.ሊ.ጳ በዓለማችን ስለምታበርከተው ዘርዝረው መድረኩን ለድርጅቱ ዋና ጸሓፊ አስተላልፈዋል፣ ዋና ጸሐፊውም በበኩላቸው “እንደተባበሩ መንግሥታት ድርጅት እርስዎም ሌሎችን ለመርዳት የተገፋፉ ነዎት” በማለት ሌሎችን ከመርዳት ጀምሮ እስከ የአካባቢ እንክብካቤ ያደረጉትን አስተዋጽኦ በመዘርዘር ምስጋናቸውን ካቀረቡ በኋላ “ቅዱስ አባታችን እንኳን ደህና መጡ ቃላችሁን ለማድመጥ ዝግጁ ነን እጅግ አመሰግናለሁ” ካሉ በኋላ አፈጉባኤው እንደገና በማመስገን ቅዱስነታቸው ለጉባኤው ቃላቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርበዋል፣ ቅዱስነታቸውም ይህን ቃል ሰጥተዋል።

“የተከበሩ ፕሬዚደንት! ክቡራትና ክቡራን! እንደምን አደራችሁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ር.ሊ.ጳ ለዚሁ ለተከበረው የአገሮች ጉባኤ ቃል እንዲሰጡ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት እንደልማዳችን እንደገና ቃሌን ለመስጠት እዚህ ስገኝ ታላቅ ክብር ይሰማኛል፣ በስሜና በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ስም ለተከበሩ ባን ኪሙን ልባዊ ምስጋናየን ለማቅረብ እወዳለሁ፣ ደስ ለሚያሰኘው ንግግራቸውም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፣ በመቀጠልም እዚህ የሚገኙ የመንግሥታት መሪዎችን አምባሳደሮችን ዲፕሎማቶችንና እሳቸውን አጅበው ለመጡ ፖለቲከኞችና አጋዦች እንዲሁም በዚሁ ሰባኛው አጠቃላይ ጉባኤ ተሳታፊዎችና ሁሉንም የዚህ ድርጅት ሠራተኞች እና ሁሉንም ከድርጅቱ ጋር የሚተባበሩትን ሁሉ አመሰግናለሁ፣ በእናንተው አማካኝነትም ለመላው ዓለም አገሮች ነዋሪዎች ሰላምታየን ለማቅረብ እወዳለሁ፣ ለመላው ዘመደ አዳም በጎ ነገር ለምታደርጉት ጥረት ሁሉ አመስግናችኋለሁ።

ር.ሊ.ጳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሲጐበኝ የዛሬው አምስተኛ ነው፣ ከእኔ በፊት የነበሩ ብፁዕ ጳውሎስ 6ኛ በ1965ዓም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ በ1979 እና በ1995 እንዲሁም ልሂቅ ር.ሊ.ጳ ቤኔዲክቶስ 16ኛ በ2008 ዓም ጐብኝተው ነበር፣ ሁላቸውም የዚህ ድርጅት ቁምነገርና አበርክቶ በማንኛውም ታሪካዊ ጊዜ ሕጋዊና ፖለቲካዊ መፍትሔ በማፈላለግ የቦታ ርቀትና ድንበሮችን ተሻግሮ ብዙ እንዳበረከቱ ገልጠዋል፣ ቴክኖሎጂካዊ ሥልጣን በተሳሳቱ አገራዊ ርእዮተ ዓለሞችና የውሸት አለም አቀፍ እጆች ሲገባ ጥፋት እንደሚያስከትል ግልጽ ነው፣ ከእኔ በፊት የነበሩ ጳጳሳት የተናገሩትን በመድገምና ድጋፌን በመግለጥ፤ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በዚህ ድርጅት ላይ ያላትን እምነትና ተስፋ አስፈላጊነት እንደገና ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፣” ሲሉ መግብያ ካደረጉ በኋላ የድርጅቱ ሰባኛ ዓመትን በማስታወስ የተገኙ ስኬቶችን በማድነቅ በዚሁ ሰባ ዓመታት ውስጥ ብዙ መሥዋዕትነት በመክፈል ታላቅ አበርክቶ ላደረጉ ሁሉ አድናቆታቸውን ገልጠዋል።

