ከአስራ አራት ዓመታት ምሥጢራዊ እስር በኋላ ያረፉት ቻይናዊ ካቶሊክ ጳጳስ

የዋሻው ጳጳስ ከአስራ አራት ዓመታት ምሥጢራዊ እስር በኋላ በ94 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለጸ

Chinese catholic bishopበሀገረ ቻይና ከመሬት በታች በተዘጋጁ ምሥጢራዊ ዋሻዎች ውስጥ ሥርዓተ አምልኳቸውን የሚፈጽሙ ካቶሊካውያን እረኛ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኮስማስ ሺ ኤንዚያንግ (Cosmas Shi Enxiang) ከአስራ አራት ዓመታት እሥር በኋላ  በቻይና እሥር ቤት ውስጥ ሕይወታቸው ያለፈ መሆኑን የቻይና መንግስት የቦዲንግ ከተማ አስተዳደር ለቤተሰቦቻቸው በስልክ አሳውቋል፡፡

የዛሬ አስራ አራት ዓመት እ.ኤ.አ. በዕለተ ዓርብ ስቅለት፣ ሚያዝያ 13 ቀን 2001 ዓ.ም. በቻይና ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት እኚሁ ጳጳስ “የዋሻው ጳጳስ” በመባል ይታወቁ ነበር፡፡ ለአስራ አራት ዓመታትም ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሠረትባቸው የት እንደሚገኙ እንኳን ለማንም ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ በእስር ቆይተዋል፡፡

የ94 ዓመቱ ጳጳስ ለአስራ አራት ዓመታት በታሰሩበት እስር ቤት ውስጥ ከማንም ጋር እንዳይገናኙ እገዳ ተጥሎባቸው የነበረ ሲሆን የሞታቸው ምንስኤ ምን እንደሆነም አልተገለጸም፡፡ ጳጳሱ በመጀመሪያ እ.ኤ.አ. በ1954 ዓ.ም. ታስረው የነበረ ሲሆን ከ1957 እስከ 1980 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት በቻይና ምሥጢራዊ እስር ቤቶች ውስጥ በተደጋጋሚ በመታሰር በከባድ የጉልበት ሥራ ቅጣት ከፍተኛ ስቃይ ተቀብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1981 ዓ.ም. ደግሞ ካቶሊክ በመሆናቸው እና የካቶሊክ ካህን ዋነኛ ተልእኮ የሆነውን ሥርዓተ ቅዳሴን ሲያሳርጉ በመገኘታቸው ብቻ ለሌላ እስር እና እንግልት ተዳርገው ነበር፡፡ በጵጵስና እረኝነት ማገልገል ከጀመሩ በኋላ እ.ኤ.አ በ1989 ዓ.ም. እንደገና ታስረው የነበረ ቢሆንም በዓለም ዓቀፉ ማሕበረሰብ ከፍተኛ ተጽዕኖ ከእስር ሊለቀቁ በቅተዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ አቡነ ኮስማስእ.ኤ.አ. 1921 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን ማእረገ ክህነትን በ1947 ዓ.ም. ተቀብለዋል፡፡ በ1982 ዓ.ም. የረዳት ጳጳስነት በ1995 ዓ.ም. ደግሞ የጳጳስነት ማእረጎችን ተቀብለዋል፡፡

ጳጳሱ ከዚሁ ጋር በተያያዘ “የዋሻው ውስጥ ጳጳስ” ብፁዕ አቡነ ጀምስ ዙ ዢሚን (James Su Zhimin) እ.ኤ.አ. ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ በቻይና ምሥጢራዊ እስር ቤት እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡

ምንጭ: ucanews - /ሳምሶን ደቦጭና ሃብታሙ አብርደው/

 

አድራሻችን

                 ገዳመ ቅዱስ ዮሴፍ ዘሲታውያን

                    ፖ.ሳ.ቁ. 21902
                 አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
             Phone: +251 (116) 461-435

              Fax +251 (116) 458-988

               contact@ethiocist.org

             http://www.ethiocist.org

 
 

ለድረ ገጻችን የሚሆን ጽሑፍ ካለዎ

1- የኢሜል አድራሻችንን contact@ethiocist.org ን ተጠቅመው አሊያም

2- ይህን ሲጫኑ በሚያገኙት CONTACT FORMበሚለው ቅጽ ላይ ጽሑፍዎን ለጥፈው ወይም 

3-facebook አድራሻችን https://www.facebook.com/ethiocist.org በግል መልእከት ይላኩልን

በተጨማሪም የሚያካፍሉት ጠቃሚ የድረገጽ አድራሻ ካለዎ ይላኩልን።