ስለአጠቃላይ የዓለማችን ሁኔታና ከድርጅቱ ለሚጠበቁ በተለይ ጦርነት፣ ረሃብ፣ ስደትና አከባቢን በተመለከተ ሰፊ ንግግር አድርገዋል።

ከዚህ በመቀጠል «ግራውንድ ዜሮ» በመባል የሚታወቀው በመስከረም 11 በመንታ ሕንጻዎች ውድመት የሞቱት ማስታወሻ ባለበት ቦታ በመገኘት ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ጋር በመሆን ጸሎት አሳርገዋል።

ምንጭ፡- http://am.radiovaticana.va/news

በአሜሪካ ለመንግሥት ምክር ቤት አባላት ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር

በተመሳሳይ መልኩ በአሜሪካ ለመንግሥት ምክር ቤት አባላት ያደረጉት ታሪካዊ ንግግርን ከቫቲካን ሬድዮ እንዳገኘነው በመቀጠል አስፍረነዋል፡-

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 24 ቀን 2015 ዓ.ም. በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከተጠዋቱ ልክ 10 ሰዓት በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ምክር ቤት ምሉእ ጉባኤ ተገኝተው ታሪካዊና በሞቀ ጭብጨባ የተሸኘ ንግግር እንዳስደመጡና ቅዱስ አባታችን ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ምክር ቤቱ ንግግር ያስደመጡ የመጀመሪያ ር.ሊ.ጳ. መሆናቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማሲሚሊያኖ መኒከቲ አስታውቀዋል።

ቅዱስነቸው ወደ ምክር ቤት የጉባኤ አዳራሽ እንደገቡም ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት ከተቀመጡበት በመነሳት የእንኳን ደህና መጡ መግለጫ የሞቀ ጭብጨባ በማቅረብ ከተቀበሉዋቸው በኋላ ባስደመጡት ንግግር፦ ምክትል ሊቀ መንበር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር፣ ክቡራት የምክር ቤቱ አባላት ሁሉ ሰላምታን እቅርበው

ወዳጆቼ፡- በዚህች የነጻነት መሬትና የከበሩ እሴቶች ቤት በሆነችው አገር ምክር ቤት ተገኝቼ ንግግር እንዳስደምጥ ላደረጋችሁልኝ ጥሪ አመሰግናለሁ ብለው ገዛ እራሳቸው የአመሪካ ዓቢይ ክፍለ አለም ተወላጅ መሆናቸው አስተዋውቀው፣ በቀጥታ የምክር ቤቱ ተመራጮች የሚወክሉትን ሁሉ የጋራ ጥቅም እርሱም አንድነትና መደጋገፍ ሁሉ በቀላሉ ላደጋ ሊጋለጥ የሚችለውን ለመከላከል የሚለው ክቡር እሴት ለማረጋገጥ በሚደረገው ፖለቲካዊ ጥረት የሚያጋጥሙት ተግዳሮችን በማስታወስ፣ የምክር ቤቱ አባላት እንደ የእስራኤል ልጆች አባትና የሕግ ሊቅ፣ በሕግ አማካኝነት እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር አምሳያ የተፈጠረ መሆኑ ለመከላከል የተጠሩ ናቸው ብለዋል።

ዛሬ ለእናተን የምለው ቃል በእናንተ በኩሉ ለመላ የተባበሩት የአማሪካ መንግሥታት ሕዝብ አቀረባለሁኝ

የጋራ ጥቅምን ተካፍሎ መኖር

ወንዱም ሴቱም ለመንግሥት ግብር ከፋይ ብቻ ሳይሆን ዕለት በዕለት በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልገው ሁሉ ድጋፍ በማቅረብ የኅብረተሰብ ሕይወት የሚገነቡና የሚደግፉ ናቸው ብለው ይኸንን ጉዳይ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት አናሥር ላይ በማተኮር የዛሬው ተጨባጩ ሁነት በታሪክ የአገሪቱ ዜጎች እንደ አብራሃም ሊንኮልን ማርቲን ሉተር ኪንግ ዶሮትይ ደይና ቶማስ መርቶን የመሳሰሉትና ሌሎች የአገሪቱ ዜጎች የበለጠ መጻኢ የጋራ ጥቅም በተካፍሎ የመኖር ሂደት ለማረጋገጥ መስዋዕትከት የከፈሉትን ታላላቅ ሰዎች ታሪክ ጋር በማዛመድ ገልጠዉታል።

አንድ ሕዝብ ወደፊት ለማለትና ይኸንን በክብር ለመከወን በአገሪቱ ታላላቅ ሰዎች አብነት ተሸኝቶ የተለያዩ ቀውሶች ውጥረቶችና ግጭቶች ያልፋል።

አብርሃም ሊንኮልን፦ ነጻነትና ሥጋት

በዚህ የነጻነት ጠበቃና አቃቢ የሆው የአገሪቱ ርእሰ ብሔር አብራሃም ሊንኮን የተገደለበት 150ኛው ዓመት በሚዘከርበት በአሁኑ ወቅት፣ ነጻነት ያለው መጻኢ ለመገንባት ለጋራ ጥቅም ፍቅር፣ ለሌለው የአበል ድጋፍ የሚልና የመተባበር መንፈስ ያለው አስፈላጊነት የማያጠያይቅ መሆኑ ያረጋግጥልናል፣ የምንኖርበት ዓለም ግጭትና አመጽ ጥላቻና አሰቃቂ ተግባር ይባስም ይኽ ዓይነት አሰቃቂ ተግባር በእግዚአብሔርና በሃይማኖት ስም የሚፈጸምበት ሆነዋል። ማንኛውም ዓይነት ሃይማኖት ለግላዊ የአታላይነት ወይንም ለርእዮተ ዓለማዊ አክራሪነት ፈተና የተጋለጠ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ እላይ ከጠቁሱት ሃሳብ ጋር በማያያዝ ክፋትና መልካም ብፁዕናና ኃጢአት ብሎ ለሁለት ለሚከፋፍለው ፈተና እጅ ሳይሰጥ፣ የሃይማኖትን፣ የኅሊናንና የግል ነጻነትን መንከባከብ ያስፈልጋል። ገዳዮች ወይንም አምባገነኖችን መምሰል ሳይሆን እንደ ሕዝብ እነዚህ ጸረ ሰብአዊ የሆኑትን ተግባሮች እምቢ ማለት ይኖርባችኋል።

ሰላም፦ ቃል የተገባውን ማክበርና ማረጋገጥ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሰላም ለማረጋገጥ ማለም፣ ስህተቶችን ማረም ቃል የተገባውን ማክበር በዚህ አኳያ የግልና የሕዝቦች ጥቅም ማነቃቃት ያስፈልጋል። በዚህ መሠረተ ሕንጸትም የእምነት ድምጽ ያለው ጠቀሜታ ማስተዋል ይኖርብናል። ምክንይቱም እምነት በእያንዳንዱ ሰውና በሕብረተሰብ ዘንድ ያለው መልካምነት እንዲጎላ ለማድረግ የሚደግፍ ነውና። በታደሰ ፖለቲካና አዲስ ማኅበራዊ ስምምነት በተካነ ሂደት አማካኝነት መፍትሔ ሊያገኙ ከሚገባቸው ከተለያዩ ኢፍትሓዊ ተግባሮች የሚወለዱት በዓለም የሚታዩት አዳዲስ የባርነት ቅርጾች ሁሉም ለማጥፋት ሁሉም እንደየኃላፊነት አስተዋጽኦ መስጠት ይኖርበታል።

ማርቲን ሉተር ኪንግ፦ ስደተኞችና መስተንግዶ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሰልማ እስከ ሞንቶጎመርይ የጥቁር አመሪካ ዜጎች ለተሟ ሰብአዊ ፖለቲካዊ መብትና ክብር አክብሮት ያለመ ማርቲን ሉተር ኪንግ የመራው የሰላም የእግሩ ጉዞ አስታውሰው፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዲህ ባለ ተግባር የገለጠው ህልም ዛሬም ባለፉት የመጨረሻ ዘመኖች ወደዚህች አገር ለገቡት በሚሊዮን ለሚገመቱ ሕዝቦች ኣስተንፋሶ ሆነዋል።

እኛ የዚህ ክፍለ ዓለም ሕዝቦች ስደተኞችን መፍራት አይገባንም፣ ምክንያቱም ባንድ ወቅት ሁላችን ስደተኞች የነበርን ነን። ይኸንን የምላችሁም እኔ ለገዛ እራሴ የስደተኛ ቤተሰብ ልጅ መሆኔ በማስተዋልና እዚህ በምክር ቤቱ በአባላነት ከምትገኙት ውስጥም ባንድ ወቅት ስደተኞች የስደተኛ ቤተሰብ ተወላጆች ሊኖሩ እንደሚችሉ በማስተዋል ነው ብለዋል።

አዱሱን ትውልድ ለጎረቤትህ ቅርብ ላሌለው ጀርባውን እንዳይሰጥ እናንጸው ብለው፣ ወዳጄ ማን ነው? በአሁኑ ሰዓት የሚታየው ከሁለተኛው የዓለም ጦርነፍ ፍጻሜ ወዲህ ያልታየው የስደተኞች ጸዓት ተከስተዋል። ሌላውና ጎረበቴ ወዳጄ እርሱ ነው። ሁሉም ሊደረግልህ የምትሻው አንተም በተራህ ለሌላው ማድረግ ብቻ ነው የሚያስፈልገው። ብዙ ውጣ ውረድ የሚጠይቅ ጉዳይ አይደለም። ዋስትና የምንሻ ከሆን ዋስትና እንስጥ ሕይወትን የምንሻ ከሆን ሕይወትን እንስጥ እድል የምንሻ ከሆን እድል እንስጥ።

የሞት ፍርድ ማስወገድ

እያንዳንዷ ሕይወት የተቀደሰች ነች፣ እያንዳንዱ ሰው የማይታበል ክብር የተካነ ነው። ስለዚህ ኅብረተሰብ ወንጀለኛው ዳግም በሰላም ከኅብረተስብ ጋር ተቀላቅሎ እንዲኖር በማድረግ ያተርፋል እንጂ ትርፉ ለሞት በመዳርግ አይደለም።

ዶሮትይ ደይ፦ ማኅበራዊ ፍትህና ተፈጥሮን መንከባከብ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የካቶሊክ ሠራተኞች እንቅስቃሴ የመሠረተቸው የእግዚአብሔር አገልጋይ ዶሮትይ ደይን አስታውሰው፣ ዶሮትይ፣ ሰዎችን ከከፋ ድኽነት ለማላቀቅ በኖረቸው ሕይወት የማኅበራዊነትና የፍትኃዊነት አብነት ነች። በዚህ በአሁኑ ወቅት ተከስቶ ባለው የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት አደራ መተባበርና መደጋገፍ እንዳይጠፋ፣ የድኽነት ቀንበር ለመስበር ማንም የማይነጥል ሁሉንም የሚያቅፍ ለጋራ ጥቅም የሚል ተፈጥሮን የሚያከብር የሰለጠነ ኤኮኖሚ ያስፈልጋል። ወቅቱ የመንከባከብ ባህል ለማረጋገጥ ጽናትና የተዋጣለት ሥልት የሚያስፈልግበት ሁነት ነው። ተፈጥሮን ለመንከባከብና ድኽነት ለመዋጋት ሁሉም እንዲተጋ ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር አደራ እንዳሉ ሚኒከቱ ገለጡ።

ቶማስ ሜርቶን፦ የሕዝቦች አገናኝ ድልድይ መገንባት

ቅዱስ አባታችን የሲታውያን ማህበር አባል መነኩሴ የጸሎት ሰውና አስተዋዩ ሊቅ ቶማስ ሜርቶንን አስታውሰው፣ በሕዝቦችና በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ሰላም በማነቃቃት የኖረበት የልዩነትና የጥላቻ መንፈስ የተሞላው ኅብረተሰብና ሥርዓት ሁሉ መጋፈጡን አውስተዋል። ከዚህ ጋር በማያያዝም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና በአገረ ኩባ መካከል የጸናው አዲሱ ግኑኝነት በማስታወስ አደራ አገናኝ ድልድይ እንገንባ፣ የሰላም የውይይት መሣሪያ እንሁን ብለዋል።

የጦር መሣርያ ንግድ ይቁም

በጦር መሣሪያ አቅርቦት የሚፈጸመው በደም ንጹሓን በሚበከለው ሃብት የመደለቡ ጉዳይ ቅዱስነታቸው አውግዘው፣ አስነዋሪውና በዝምታ በመልከቱ ምርጫ ተጠያቂነት እንዲኖረን የሚያደርግ የጦር መሣሪያ ንግድ እቅርቦት ያብቃለት።

ቤተሰብ

ቅዱስነታቸው ባስደመጡት ንግግር በፊላደልፊያ የሚካሄደው ስምንተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ በማስተዋል፣ ለኅብረተሰብ ግንባታ ቤተሰብ ያለው ማእከልነት አስገንዝበው፣ ቤተሰብ ያለው መሆናዊ ሃብትና ውበት ለማስተጋባት እወዳለሁ፣ ያ የቤተሰብና የትዳር መሠረት የሆነው ሰብአዊ ግኑኝነት እጥያቄ ውስጥ ሲገባ ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

ወጣቶች

በአሁኑ ወቅት ወጣት ትውልድ ቤተሰብ ላለ መመሥረት ምርጫ በሚዳርግ ባህል የተጠቃ ሆነዋል። ስለ መረጠው ሳይሆን መጻኢ የመገንባቱ ዕድል በማጣቱና አልፎ አልፎም ተስፋ አልቦ ነጻነት መሳይ አመጽ ተስፋ ቀቢጽነትና ለተለያዩ አመጽ ሰለባ እንዲሆን ይኽ ሁነት በከፋ ባርነት እንዲኖር ስለሚዳርገውም ነው። የወጣቱ ችግር የእኛ ችግር ነው ብለው ለወጣቱ ትውልድ ከፍ ያለ እድል እንዲፈጠርለት አደራ፣ ይህች ብዙ ሰዎች መልካም ህልም እንዲያልሙ ያደረገች መሬት ወጣቶች ያንን ያለፉት አበይት የአገሪቱ ልጆች አስተንፍሶ እንዲያደርጉ አደራ።

ለሁላችሁም የእግዚአብሔርን ቡራኬ እማጠናለሁ፣ ቤተሰቦቻችሁንና ልጆቻችሁን ጌታ ይባርክ፣ ጌታ የአመሪካ ሕዝብን ይባርክ፣ እያንዳንዳችሁን ይባርክ፣ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ፣ ከእናንተ ውስጥ የማያምን ካለም ደግሞ መልካሙን ይመኝልኝ ዘንድ አደራ፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ

እግዚአብሔር አሜሪካን ይባርክ ብለው ያስደመጡት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።